Chapter List
Chapter One
Course Topics
1-ለሞተር ሳይክል ወይም ለአውቶሞቢል የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሆን በያንስ የአራተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀና እድሜው 18 ያላነሰ፡፡
2-ለታክሲ፡ለፈሳሸ ወይም ለህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሆን ቢንስ የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና አድሜው 24 ያላነ፡፡
3-ለደረቅ ጭነት ወይም ለልዩልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሆን ቢንስ የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና አድሜው 20 ያላሰነ፡፡
1-የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማግኘት የሚያመለክት ማናቸውም ሰው ባለ ሞተር ተሸከርካሪ በሚገባ ለማንቀሳቀስ ከሚያውክ ማንኛውም ዓይነት የአካል ጉዳት ወይም የጤና መታወክ ነጻ መሆን አለበት፡፡
2-ማንኛውም አመልካች ባለሞተር ተሽከርካሪ ለማስከርከር ብቁ መሆኑ ባለስልጣኑ ወይም ፈቃድ ሰጪው አካል ከጤና ጥበቃ ሚኒስተር ወይም ቢሮ ጋር በመመካከር በሚያወጣው መስፈርት መሰረት በሚመረጥ የሕክምና ተቆም በሚደረግ ምርመራ ይረጋገጣል፡፡
3-ፈቃድ ሰጪው አካል በህክምና ተቆም ምርመራ ውጤት ተቀባይነት ላይ ጥርጣሬ ካለው በሌላ የህክምና ተቆም ድጋሚ ምርመራ እንዲያደርግ ሊጠየቅ ይችላል፡፡የሆላኛው ውጤት ከፊተኛው ጋር የሚጣጣም ከሆነም የመጨረሻ ይሆናል፡፡
-›በሁለት የህክምና ተቆምት የተሰጠው የህክምና ውጤት የተለያየ ከሆነ ፈቃድ ሰጪው አካል ለመረጠው 3ኛ የህክምና ተቆም ተልኮ የሚሰጠው የህክምና ውጤት የመጨረሻ ይሆናል፡፡
1-የማንኛውም ምድብ የተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ጸንቶ የሚቆየው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ለ4አመት ይሆናል፡፡
2-ማንኛውም የተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በዚህ አዋጅ አንቀጽ መሰረት የተደረገ የጤንነት ምርመራ ውጤት ሲቀርብና ተገቢው ክፍያ ሲፈጸም በእያንዳንዱ እድሳት ወቅት በየ4አመቱ ይታደሳል፡፡
3-የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ባለቤት ፈቃዱን ለፈቃድ ሰጪው አካል ራሱ ወይም በህጋዊ ወኪል አማከኝነት በማቅረብ ሊያሳድስ ይችላል፡፡ሆኖም ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በወኪል አማካኚነት ማሳደስ አይቻልም፡፡
4-የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ባለቤት እድሜው ከ55አመት በላይ ከሆነ ፍቃዱ በየ2አመቱ መታደስ አለበት፡፤
5-የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን በ60ቀን ውስጥ ሳያሳድስ የቀረ አሽከርካሪ የተግባር ፈተና ተፈትኖ ሲያልፍ የብቃት ማረጋገጫውን ፈቀድ ይታደስለታል፡፤
1-የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የተሰጠው ሰው በፈጸመው የትራፊክ ደንብን የመተላለፈ ጥፋት ሪከርድ ወይም በሌላ አጥጋቢ ምክንያት ላይ ተመስርቶ የጤንነት ሁኔታው ወይም የመንዳት ችሎታው አጥጋቢ አለመሆኑ ሲረጋገጥ ፈቃድ ሰጪው አካለ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድን ማገድ ወይም ባለፍቃዱ የጤንነት ሁኔታ ምርመራ አነዲያደርግ ወይም የችሎታ ማረጋገጫ ፈተና እንዲወስድ ወይም ሁለቱንም እንዲፈጽም ሊያስገድደው ይችላል፡፡
2-የተካሄደውን የጤና ምርመራ ወይም የችሎታ ማረጋገጫ ፈተና ውጤት የባለፍቀዱ የጤና ሁኔታ ወይም የመንዳት ችሎታ አጥጋቢ አለመሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ወይም ባለፍቃዱ ያለበቂ ምክንያት የምርመራ ወይም የፈተና ውጤቱን በ3ቀናት ውስጥ ሊያቀርብ ካልቻለ ፈቃዱ ሰጪው አካል ፈቃዱን ሊሰርዝው ይችላል፡፡
3-ሚኒሲቴሩ በአሽከርካሪው የጥፋት ሪከርድ መሰረት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ለማገድወይም ለመሰረዝ የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ ያወጣል፡፡
4-በተራ ቀጥር 1እና2 መሰረት በተሰጠው ውሳኔ በደረሰው በ፴ቀናት ውስጥ ለሚኒሲቴሩ ቅሬታውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡የሚኒሲቴሩ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
ቅጣት
1-ይህን አዋጅ ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው ህግ ይቀጣል፡፡
2-ጥፋት የፈጸመ አሽከርካሪ ቀጥሎ በተያያዘው ሰንጠረዥ እና የተመለከተው ቅጣት ይጣልበታል፡፡
3-በተጣለበት የገንዘብ ቅጣት ጥፋተኛ አይደለሁም የሚል አሽከርካሪ በ30ቀን ውስጥ ለሚኒሲቴሩ ለሚወክለው አካል አቅርቦ ለማሻር ካልቻለ ለፈቃድ ሰጪው አካል ገንዘቡን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
4-አሽከርካሪው በተሰጠው ጊዜ የተጣለበትን የገንዘብ ቅጣት ገቢ ሳያደርግ ቢቀር የአሽከርካሪው ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰረዛል፡፡
->ለቅጣት አፈጸጸም ሲባል በአሽከርካሪ የተፈጸመ ቀላል ጥፋት ለ1አመት እና ከባድ ጥፋት ለ3አመት በሪከርድነት ይያዛል፡፡
CHAPTER TWO
ስነ-ባህሪ ማለት ምን ማለት ነው?
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ
የማሽከርከር ስነ-ባህሪያዊ ጉዳዮች
የባህሪ መለዋወጥ መንስኤዎች
የአሽከርካሪዎች ሙያዊ ስነ-ምግባር
ሶስቱ የማሽከርከር ባህሪያት ዘርፎች
የማሽከርከር ባህሪ ስነ-ባህሪያዊ ዘርፎች
የመልካም አሽከርካሪ ባህሪያት የማዳብር ስልት
የተለያዩ የስነ-ባህሪ ባለሙያዎች ለስነ-ባህሪ የተለያየ ትርጉም ሰጥተዋል፡፡ከነዚህ ትርጉሞች ውስጥ ሁለቱ እንደሚከተለው ተገልጻል፡፡
1-ስነ-ባህሪ የሰዎች እና የእንስሳትን ባህሪይ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዲሲፒሊን ነው፡፡
2-ስነ-ባህሪ ባህሪንና የአዕምሮን የአስተሳሰብ ሂደት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዲሲፒሊን ነው፡፡ከነዚህ የስነ-ባህሪ ትርጉሞች የምንረዳው ሁለት ነገሮችን ነው፡፡የመጀመሪያው ስነ-ባህሪ የሚያጠናው ስለባህሪ እና የአስተሳሰብ ሂደት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የስነ-ባህሪ ባለሞያዎች ባህሪንና ያስተሳሰብን ሂደት የሚያጠኑት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሆኑን ነው፡፡
ባህሪ፡-የሠው አስተሳሰብ፤አመለካከትና ድርጊት ውጤት ነው፡፡በቀጥታ ሊቃኝ ሊመዘገብና ሊለካ የሚችል ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሊታወቅ የሚችል ሊሆን ይችላል፡፡
<->ባህሪን መግለጽ
<->የተለያዩ ባህሪያትን መንስኤ ማብራራት፡
<->ወቅታዊ የባህሪን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የወደፊቱን መተንበይና፤
<->ባህሪን ማሻሻል ማለትም የሰው ልጅ መልካምና መጥፎውን ባህሪያትን ሊያዳብር ይችላል፡፡መልካም ያልሆነውን ባህሪ በተለያየ የስነ-ባህሪ ዘዴዎች መለዎጥ ሌላኛው የስነ-ባህሪ ግብ ነው፡፤
የማሽከርክር ስነ-ባህሪ አሽከርካሪራች በሚያሽከረክሩብት ወቅት የሚያሳዩትን ባህሪ የሚያጠና የስነ-ባህሪ ዘርፍ ነው፡፡
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ዋና አላማ በተሸከርካሪ የሚደርስ አደጋን መቀነስ ነው፡፡ይህም በዋናነት ሊከናወን የሚችለው አላስፈላጊ የማሽከርከር ባኅሪን በማስተካከል ነው፡፡አሽከርካሪዎችን በሚከተሉት ጉዳዬች አኒዲያበረታ አድርጎ በማሰትማር ነው፡፡
1.ትህትና፡-ለመንገደኞች ተሁት መሆን፤
2.ርህራሄ፡-የሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎችን ስሜት መጠበቅ፤
3.-እንደዜጋ ህግና ደንብን አክባሪ መሆን፤
4.-ከሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ጋር መንፈሳዊ ተስስር መፍጠር፤
5.-የፈጠራ የአነዳድ ልምዶችን እና የዘመኑን የሳይነስ ግኝቶች ማዳበር፤
6.-የሌሎችን መንገድ ተጠቃሚ ስሜት መጋራት ናቸው፡፡
1.ዝግጁነት፡-ዝግጅነት የብስለት፤የችሎታ፤የትምህርትና የመነሳሳት የጋራ ውጤት ነው፡፡የዝግጁነት መገለጫ የሆኑትና ከማሽከርከር በፊት ሊጤኑ የሚገባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ይገለጻል፡፡
-ለማሽከርከር ጤነኛ መሆንህን ማረጋገጥ፡፡
-መፈተሸ ያለብኅን ነገር መፈተሸ ማለትም ተሸከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ፡፡
-የመንገድ፤የአየር እና የትራፊክ ሁኔታ በማሽከርከር ሂደት ላይ የሚፈጥረውን ችግር ቀድሞ መገመት፡፡
2-መነቃቃት፡-መነቃቃት በሰዎች ውስጥ የለ ሁኔታ ሆኖ ባህሪን ወደ ግብ የሚያንቀሳቅስ ሂደት ነው፡፡ንቁ ወይንም ተነሳሽነት የለው አሽከርካሪ በማንኛውም የትራፊክ ሁኔታ ውሰጥ የሚወሰደው ውሳኔና እርምጃ ፈጣን መሆን እንዳለበት ይረዳል፡፡
3.ሀ.መገንዘብ፡-መረጃን ከአካባቢያችን በስሜት ህዋሳችን የመቀበል፤የመለዎጥና ወደ አእምሮአችን የመላክ ሂደት ነው፡፡ ማለትም በማየት፤በመስማት፤በማሽተት፤በመቅመስና በመዳሰስ ነው፡፡ከ80-90% አካባቢን ለማወቅና ስለ አካባቢ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችለው በማየት ነው፡፡ በመቀጠልም ጆሮ ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል፡፡
ለ.ትኩረት በስሜት ህዋሳችን ከሚደርሰን መረጃዎች መካከል ዋናውንና ተፈላጊውን የመምረጥ ሂደት ነው፡፡
ሐ.ማስተዋል፡-በስሜት ህዋሳችን ከሚደርሰን መረጃዎች የመምረጥ፤ማቀናበርና ትርጉም የመስጠት ሂደት ነው፡፡
ለባህሪ መለዎጥ መንስኤዎቹ በዋናነት የሚከተሉት ናቸው፡፡
-ከተፈጥሮ የሚወረስ፤ከአካባቢ ሁኔታዎች፤አካላዊ ሁኔታ፤ኀይለ ስሜታዊ ውጥረት፤ስልጠናና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
-ከቤተሰብ የወረስናቸው ባህሪያት ያለን አመለካከት፤አስተሳሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡
-የምኖንርበት አካባቢ፤በእኛ ዙሪያ ያለው ህዝብ ፤ሰዎች የሚሉዋቸውና የሚየደርጉዋቸው ማንኛውም ቁሳቁስ ያካትታል፡፡
-አካላዊ ሁኔታ ለምሳሌ በሚደክመንና በህመም ስሜት በሚሰማን ወቅት የባህሪ መለዋወጥ ልናሳይ አንችላለን፡፡
-ሀይለ ስሜታዊ ውስጣዊ ፍላጎትን፤ፍቅርን፤ጥላቻን፤ሀዘንን፤ብስጭትን ወ.ዘ.ተ ያመለክታል፡፡
-ስልጠና የተመረጠ አመራርና ዕቅድ ባለው መንገድ የሚከናወን ድረጊት ሲሆን የሰው ልግ በሚፈልገው ሁኔታ ለማስተማር ያስችላል፡፡
-ሙያ ማለት በህብረተሰቡ ውስጥ የተከበረና የተወደደ የስራ መስክ ሆኖ በተወሰነ የእውቀት መስክ በትምህርትና ስልጠና የሚገኝ ነው፡፡
-ስነ-ምግባር፡-ስነ-ምግባር መልካሙንና መጥፎውን ለመለየት የሚያስችልና መጥፎውን በመተው መልካሙን እንድንከተል የሚያበረታታ እሴት ነው፡፡
-የሙያ ስነ-ምግባር፡- ማለት ባለሙያው በተሰማራብት ሙያ የሚሰራውን ስራ ውጤታማ እንዲሆን እንደተሰማራበት የሙያ አይነት አባላቱ በጥብቅ መከተል የሚገባቸውን መርሆችእና ስነ-ስርዓቶችን ያመለክታል፡፡
.ሙያዊ ስነ-ምግባራቸውን አክብረው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች የሚከተሉትን መልካም ተግባራት ያከናውናሉ፡፡
-ከነዱ አይጠጡ፤ከጠጡ አይነዱም፤
-ያለምንም እረፍት ከ4 ሰዐት በላይ አያሽከረክሩም፤
-የእንቅለፍ ስሜት በተሰማቸው ጊዜ ሙመሉ እረፍት ይወስዳሉ፤
-በእንቅስቃሴ በማቆም ሂደት ተገቢውን ምልክት በተገቢው ቦታና ጊዜ ይጠቀማሉ ወ.ዘ.ተ
-ሞገድኘት፤ከሚፈለገው በላይ ራስ ወዳድነት፤ሀይለ-ስሜታዊ አለመረጋጋት፤ቸልተኝነት፤ትኩረት ለመሳብ መሞከር፤ሀላፊነት መዘንጋት፤ሱሰኝነት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በማሽከርከር ሂደት አሽከርካሪው በሌሎች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የሚረዳው ባህሪ በተረበሸ ስሜት ተጽዕኖ ስር በወደቀበት ሁኔታ የሚያሽከረክርበት ሂደት ነው፡፡
-በፍርሃት ውሰጥ ሆኖ ማሽከርከር፤
-በጭንቀት ውስጥ ሆነው ማሽከርከር፤
-በማሽከርከር ላይ እያሉ አትኩረትን በሌላ ነገር መውሰድ፤
-ተናደው ተቆጥተው ወይም እነዚህን መሰል ስሜት ውስጥ ሆነው ማሽከርከር፤
-አልኮል፤አደንዛዥ ዕጽ፤ከባድ መድሃኒት ወስዶ፤በእንቅልፍ፤በድብርት ወይም ከባድ ህመም እየተሰቃዩ ማሽከርከር
1.ትግስት ማጣት እና ትኩረት አለመስጠት፤
-የትራፊክ መብራት አለማክበር፤
-ያለአግባብ ረድፍን መቀየር ወይም መሽሎክሎክ፤
-ከተፈቀደው ፍጥነት በላየ ማሽከርከር፤
-የማቆራጫ መንገዶችን መዝጋት ወ.ዘ.ተ
2.ተጽዕኖ የማድረግ ትግል፤
-በበቀል ምክንያት በድንገት ፍሬን መያዝ፤
-ለመበቀል ተሸከርካሪን መድንገት ማቃረጥ፤
-የተሸከርካሪ ጥሩምባ በተደጋጋሚ ማስጮህ፤
-በምልክትና በመሳደብ ማስፈራራት፡፡
3.ግድየለሽነት እና የመንገድ ዳር ላይ ጠብ ናቸው፡፡
-በአልኮል መጠጥ ተመርዞ ማሽከርከር፤
-በጣን ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት ማሽከርከር፤
-መሳሪያ መደገን ወይም መተኮስ፤
-መንገድ ዳር መኪና በማቆም ማስፈራራት ወይም መደብደብ፡፡
-ረድፍዎን ላለመልቀቅ ሲሉ ፉክክር ውስጥ አለመግባት፤
-ጠያፍ ስድቦችንና ምልክቶችን ችላ ማለት፤
-የአይን ለአይን ግንኙነትን ማሰወገድ፤
-እግሩን ሳያባብሱ በሰላም ለመጨረስ ጥረት ማድረግ፡፡
1ኛ.የስሜት ባህሪ፤-ፍላጎትን፤አመለካከትን፤እሴትን፤መነሳሳትንና ማንኛውንም ግብ ያለመ የሰዎች ድርጊት ያጠቃልላል፡፡
2ኛ.የመገንዘብ ባህሪ፡-መረዳትን፤ማሰብን፤ምክንያት እና ማናቸውንም ውሳኔ መስጠትን እና የሰዎችን ደርጊት ማጤንን ያካትታል፡፡
3ኛ.የክህሎት ባህሪ፡-በአዕምሮ አዛዥነትና በአካላችን እንቅስቃሴ የሚፈጠሙ ማናቸውንም የክሂሎት ባህሪ ያካትታል፡፡
1ኛ.ኀላፊነት
ሀ)ስሜታዊ ሐላፊነት
-ለሌሎች ማሰብና ስነ-ምግባራዊነት
-ለማሽከርከር ተግባር፤ሃሳብና እንቅስቃሴ ስነ-ምግባራዊና ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን መጠቀም፤
-ለሌሎች ላይ አደጋንና ጉዳትን ላለመፍጠር መጠንቀቅ፤
የስሜት ሃላፊነት ጉድለቶች
-ራስ ወዳድነትና ቅንነት የጎደለው አስተሳሰብ
-የበቀልኝነት ስሜት፤
-በራስ ላይ የደረሰን ችግር ለሌሎች መሻት፤
-የሌሎችን ስሜትና መብት መጣስ፡፡
ለ)አእምሮኣዊ ሃላፊነት
-አወንታዊ ህሊናዊ አስተሳሰብ አእምሮኣዊ ጤንነት
-የራሰንና የሌሎችን የማሽከርከር ተግባር ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት ቀድሞ መገመት፤
-ሰዎችንና ንብረትን ከአደጋ የሚጠብቅና የሚከላከል ፤
-በማሽከርከር ወቅት ራስን የተለያዩ ስሜቶችን ነጻ ማድረግ፡፡
የአእምሮኣዊ ሀላፊነት ጉድለት
-አሉታዊ ህሊናዊ አስተሳሰብ እና አደገኛ የሆነ ባህሪ፤
-ሌሎች አሽከርካሪዎች ይተቹኛል ያወግዙኛል፤ያጠቁኛል የሚል አስተሳሰብን መያዝ፤
-የሌሎች አሽከርካሪዎችን ባህሪ በአቁዋማቸውና መኪናቸው ሁኔታ መገመትና ዝቅ አድርጎ ማየት፡፡
-መኪና እየሽከረከሩ በቅዠትና በቀን ህልም ውስጥ መሆን፡፡
ሐ)ክሂሎታዊ ሃላፊነት
-ደስተኝነትና እርካታ፤
-በመልካም ስሜት ውስጥ ሆኖ መኪና ማሽከርከር፤
-በማሽከርከር ሁኔታ ላይ ለምናያቸው መልካምና ጥሩ ነገሮች አድናቆትን መግለጽ፡፡
የኪህሎታው ሓላፊነት ጉድለት
-ውጥረትና ድብርት፤
-በማሽከርከር ሂደት መፍራት፤መጨነቅና አለመረጋጋት፤
-በማስከርከር ወቅት በስህተት ምክንያት ራስን ዝቅ አድርጎ ማየት፡፡
2ኛ.ጥንቃቄ ወይም ደህንነት
ሀ)ስሜታዊ ደህንነት
-ራስን ማዘጋጀትና ሚዛናዊነት፤
-ለሌሎች አውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ሚዛናዊ ለመሆን መሞከር፤
-የማሽከርከር እንቅስቃሴን ላለማሰናከል ጣልቃ ላለመግባት ፍላጎት ማሳየት፡፡
የስሜት ደህንነት ጉድለት
-የሞገደኝነት ስሜት
-ለመቅደም ራስን ውድድር ስሜት ውስጥ ማሰገባት፤
-የቁጣ ስሜት ማሳየት፤
-ሌሎች አሽከርካሪዎችን ፈታኝ ሁኔታ ማሰገባት፡፡
ለ)አእምሮኣዊ ደህንነት
-ሚዛናዊ መለያ ባህሪያት፤
-ምክንያታዊና ሚዛናዊ የሆነ ገለጻ መስጠት፤
-ክስተቶችን ለመረዳት ሁኔታዎችን መረዳት፤
አእምሮኣዊ ደህንነት ጉድለቶች
-ሚዛናዊነት የጎደለው መለያ ባህሪት፤
-የራስን የማሽከርከር ባኅሪና ጥፋት በተሳሰተ መንገድ መተርጎምና መከላከል፤
ሐ)ክህሎታዊ ደህንነት
-ትህትና የተሞላበት መግባባትና የመረጋጋት ስሜት፤
-ፈታኝ ስሜትን ጎጅ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ማረጋጋትና ግፊትን መቻል፤
-በእግረኞችና በሌሎች የአውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ላይ ፀያፍ የሆኑ ቃላቶችንና ተግባሮችን ከመፈጠም ራስን መቆጠብ፡፡
የክህሎታዊ ደህንነት ጉድለት
-ትህትና የጎደለው ምልልስና የተጋነነ አፀፋ፤
-ለሌሎች አውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች በቃል ወይም በምልክት መሳደብ፤
-እነዲሁም መተቸት፤መናቅና ማጣጣል፡፡
3ኛ.ብቃት
ሀ)ስሜታዊ ብቃት
-ደንብን ማክበርና ልበ-ሙልነት፤
-በራስ መተማመን መንፈስ ማሽከርከር፤
-ለትራፊክ እንቅስቃሴ እራስን ማሰገዛት፤
-በትራፊክ መብራቶች ምልክቶችና ማክብር፡፡
የስሜታዊ ብቃት ጉድለት
-ደንብና ስርአትን ያለማክበርና በራሰ ያለመተማመን፤
-ለትራፊክ ፖሊስ እና ደንብ አስከባሪዎች በጥላቻ ማየት፤
-ታጋሽ ያለመሆን፡፡
ለ)አእምሮኣዊ ብቃት
-እውቀትና ግንዛቤ፤
-መረጃዎችን ማወቅና በአእምሮ መያዝ፤
-ትክክለኛ የማሽከርከር ጥበብ መለማመድ፤
የአእምሮኣዊ ብቃት ጉድለት
-በመረጃ ያልተደገፈና የተዛባ አስተሳሰብ፤
-መንገዱ በሚፈቅደው ፍጥነት መሰረት ማሽከርከር መንቀርፈፍ እነደሆነ ማሰብ፤
ሐ)ክህሎታዊ ብቃት
-ትክክለኛ ተግባርና ጠንቃቃነት፤
-ለትራፊክ ምልክቶች እና ለሌሎች የአውራ መንገድ ተጠቃሚዎች እንቅስቃሴዎች ትኩረት መስጠት፡፡
የክህሎት ብቃት ጉድለት
-ትክክለኛ ያልሆነ አካሄድና ትኩረት ማጣት፤
-ያለበቂ አትኩረትና በሌላ ሃሳብ ተጠምዶ ማሽከርከር፡፡
1.መልካም ያልሆነ ስሜትን መቆጣጠር
2.ጥቃቅን የማሽከርከር ስህተቶችን ልምድ ያለማድረግ
3.እራስን የማረም ዘዴ
4.ወደ አላስፈላጊ የማሽከርከር ባህሪ የመገፋፉ ሁኔታዎችን ማስወገድ
5.ለራስ ህይዎት ዋጋ መስጠት
6.ውጤታማ የመግባባት ክህሎት ማዳበር
ሀ)መቻቻል፡-የማንወደውን ወይም የማንስማማበትን አመለካከት ያናኖር ዘቤ እምነት ወ.ዘ.ተ ለመፈቀድ ዝግጁ መሆን፡፡
ለ)ማካፈል፡-አንዳንድ ነገር በጋራ ለማከናወን ከሌሎች ጋር መሳተፍ፡፡በሌላ አነጋገር ያለህን ነገር ሌላው አንዲጠቅምበት ፍቃደኛ መሆን፡፡
ሐ)አዛኝ መሆን፡-ሌሎች ሰዎች ችግር ሲያጋጥማቸው ችግሩን እደራስ በማየትና በመንገንዘብ ችግሩ የሚቃለልበትን መንገድ መፈለግን ያካትታል፡፡
መ)መደራደር፡-ስሜትን የሚጎዱና እራስን ከአደጋ ሁኔታዎችን የመቆቆም ችሎታ ነው፡፡
መሰረታዊ የተሸከርካሪ ክፍሎች
አንድ ተሸከርካሪ በዋናነት ከ5 መሰረታዊ ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡
1ኛ)ኢንጅን(ሞተር)
ኢንጅን ማለት በሲሊነደር ውስጥ እሳት ሲቀጣጠል የሚገኘውን የሙቀት ሀይል ወደ መካኒካል ሀይል በመለወጥ የተሸከርካሪ ክፍሎችን ያንቀሳቅሳል፡፡
ኢንጅን ከ3 ዋናዋና ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡
1ኛ.ሲሊነደር ሄድ(ቴስታታ)፡-
በውስጡ ቫልቮችን፤ቫልቭ ጋይዶችን፤ቫልቭ እስፕሪንጎችን፤የራዲያትር የላይኛው ማኒኬቶ(ሆዝ)፤ካርቡሬተርን፤ካምሻፍትን፤ብላንቸሪዎችን፤ጭስ መውጫውን እና የመሳሰሉትን ክፍሎች ይዛል፡፡
2ኛ.ሲሊንደር ብሎክ/ማኖብሎክ/፡-
በውስጡ ሲሊንደር፤ፒስተን፤ክራንክ ሻፍት(ኮሎ)፤የዘይት ፊልትሮና ፓምፕ....፡፡
3ኛ.ክራንክ ኬዝ፡-
በውስጡ ስቶኮፓ(ኦይል ፓን) ያለበት ክፍል ነው፡፡
-ኢንጅን በሚጠቀመው የነዳጅ አይነት በሁለት ይከፈላል፡፡1)የቤንዝን 2)የናፍጣ ሞተር
-ኢንጅን በማቀዝቀዣ ዘዴ በሁለት ይከፈላል፡፡1)በውሃ የሚቀዘቅዝ 2)በአየር የሚቀዘቅዝ
-ኢንጅን በፒስተን እንቅስቀሴው በሁለት ይከፈላል፡፡1)ባለሁለት ምት፡-በአንድ ሙሉ ዙር የክራነክ ሻፍት እንቅስቃሴ ፒስተን ወደታች ሲወርድ የማስወጣትንና የሃይል ምትን፤ወደላይ ሲዎጣ የማስገባትና የእመቃን ያከናውናል፡፡
2)ባለ አራት ምት እንቅስቃሴ፡-በሁለት ሙሉ ዙር የክራነክ ሻፍት እንቅስቃሴ በማሰገባት፤በእመቃ፤በሀይል ምት፤በማስዎጣት ይሰራል፡፡
የኢንጅን ዋናዋና ክፍሎችና ተግባራቸው
ሀ)ሲሊንደር፡-ጣሳ መሰል ቅርጽ ኖሮት ከላይና ከታች ክፍት የሆነ በውስጡ አየርና ነዳጅ በመግባት ከታመቀ በሁዋላ በመቀጣጠል ሀይል ይፈጠራል፡፡
ለ)ፒሰቶን፡-በሲሊነደር ውስጥ በመሆን በተለያ ጊዜ ወደ ላይና ወደ ታች በመንቀሳቀስ አየርንና ቤንዚንን ስቦ በማሰገባት አምቆ ሀይል እንዲፈጠር የሚያግዝና በማስወጣት ምት ጊዜ ጭሱን ከሲሊነደር ውስጥ የሚያስወጣ ክፍል ነው፡፡
ሐ)ፒሰተን ፒን፡-ፒስተንና ኮኔክቲግ ሮድ ከአገነኝ ዘንግ ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡
መ)ኮኔክቲነግ ሮድ፡-ፒስተንና ክራነክ ሻፍትን የሚያገናኝ
ሠ)ፒስተን ሪንግ፡-በአንድ ፒሰተን ላይ ሀለት ስራወችን ይሰራል፡፡የእመቃ ፋሻ እና የዘይት ቀለበት ናቸው፡፡
ረ)ክራነክ ሻፍት(ኮሎ)፡-ወጣ ገባ ቅርጽ ያለው፤የሙቀትን ሀይል መሸከም የሚችል፤የፒስተንን የቀጥታ እንቅስቀሴ ወደ ክብ(360ድግሪ)የሚለውጥ ነው፡፡
ሸ)ካም ሻፍት(አልብሮካም)-በክራነክ ሻፍት ላይ እንደ ተሸከርካሪው አይነት በ3 ዘዴዎች በመገጠም ማለትም ጥርስ ለጥርስ፤ በቺንጋ ወይም በሰንሰለት በመገጠም -አስገቢና አስወጭ ቫልቮችን እንዲከፈቱ፤የዘይትና የነዳጅ ፓምፕ እንዲሰሩ፤በቤንዝን ሞተር ላይ የዲስተሪቢውተር ሻፍት እንዲሽከረከር ያደርጋል፡፡
ቀ)ፍላይውል(ቮላኖ)፡-በክራንክ ሻፍት ላይ በስተሁዋላ በመገጠም 3 ተግባራትን ይሰራል፡፡-የሞተርን ሚዛን ይጠብቃል፤ለሞተር ማስነሻነት፤ለፍሪሲዮን መገጠሚያነት ያገለግላል፡፡
የሞተር ሀይል አጋዥ ክፍሎች
--ሞተር ትክክለኛውን ስራ እንዲሰራ የሀይል አገዥ ክፍሎች ያስፈልጉታል እነርሱም፡-
1----የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች፤
2----የማቀዝቀዣ ክፍሎች፤
3----የማለስለሻ ክፍሎች፤
4----የእሳት አቀጣጣይ ክፍሎች፡፡
1.የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች
የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች በሁለት ይከፈላሉ፡-
1ኛ.የቤንዝን ሞተር የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች፡-
-የነዳጅ መያዣ(ሳልባትዮ)፡-በቂ ነዳጅ የሚይዝና በውስጡ ማጣሪያ የሚይዝ ክፍል ነው፡፡
-የነዳጅ መስመር:-ከሳልባትዮ ወደ ፓምፕ ወይም ወደ ካርቡሬተር ነዳጅን የሚያስተላልፍ ነው፡፡
-ፊልትሮ:- ወደ ካርቡሬትርና ወደ ሲሊንደር የሚገባውን ነዳጅ አጣርቶ የሚያስተላልፍ ነው፡፡
-የነዳጅ ፓምፕ(ፓምፔታ)፡-ነዳጅን ከሳልባትዮ በመሳብ በግፊት ሀይል ወደ ካርቡሬተር ያስተላልፋል፡፡
-ካርቡሬተር፡-አየርና ነዳጅን መጥኖና ቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር የሚያስተላልፍ ክፍል ነው፡፡
-ቾክ ቫልቭ፡-በካርቡሬተር በላይኛው ክፍል በመገጠም የአየር ማሰገቢያውን ለመዝጋት ወይም ለመክፈት የሚያገለግል ክፍል ሲሆን በቅዝቀዜ ወቀት ሞተር ስናስነሳ የአየሩ መጠን አነስ ብሎ የነዳጅ መጠን መብዛት ስላለበት የአየር መተላለፊያውን በመዝጋት ሞተር ቶሎ እንዲነሳ ያደርጋል፡፡
-ፍሎት ቦል(ተንሳፋፊ ካስ)፡-በካርቡሬተር ውስጥ የነዳጅን መጠን የሚከታተል ክፍል ነው፡፡
ጠባቡ ካርቡሬተር ጎሮሮ(ቬንቹሪ)፡-በካርቡሬተር ውስጥ አየርና ነዳጅ ተመጥነው የሚደባለቅበት ክፍል ነው፡፡
ትሮትል ቫልቭ፡-ከነዳጅ መስጫ ፔዳል ጋር የተያያዘ ሆኖ በቬንቹሪ ውስጥ የተቀላቀለው የነዳጅና የአየር ድብልቅ ወደ ሲሊንደር ውስጥ ሲገባ መጠኑን ለመጨመርና ለመቀነስ የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡
የአየር ማጣሪያ(deeprature):-ከካርቡሬተር ከላይኛው ክፍል ላይ በመሆን የተለያዩ ተግባርን ያከናውናል፡፡
--ወደ ሲሊነደር የሚገባውን አየር ያጣራል፡፡
--በካርቡሬተር አናት በኩል የሚነሳውን እሳት ይከላከላል፡፡
--ድምጥን አፍኖ ያስቀራል፡፡
--በናፍጣ ሞተር ላይ ግን ዲፕራተሩ የሚገጠመው በአስገቢው አንገት ላይ ነው፡፡
2ኛ.የናፍጣ ሞተር የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች፡-
ሰልባትዮ(fuel tanker)፡-የሞተር ነዳጅ ማጠራቀሚያ
መጋቢ ፓምፕ(feed pump)፡-ከሳልባትዮ ስቦ ለፊልትሮ አስተላልፎ በዝቅተኛ ሀይል በመግፋት ለኢንጀክሽን ፓምፕ ያስተላልፋል፡፡
ፊልትሮ(fuel filter)፡-በናፍጣ ሞተር ላይ ሁለት አይነት በመሆን ነዳጅን ያጣራሉ፡፡
ኢንጀክሽን ፓምፕ(injection pump)፡-ከፊድ ፓምፕ የመጣውን ነዳጅ በመቀበል በከፍተኛ ግፊት ለኢንጀክተር ኖዝል በማከፋፈል ያስተላልፋል፡፡
ኢንጀክተር ኖዝል(injector nozzle)፡-ከእንጀክሽን ፓምፕ በከፍተኛ ግፊት የመጣውን ነዳጅ በመያዝ ወደ ሲሊንደር ይበትናል፡፡
መላሽ መስመር፡-ከሁሉም ኢነጀክሽን ኖዝል ላይ በመሆን ትርፍ የሆነውን ነዳጅ በማሰባሰብ ወደ ሳልባትዮ ይመልሳል፡፡
ካንዴሊቲ(glow plug)፡-በናፍጣ ሞተር ተጨማሪ ሙቀት በመፍጠር ሞተር ቶሎ እነዲነሳ ያግዛል፡፡
2.የማቀዝቀዣ ክፍሎች
--ሞተር በሁለት አይነት መንገድ ይቀዘቅዛል፡-
1.-በአየር የሚቀዘቅዝ፡-በሲሊንደር አካባቢ ባሉት ፈንሶች ውስጥ አየር በመዘዋወር ሙቀትን ይቀንሳሉ፡፡
2.-በውሃ የሚቀዘቅዝ፡-በሲሊነደር ዙሪየ በሚገኙ የውሃ ቦዮች ውስጥ ውሃ በመንቀሳቀስ በዙሪያው ያለውን ሙቀት ይቀንሳል፡፡በውሃ ከሚቀዘቅዝ ሞተር ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ)ራዲያተር፡-ለሞተር የሚያስፈልገውን ወሃ በመያዝና ከሞተር ሙቆ የተመለሰውን ውሃ በማቀዝቀዝ የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡
ለ)የራዲያተር ክዳን፡-ውሃ ወደ ውጭ እንዳይፈስ እንዲሁም ሞተር በሚሰራበት ጊዜ ውሃ ወደ ውጭ እዳይፈስና ሞተሩ ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ፤ሞተር ከጠፋ በሁዋላ በራዲተር ውስጥ ያለው ውሃ በተን መልክ ስለሚወጣና ራዲያተሩም ባዶ ከሆነ ስለሚጨማደድ ይህን ለመከላከል ቫልቩን በመክፈት ካካባቢው አየርን በማሰገባት ይከላከላል፡፡
ሐ)የውሃ ፓምፕ፡-በራዲያተር ውስጥ ያለውን ውሃ እንዲዘዋወር ያደርጋል፡፡
መ)የውሃ ቦይ፡-በሞተር ውስጥ ውሃ የሚዘዋወርበት ክፍል ነው፡፡
ሠ)ቬንትሌተር(ፈን)፡-ራዲያተርንና የሞተርን አካባቢ ያቀዘቅዛል፡፡
ረ)ቴርሞስታት፡-በውሃ ሙቀት የሚሰራ የውሃ መንገድን መዝጊያና መክፈቻ ቫልቭ ሲሆን የሞተሩ የመስሪያ ሙቀት እሰኪደርስ ድረስ በመዝጋት ውሃ ከሞተር ወደ ራዲያተር እንዳያልፍ ዘግቶ የሚቆይ ነው፡፡
ሸ)ወሳጅ ሆዝ፡-ወሃን ከራዲያተር ወደ ሞተር የሚወስድ፡፡
ቀ)መላሽ ሆዝ፡-የሞቀውን ውሃ ከሞተር ወደ ራዲያተር የሚወስድ ከቀዘቀዘ በሁዋላም ተመልሶ በወሳጅ ሆዝ አማካኝነት ወደ ሞተር ይገባል፡፤
ሞተር ከመጠን በላይ ለምን ይሞቃል?-በቂ ውሃ በራዲያተር ውስጥ ያለመኖር፤
-የራዲያተር መቀደድ፤
-የሌላ የሆነ ራዲያተር ክዳን መጠቀም፤
-በክዳኑ ላይ የሉት ጎሚኖወች መበላት፤
-የቴርሞሰታት መበላሸት ወይም ተቀርቅሮ ሲቀር፤
-የዘይት መወፈር፤መቅጠን፤መቆሸሽ ወ.ዘ.ተ
ማስታወሻ፡-ሞተር በትክክል ስራውን ለመስራት የሚያስፈልገው የሙቀት ደረጃ ከ100% ፐርሰንት ውስጥ 20% ሲሆን ቀሪው ደግሞ በተለያዩ መንገዶች ይወገዳል ማለትም፡
--- 35%-40% --በማቀዝቀዣ ሲሆን፤
--- 35% በጭስ መውጫ አማካኝነት ይወገዳል፤
--- 5% በማለስለሻ ይቀነሳል::
3.የማለስለሻ ክፍሎች
ሞተር ትክክለኛውን ስራ እንዲሰራ በውስጡ ያሉ የሞተሩ ክፍሎች በማለስለሻ አማካኝነት ሰበቃን፤ሙቀትን፤ቆሻሻን፤ድምጽን ይቀንሳሉ፡፡በመሆኑም ሞተር በዘይት ሊለሰልስ ይችላል፡፡ዘይቱም በሞተር ውስጥ በሁለት መንገድ ይረጫል(ይሰራጫል)፡፡
--ኦይል ፓን፡-ከሞተር ከታችኛው ክፍል የሚገኝና ለሞተሩ በቂ ዘይት ያለበትና እነዲሁም በውስጡ የዘይት ማጣሪያ አለው፡፡የዘይቱን መወፈርና መቆሽሹን የምናይበትም መሳሪያ በዚሁ ይገኛል፡፡
-ኦይል ፊልተር፡-ዘይትን አጣርቶ ወደ ኦይል ጋላሪ ይልካል፡፡
-የዘይት መስመር፡- ዘይትን ወደ ሁሉም የሞተር ክፍል የሚያደርስ፡፡
-የመጀመሪየ ማጣሪ(እሰክሪነር)፡-ከኦይል ፓን ውስጥ ይገኛል፡፡
-ዲፕስቲክ(ሊቤሎ)፡-የዘይትን መወፈር እነዲሁመ መቆሸሽ የምናይበት ዘንግ ነው፡፡
-የዘይት ግፊት አመልካች፡-በዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዘይቱ በሞተር ውስጥ በትክክል መዘዋወሩን የሚጠቁም ነው፡፡
ማሰታወሻ፡-ለተሸከርካሪዎች ዘይት ስንቀይር የዘይት ቁጥሮችን በመለየት ነው ማለትም
1----የሞተር ዘይት ቀጥር-40 ቁጥር፤
2----ለዲፈረንሻል 140 ቁጥር፤
3----ለካንቢዮ 90 ቁጥር፤
4----ለፍሬን 30 ቁጥር፤
5----ለመሪ 10 ቁጥር፤
2ኛ)ኤልክትሪክ ክፍሎች
--በተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ የኤሌትሪክ ክፍሎች በ4 ይከፈላሉ፡፡
1)እሳት የማቀጣጠል ዘዴ(እግኒሽን ሲስተም)፡-ከሞተር ሀይል አጋዥ ክፍል ይመደባል፡፡የሚገኘውም በቤንዝን ሞተር ብቻ ነው፡፡
----የእሳት አቀጣጣይ ክፍል በስሩ ብዙ ክፍሎች አሉት እነርሱም፡-
-ኢግኒሽን ኮይል(ቦቢና)፡-ከባትሪ አነስተኛ የኤሌክተሪክ ሀይል ወስዶ ወደ ከፍተኛ ሀይል የሚለውጥ ማለትም ከ6-12 ቮልት ወስዶ 10ሺ-30ሺ ቮልት በማብዛት ለካንዴላ ገመዶች የስተላልፋል፡፡
--ዲስተሪቢውተር(አቫነስ)፡-የተባዛውን ኤሌክተሪክ ሀይል ለካንዴላ ማቅረብ ነው፡፡ሂደቱም በውስጡ በያዛቸው ክፍሎች እነደሚከተለው ይከናወናል፡፡
1.ሮተር(ስፓሱላ)፡-በዲስተሪቢውተር ሻፍት ላይ በመሆን እየተሽከረከረ ከቦቢና ተባዝቶ የመጣውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ለካንዴላ ገመዶች በተወሰነ ጊዜ በየተራ ያከፋፍላል፡፡
2.ኮንታክት ፓይንት(ፑንቲና)፡-በዲሰትሪቢውተር አማካኝነት በመከፈትና በመዘጋት ኢግኒሽን ኮይል ውስጥ የገባው አነስተኛ ሀይል ወደ ከፍተኛ የኤለክትሪክ ሀይል ይቀይራል፡፡
3.ኮንደሴር(ካፓሲተር)፡-የኤሌክትሪክ ሀይልን የሚሰበስብ እና ፑነቲና እንዳይቃጠል ይከላከላል፡፡
4.ካንዴላ፡-በሲሊንደር ውስጥ በታመቀው የአየርና የቤንዝል ቅልቅል ላይ የእሳት ብልጭታ በመፍጠር እንዲቃጠል ያደርጋል፡፡
--ሞተርን የማስነሳት ዘዴ እነደሚከተለው ይከናወናል፡-1-ባትሪ፡-የመጀመሪያ ኤሌክትሪክ ሀይል የሚፈጠርበት ክፍል ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ኬሚካሎችን በመያዝ የኬሚካል ሀይልን ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል ይለውጣል፡፡
2-ቁልፍ(ኩዋድሮ)፡-ሞተርን ለማስነሳት እና ለተለያዩ ክፍሎች ኤሌክትሪክ ማስገኘት፡፡
3-ሞተሪኖ፡-ከባትሪ ሀይል በማግኘት ያገኘውን ኤሌክተሪክ ሀይል ወደ መካኒካል ሀይል በመቀየር ሞተር ለማስነሳት ያገለግላል፡፡
4-ዲናሞ(ጀኔሬተር)፡-ከኮሎ መካኒካል እንቅስቃሴ ወስዶ ወደ ኤሌክተሪካል ሀይል በመለወጥ ባትሪን ይሞላል፡፡
5-ሬጉሌተር፡-የኤሌክትሪክን ሀይል የተመጠነ እኒዲሆን(እንዳይቃጠል)ይቆጣጠራል፡፡
ለኤሌክትሪክ ክፍሎች መደረግ ያለበት ቁጥጥር
-ሁሌም ባትሪ ሲፈታ መጀመሪ ኔጌቲቡን(-)በመቀጠል ፖዘቲቡን፤
-ሁሌም ባትሪ ሲታሰር መጀመሪ ፖዘቲቡን በመቀጠል ነጌቲቡን፤
-ባትሪ መቀመጥ ያለበት ደረቅ ቦታ ላይ ነው፤
-ባትሪ ሳይጠብቅ ሳይላላ መታሰር አለበት ወ.ዘ.ተ
3ኛ)ሀይል አስተላላፊ ክፍሎች
በሞተር ውስጥ የተፈጠረውን እንቅስቃሴ በማስተላለፍ ጎማ ድረስ በማድረስ ተሸከርካሪውን እንዲቀሳቀስ የሚያደርግ ክፍል ነው፡
1-ፍሪሲዮን፡-በሞተርና በካምቢዮ መካከል ይገኛል፡፡ሀይልን ከሞተር ወደ ካመቢዮ ያስተላልፋል፡፡
-የፍሪሲዮን ዋነዋና ክፍሎች፡-ፍላይዊል፤የፍሪሲዮን ሸራ፤የፍሪሲዮን ፔዳል፤ፕላቶ፤ሪሊዝ ፊንገር፤ ሪሊዝ ቤሪንግ፡፡
2-ጊርቦክስ(ካምቢዮ)፡-በማርሽ እጀታ አማካኝነት ነጅ ጥርስ ከተነጅ ጥርስ ጋር በማገናኘት ተሸከርካሪው ጉልበት፤ፍጥነት፤የአቅጣጫ ለውጥ የሚያስችል ክፍል ነው፡፡
-ትንሹ ጥርስ ትልቁን ጥርስ ሲነካከስ ጉልበት ይፈጥራሉ፡፡
-ትልቁን ጥርስ ትንሹ ጥርስ ሲነካከስ ፍጥነት ይፈጥራሉ፡፡
-ሶስቱ ጥርሶች ሲነካከሱ የአቅጣጫ ለውጥን(ተሸከርካሪው ወደ ሁዋላ ሲሄድ)
3.ፕሮፕለር ሻፍት(ትራንስሚሲዮን)፡-ከጊር ቦክስ የተቀበለውን ሀይል ለዲፈረንሻል ያደርሳል፡፡
-ኮሬቼራ(ዩኒበርሳል ጆይንት)፡-ፕሮፔለር ሻፍቱ እንዳይሰበር ይከላከላል፡፡
-ተንሸራታች መገናኛ(ሰልፕ ጆይንት)፡-በጊር ቦክስና በዲፈረንሻል መካከል የሚያጥረውን እርቀትና ቅርበት ያስተካክላል፡፡
4.ዲፈረንሻል፡-ከትራንስሚሲዮን የተቀበለውን ሀይል ለሺሚያስ ያስተላልፋል፡፡
-የጎማ ዙርን በኩርባ መንገድ ላይ ያበላልጣል፡፡
-ሀይልን ለሁለቱም ሽሚያሶች እኩል ያስተላልፋል፤
-ከትራስሚሲዮን የተቀበለውን ክብ ዙር ወደ ቀጥታ የጎማ ዙር ይለውጣል፤
5.አክስል(ሽሚያስ)፡-ከዲፈረንሻል የተቀበለውን ሀይል ለጎማ ያስተላልፋል፡፡
6.ሮዴታ(ኦግዝለሪ)፡-በጭቃ፤በሚያነሸራትት ቦታ ላይ በፊተኛው ጎማ ወይም በሁዋለኛው ጎማ ላይ በመሆን ተጨማሪ ሀይል እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡
---ዘ2--ማርሽ ስንጠቀም ለኖርማል አነዳድ፤
---ዘ4--ከፍተኛ ፍጥነት፤
---L4--ጉልበት፤
---ከH4 ወደ L4 ወይንም ከL4 ወደ H4 ስንቀይር መኪናው ሙሉ በሙሉ ቆሞ መሆን አለበት፡፡
.አውቶማቲክ ካምቢዮ፡-ይህ አይነት ተሸከርካሪ ፍሪሲዮን ፔዳል የሌለው ነው፡፡ -p for parking,-D for driving,-N for neutral,-R for reverse,-L for low drive(more power)
4ኛ)ቻሲስ(መሪ፤ፈሬን፤ጎማ)
1.መሪ፡- መካኒካል መሪ/በሰው ጉልበት የሚሰራ/ እና ፓወር መሪ በሞተር ሀይል የሚሰራ በመባል ይከፈላል፡፡
የመሪ ዋናወና ክፍሎች
-የመሪ መዘወር፡-የሾፌሩ እጅ የሚያርፍበት ክፍል ሆኖ ተሸከርካሪውን ወደ ተፈለገበት አቅጣጫ ለማንቀሳቀስ ይረዳል፡፡
-የመሪ ዘንግ፡-ሀይል ከመሪ መዘውር ወደ መሪ ጥርሳ ጥርስ ሳጥን ያቀብላል፡፡
-የመሪ ጥርስ ሳጥን፡-ከመሪ ዘንግ የሚቀበለውን ሀይል በተወሰነ ሀይል አባዝቶና ወደ ቀጥታ ዙር ለውጦ ለመሪ ጥርስ ዘንግ ያስተላልፋል፡፡
-የመሪ ጥርስ ዘንግ፡-ጎማን እነደአስፈላጊነቱ ወደ ግራና ቀኝ እንዲጠመዘዝ ያደርጋል፡፡
-ቦል ጆይንት፡-በመሪ ክፍሎች ውስጥ ነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
-አሳሪ ዘንግ፡-ሁሉንም የመሪ ክፍሎች ከጎማ ጋር የሚያገናኝ ክፍል ነው፡፡
2.ፍሬን፡-ከመቆጣጠሪያ ክፍሎች አንዱ ነው -የእጅ እና የእግር ፍሬን፡፡
-የእጅ ፍሬን፡-ተሸከርካሪን ለረጅም ጊዜ ለማቆም ይረዳል፡፡-መካኒካል የእጅ ፍሬን እና በታመቀ አየር የሚሰራ በመባል ይከፈላል፡፡
-የእግር ፍሬን፡-ፍጥነትን ለመቀነስና ሙሉ በሙሉ ለማቆም ይረዳል፡፡
-የእግር ፍሬን በሶስት ዘዴ ሊሰራ ይችላል፡፡
.....መካኒካል የእግር ፍሬ፤
.....ሀይድሮሊክ(በዘይት)የሚሰራ የእግር ፍሬ፤
.....ፓወር ብሬክ(በሞተር ሀይል)የሚሰራ የእግር ፍሬ፡፡
**ፍሬናታ፡- የፍሬን ሸራ ከታንቡሩ ጋር ተጣብቆ መቅረት(ፍሬን እንደተያዘ)ፍሬናታ አደረገ ይባላል፡፡
ለፍሬናታ ዋናዋና ምክንያቶች
-የመላሽ እስፕሪነግ መላሸቅ፤
-አጀስትመንት(ሪጅስትሮ)መብዛት፤
-በፍሬን ሲሊነደር ውስጥ በሚፈጠር ዝገትና የጎሚኖዎች መበላት፤
-ማስተር ሲሊነደር ውስጥ ያለው እስፕሪነግ ተጨምቆ መቅረት ናቸው፡፡
-- ብዙ ጊዜ ፍሬን ስንይዝ የመየዝ ብቃቱ ይቀንሳል ለምን?
-የፍሬን ዘይት ማለቅ፤የፍሬን ሸራ ማለቅ፤-የፍሬን ዘይት ማለቅ፤የፍሬን ሸራ ማለቅ፤
-የፍሬን ዘይት ትቦ መቀደድ፤በትቦ ውስጥ አየር መግባት፤
-የጎማ ሊሾ(ጥርስ)ማለቅ ወ.ዘ.ተ
3.ተሸካሚ ክፍሎች:-
የተሸከርካሪ ተሸካሚ ክፍሎች የሚባሉት፡-አስፕሪጎች፤አሞርዛተሮች፤(ሾክአብዞርቨር)ናቸው፡፡አገልግሎታቸውም ..የተሸከርካሪውን አካል ከጎማ ጋር ያገናኛሉ፤በወጣ ገባ መንገድ ላይ ምቾት ይሰጣሉ፤ ጭነትን ይሸከማሉ፡፡
ስፕሪነግ፡-ማሰፈንጠርና መመለስ ባህሪ አላቸው እነርሱም
--ጥቅል ሞላ(ኮይል ስፕሪነግ)፤--ባሊስትራ፤--የብረት ዘንግ(ቶርዥን ባር)፤--የንፋስ(ኤርባግስ)ናቸው፡፡
አሞርዛተር፡-ተሸከርካሪውን ወደታች በዝግታ ከወረደ በሁዋላ በዝግታ እንዲመለስ ያደርጋል፡፡
የተሽከርካሪ ውስጣዊ ክፍሎች
...የሁዋላ ማሳያ መስታውት(ስፖክዮ)
...የአየር ከረጢት
...የደህንነት ቀበቶ
...የወንበር የራስ ድጋፍ፣ወንበር
...የአየር ማቀዝቀዣና ማሞቂያ
...የውስጥ መብራት
...ጥሩንባ፣ነዳጅ መስጫ ፔዳል፤የሞተር ማስነሻ ቁልፍ ወ.ዘ.ተ
Chapter Four
ትራፊክ ምንድን ነው?
ትራፊክ ማለት በመሬት ፣ በአየር እና በባህር ላይ የሚከናወኑ ማናቸውንም የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችን ያጠቃልላል ፡፡
ለአደጋ ተጋላጭነት ጉዳዮች በአጠቃላይ በሦስት ሊመደቡ ይችላሉ ፡፡
1, የአሽከርካሪዎች ባህሪ
2, ራሱ የመኪናው ባህሪ
3, የአከባቢ ምክንያቶች እና የመንገድ ተጠቃሚዎች በአጠቃላይ
የአሽከርካሪዎች ባህሪ
ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፍሰትን ዝቅተኛነት ያውቃሉ እና መመሪያዎች ግን ህጉን የሚያከብሩ ጥቂቶች ናቸው ፡፡ አብዛኞቹ ሾፌሮች እንደየ መንገዳቸው ማሽከርከር እና የተወሰኑትን ለመግለጽ ፍላጎት በሚያሽከረክሩበት ጊዜ አላስፈላጊ ባህሪዎች ከሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
በሚያሽከረክሩበት ጊዜ አሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪ
1.1 የመንገድ ክልል-በአንዱ አሽከርካሪ ጠበኛ ወይም የቁጣ ባህሪ ነው
አውቶሞቢል ወይም ሌላ የሞተር ተሽከርካሪ። እንዲህ ዓይነቱ ባህሪ ሊያካትት ይችላል
ጨዋነት የጎደለው እንቅስቃሴ ፣ የቃል ስድብ ፣ ሆን ተብሎ ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ማሽከርከር ወይም በማስፈራራት ፣ የመንገድ ክልል ሀ ሊሆን ይችላል
ለመኪና አደጋዎች ጥሩ ምክንያት;
ንቁ መሆን ይመከራል
ጠንቃቃ ነጂ
1.2 መድኃኒቶችና አልኮሆል-አልኮሆል እና መኪናዎች ገዳይ ናቸው
ድብልቅ. አልኮል እና አደንዛዥ እጾች ድብርት ናቸው ፡፡ እነሱ ተውጠዋል
ወደ ደም ፍሰት እና በሰውነት ተግባራት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፡፡ ምንም እንኳን
በፍጥነት ተጠምደዋል ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ለክፍለ-ጊዜ በሰውነት ውስጥ ይቀመጣሉ ፡፡
የመድኃኒት እና የአልኮሆል ማስፈራሪያዎች
የመኪናዎን ተሽከርካሪ ለማስተናገድ አስቸጋሪ ያደርገዋል
የእርስዎን አጭር መግለጫ ማግኘት አልቻለም
የትራፊክ ህጎችን እና ደንቦችን አይታዘዙ
በአጠቃላይ ለአብዛኛዎቹ ለትራፊክ አደጋዎች ዋና cau ይጠቀሙ
1.3 በማሽከርከር ረገድ የእድሜ ዘመን የራሱ ሚና ይጫወታል ፡፡ እኛ scruiriae አንድ ይችላሉ
በወጣቶች እና በዕድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነት።
ወጣት አሽከርካሪ (ወጣት አሽከርካሪዎች) ወጣት አሽከርካሪዎች በመነሻ ምክንያቶች ምክንያት በመኪና አደጋ በጣም የተጋለጡ ናቸው ፡፡
ስለ መንዳት ችሎታቸው በልበ ሙሉነት ላይ ናቸው
እነሱ በጣም እረፍት የላቸውም
በቀላሉ ይበሳጫሉ
ብልጥ ሆነው ለመጫወት ይሞክራሉ
ትዕግሥት የለሽ
እነሱ በጣም ተቃዋሚ ናቸው
ዓለም አቀፍ የትራፊክ ምልክቶች
የትራፊክ ምልክቶች ወይም የመንገድ ምልክቶች ለመንገድ ተጠቃሚዎች ድንገተኛ ሁኔታን ለማሳየት በመንገዶች ዳር ላይ የተተከሉ ምልክቶች ናቸው ፡፡
በቀለሞቻቸው እና በመዋቅሮቻቸው እንደየአገሪቱ የትራፊክ ምልክቶች ልዩነት ላይ በመመርኮዝ ፡፡ ኢትዮፓ ሦስቱን በጣም አስፈላጊ የትራፊክ ምልክቶችን ይ encል ፡፡
1. ዋሚንግ ምልክቶች
2. የቁጥጥር ምልክቶች
3 የኢንፌክሽን የፊት ገጽታዎች ወይም የአገልግሎት ምልክቶች
የማሞቅ ምልክቶች-ዋምንግ ምልክቶች ማንኛውንም እምቅ ሀይል ፣
ልዩ ትኩረት የሚፈልግ መሰናክል ወይም ሁኔታ። በአብዛኞቹ ሀገሮች ውስጥ ከነጭ ዳራ እና ወፍራም ቀይ ድንበር ጋር እኩል የሆነ የሶስት ማዕዘን ቅርፅን ይይዛሉ ፡፡ ሆኖም ፣ ሁለቱም የእርስዎ ቀለም
የጀርባው ገጽታ እና የድንበሩ ቀለም እና ውፍረት የተለያዩ የሮማን አውራጃዎች ወደ ሀገር ይለያያሉ።
2. የቁጥጥር ምልክቶች-የሮድ ተጠቃሚዎችን እንዲያስተምር የታሰበ የትራፊክ ምልክቶች ናቸው
ምን ማድረግ አለባቸው ወይም ምን ማድረግ አለባቸው (ወይም ማድረግ የለባቸውም) በተንሸራታች ስር o
ሁኔታዎች. እነዚህ ምልክቶች በሦስት ጉልህ ክፍሎች ይመደባሉ ፡፡
- የመገደብ ምልክቶች-ከነጭ ጋር የክብ ቅርጽን ይያዙ
የቦክስ መሬት onick tick ድንበር እና እነሱ ያሏቸው መረጃዎች
ማስተላለፍ ይፈልጋሉ በጥቁር የተፃፈ ነው ፡፡
- ጠንከር ያሉ ምልክቶች ከሰማያዊ ዳራ እና ለምልክቶች ነጭ ጋር ክብ ቅርፅን ይያዙ ፡፡
- የቅድሚያ ምልክቶች እነዚህ ምልክቶች ለመስጠት መረጃ ያስተላልፋሉ
ሌሎች ሰዎች prionty
3 መረጃ. ያመቻቻል ወይም የአገልግሎት ምልክቶች-በጣም በቀላሉ ሊታተም የሚችል እና በጣም የታተመ ነው
ስለ አንድ ነገር ዓላማ ሰዎችን የሚያሳውቅ ወይም አንድ ነገርን የመጠቀም ችሎታን የሚሰጥ ማስታወሻ ያለው ማስታወሻ በሁለት ተያያዥ ክፍሎች ውስጥ ይመደባል ፡፡
3.1. መረጃ ሰጪ
3.2. አቅጣጫ ጠቋሚዎች
አስደንጋጭ ምልክቶች-ስለማንኛውም መንግስታዊ መረጃ ይሰጣል
ወይም የግል ድርጅቶች በቦርዱ ላይ በተጻፈ ፎም ውስጥ በምስል በኩል ፡፡
አቅጣጫ አመልካቾች ስለ መረጃ ለመስጠት በመጀመሪያ ደረጃ ጥቅም ላይ ውሏል
የሾፌሩ ወይም የመድረሻ ቦታው።
የትራፊክ መብራቶች በትውልድ በሁለት ይከፈላሉ: -
ለተሽከርካሪዎች መደበኛ የትራፊክ መብራቶች
የእግረኛ መሻገሪያ መብራቶች
ለተሽከርካሪዎች መደበኛ የትራፊክ መብራቶች በአራት የመለኪያ ደረጃዎች ያልፋሉ
1. ቀይ
2. ቀይ እና ቢጫ በአንድ ጊዜ
3. አረንጓዴ
4. ቢጫ
ቀይ (ማቆሚያ)-መብራቱ ለሚገጥሟቸው ተሽከርካሪዎች ለማቆም የቀይ ዕይታ ያመለክታል ፡፡
ቀይ እና ቢጫ በአንድ ጊዜ-ጥንቃቄን ያሳያል ፣ ወይም ምክንያቱም
መብራቶች ወደ አረንጓዴ ሊለወጡ ነው ወይም መብራቶች ሊበሩ ስለሆነ
እርስዎ ባሉበት ክልል ላይ በመመርኮዝ ቀይ ፡፡
አረንጓዴ: አረንጓዴ መብራት መቀጠል አለበት ፣ (ይህን ለማድረግ ደህና ከሆነ)።
ቢጫ-ቢጫ መብራቱ ከአረንጓዴው በኋላ ሲመጣ ይጠቁማል
እነዚያን ያልፉትን እና ቀድሞውኑ በመስቀል ላይ ናቸው
ለማፋጠን እና ለማለፍ ክፍፍል መንገድ ፣ እና እነዚያ
መብራታቸውን እየተመለከተ መኪናቸውን ለማቆም ወደ ብርሃኑ መቅረብ ፡፡
የእግረኞች መሻገሪያ መብራቶች የትራፊክ መብራቶች መቼ መደረግ እንዳለባቸው ትራፊክ ያስተምራሉ
ሲቆሙ እና እግረኞች ሲሻገሩ ፡፡
ቀይ-ቀይ አኃዝ ያሳያል ፣ አይለፉ ማለት ነው ፡፡
አረንጓዴ: - ትራፊኩ መቆሙን በጥንቃቄ ያረጋግጡ ፡፡
የተቆራረጡ መብራቶችን በመጠቀም መወሰድ አስፈላጊ የሆነውን ጥንቃቄ
ቀይ-ብልጭ ድርግም ብሎ ወደ ቀይ መብራት የሚደርስ ተሽከርካሪ በመቆም ግራ እና ቀኝ መመርመር አለበት
ከብርሃን ፊት ለፊት እና በጥንቃቄ ያስተላልፉ. በማሽከርከር ጊዜ በምሽት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡
ጥሩው ብልጭ ድርግም ብሎ ወደ ቢጫ መብራት የሚደርስ ተሽከርካሪ ፍጥነት መቀነስ ፣ ግራ ቀኙን ማረጋገጥ እና ማለፍ አለበት ፡፡
ባለ ሁለት ትራፊክ መብራቶች
እኛ ከላይ የትራፊክ ምልክቶች ጋር ሁለት የትራፊክ መብራቶችን እናገኛለን ፡፡ አረንጓዴ መብራት ከፊት ለፊቱ ለሚሄዱ እና ወደ ቀኝ ለሚመሩት በርቷል ፡፡ ቀይ መብራቶች
ወደ ግራ ለሚዞሩ በርቷል.የምን እንደሆነ የሚለውን ጥቅስ አሳዩን
ብለን ጠቅሰናል ፡፡
ዓለም አቀፍ የመንገድ መስመሮች
በተሽከርካሪ ጎዳናዎች ላይ ለአሽከርካሪዎች እና ለእግረኞች መመሪያ እና መረጃ ለመስጠት ያገለግላሉ
የመንገድ መስመሮች በአጠቃላይ በሁለት ይከፈላሉ
1. የዜብራ መሻገሪያ መስመሮች-በብዙ ቦታዎች ጥቅም ላይ የሚውለው የእግረኛ መሻገሪያ ዓይነት
በዓለም ዙሪያ. የእሱ መለያ ባህሪ ተለዋጭ ጨለማን ያካትታል
እና በመንገድ ወለል ላይ የብርሃን ጭረቶች አንድ የሜዳ አህያ መሻገሪያ ዓይነተኛ ይሰጣል
ለእግረኞች የመንገድ ተጨማሪ መብቶች ፡፡ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት
እግረኞች መንገዳቸው ቢሆንም እንኳን በዜብራ ማቋረጫ ላይ ከወደቁ ፡፡
2. የሮድ አቅጣጫ ማቋረጫ መስመሮች (ሹፌር ለመንጃ)
የተሰበረው መስመር ሁለቱን መስመሮች በሚለያይበት በሁለት መስመር መንገድ 2.1
- መስመሩን ማቋረጥ።
- የ U ተራ ያድርጉ።
- የሚከለክለው ምልክት ከሌለ ወደ ግራው መዞር ይፈቀዳል
ግራ እና ዩ መዞር.
- የትራፊክ ሁኔታ ተስማሚ ከሆነ አሽከርካሪዎች ሊያልፉ እንደሚችሉ ያሳውቃል
የፊት ተሽከርካሪውን ወይም መስመሮቹን ይቀይሩ ፡፡
ጠንከር ያለ መስመር ሁለቱን መንገዶች በሚለያይበት በሁለት መስመር መንገድ 2.2 ፡፡
- ወደ ግራ መዞር።
- መስመሮቹን ማቋረጥ እና የፊት ተሽከርካሪውን ማለፍ ..
- ዩ ተራ ማድረግ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነው
የተሰነጠቀ መስመር እና ለመለያየት ጠንካራ መስመር ባለበት በሁለት መስመር መንገድ 2.3
ሁለቱ መንገዶች
ሀ በጠንካራ መስመር መስመሩ ላይ ጠልቆ -
- የ U መታጠፍ ያድርጉ
- ወደ ግራ መዞር
- መስመሮቹን ማቋረጥ እና የፊት ተሽከርካሪውን ማለፍ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነው
ቢ በተሰበረው መስመር መስመር ላይ መንዳት-
- መስመሮቹን በማቋረጥ ዩ መዞሩ የተከለከለ ነው ፡፡
- ወደ ግራ መዞር
- የለውጡን የፊት መስመር ተሽከርካሪ ማለፍ ይፈቀዳል ፡፡
2.4 በጠንካራ የእግረኛ መስመር በሚለየው በሁለት መስመር መንገድ
- ኡስታን ኡ ቱ ማድረግ የተከለከለ ነው ፡፡
የእግረኞችን መስመር በማቋረጥ ወደ ግራ መዞር አይቻልም።
- የእግረኞችን መስመር በማቋረጥ ተሽከርካሪን ማለፍ አይቻልም ፡፡
የእግረኛ መስመሩን ሳይነካ የ U መዞር ይቻላል
2.5 በተሰበረ መስመር ሲለያይ አንድ ሌን መንገድ።
- በመስመሩ በኩል ማለፍ እና ከፊት ለፊት ያለውን ተሽከርካሪ ማለፍ ይቻላል
ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ለመዞር ይፈቀዳል
የ U ማዞር የተከለከለ ነው
2.6 ማቋረጫ መንገድ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ተሽከርካሪ-
በ 50 ሜትር ክልል ውስጥ አንድ ተሽከርካሪ መስመሩን ሊቀይር ይችላል
በተሰበረ መስመር ውስጥ ሆነው ሌሎች መኪኖችን ያስተላልፉ ፡፡
በ ውስጥ መስመሩን መለወጥ ወይም አቅጣጫውን መቀየር የተከለከለ ነው
30 ሚ.ሜትር በተጣራ መስመር ውስጥ መሆን።
ወደ ላይ ሂድ





