Total Pageviews

የማሽከርከር ህግ

የማሽከርከር ህግ 

የማሽከርከር ህጎች ፦ የአንድ ሀገር የማሽከርከር ህግ ዋና ዓላማ ለአሽከርካሪወች እንደ መሆኑ መጠን አሽከርካሪወች የሚከተሉትን 5 የማሽከርከር ህግ ሀሳቦችን መማርና ማወቅ አለባችው።

የማሽከርከር ህግ ሀሳቦች

  1. ዓለም አቀፍ የትራፊክ ቋንቋወች ህግ
  2. የትራንስፖርት ህጎች እና ደንቦች
  3. የፍጥነት ወሰን
  4. የማሽከርከሪያ ርቀት ወሰን
  5. የአሽከርካሪዎች የእጅ ምልክቶች ናቸው።

ዓለም አቀፍ የትራፊክ ቋንቋወች ህግ

Ω ትራፊክ ማለት ምን ማለት ነው?

ትራፊክ ማለት፡- ማንኛውም ተንቀሳቃሽ /ተላላፊ/ የሆነ ነገር ሁሉ ትራፊክ ተብሎ ይጠራል፡፡

ትራፊክ በሚንቀሳቀሱበት /በሚተላለፋበት/ ቦታ በሶስት ይከፈላሉ እነርሱም፡-

1. በየብስ የሚንቀሳቀሱ

2. በባህር /በውሃ/ የሚንቀሳቀሱ

3. በየአር የሚንቀሳቀሱ ተብለው ይጠራሉ፡፡

a) በየብስ ላይ ከሚንቀሳቀሱ ትራፊኮች ውስጥ፡- ሰው፣ ተሽከርካሪዎች፣እንስሳት….

b) በባህር /በውሃ/ ላይ ከሚንቀሳቀሱ ትራፊኮች ውስጥ፡- መረከቦች፣ ጀልባዎች …..

c) በየአር ላይ ከሚንቀሳቀሱ ትራፊኮች ውስጥ አውሮኘላኖች፣ መንኮራኩሮች፣አእዋፋት፣በራሪአካላት ወዘተ.. ሲሆኑ

▶ እነዚህ ተንቀሳቃሽ አካላት ያለምንም አደጋ እንቀስቃሴያቸውን በሰላም እንዲያከናውኑ የአሽከርካሪዎች አንዱ ዋና ሀላፊነት የትራፊክ አደጋ መንስኤወችን ጠንቅቆ መለየት/ማወቅ/ ሲሆን

▶ በዋናነት አሽከርካሪዎችን የሚመለከተው የትራፊክ አደጋ የየብስ ትራፊክ አደጋ ሲሆን

▶ በየብስ ላይ የትራፊክ አደጋ መስኤዎች በሶስት ይከፈላሉ
እነሱም፡-

1. የአሽከርካሪው ባህሪይ /90%/

2. የተሽከርካሪው የብልሽት ባህሪ /8%/

3. የአካባቢው ባህሪይ /2%/ ናቸዉ።

▶ስለሆነም ▸ በ አሽከርካሪዎች የባህሪ ፤ የብቃት እና የእውቀት ጉድለት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ አሽከርካሪዎች ከታች ከመግቢያ 2 ጀምሮ ያለውን ጨምሮ ሁሉንም ከታች በ ቻፕተር (በክፍል) የተከፋፈሉ የማሽከርከር ህግ ሀሳቦችን በሚገባ ማወቅ አለባቸው።

ዓለም አቀፍ የትራፊክ ቋንቋወች

የማሽከርከር ህጎች ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ሲሆን ከነዚህም አንዱ ዓለም አቀፍ የትራፊክ ቋንቋወች ደንብ ይባላል ።
እነዚህም ዓለም አቀፍ የትራፊክ ቋንቋወች እንደሚከተሉት ናቸው ።

  1. አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች
  2. አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች
  3. አለም አቀፍ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች
  4. አለም አቀፍ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች ናቸው።

አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች

አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ የመንገድ ዳር ምልክቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ እና ተቀራራቢ ትርጓሜ እንዲኖራቸው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1968 ዓ.ም ኦስትሪያ ቬና ላይ በተደረገው የስምምነት ጉባኤ መሠረት በአለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይነት እንዲኖራቸው ተደርገዋል።

▶ስለዚህም የመንገድ ዳር ምልክቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ናቸው።

▶ በዚህም መሠረት ምልክቶች በሁሉም አገሮች አንድ ዓይነት መግባቢያ የትራፊክ ቋንቋ በመሆን ማንኛውም ዜጋ የትም ሀገር ሲያሽከረክር ግራ እንዳይጋባ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ሰላማዊነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

❖ አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በዋናነት በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡

እነሱም፡-

3ቱ የመንገድ ዳር ምልክቶች

1- የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች።

2- የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች።

3- መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ናቸው፡፡ 

የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ የመንገዶችን ቅደመ ሁኔታ ወይም አደገኝነት አስቀድመው ይገልፃሉ።

▶ ከፊት ለፊታችን የምናገኘው መንገድ ለማሽከርከር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ያሳያሉ።

▶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ካላደረግንም ለከፍተኛ ችግር ሊዳርጉን የሚችሉ የተለያዩ የመንገድ ሁኔታዎችን ቀድመው የሚነግሩን ወይም የሚያሳስቡን ናቸው።

▶ ማንኛውም አሽከርካሪ ለየሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች በምላሹ አስፈላጊውን ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ማሽከርከር ይገባዋል፡፡

❖ የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች አለም አቀፍ መለያ


1. ቅርፃቸው፡- ሦስት ማዕዘን ነው ።

2. ጠርዛቸው ወይም ክፈፋቸው፡- በቀይ ቀለም የተከበበ ነው ።

3. መደባቸው ወይም ውስጡ፡- ነጭ ነው ።

4. መልዕክት የሚያስተላልፉት ፡- ማለትም መልዕክት የሚያስተላልፉበት የውስጥ ምስል በጥቁር ቀለም የተሰራ ስዕል ወይም ቀስት ነው ።

5. የሚያስተላልፉት ትዕዛዝ (መልዕክት)፡- ˝… ተጠንቅቀህ አሽከርክር˝ የሚል ነው፡፡



የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች ከስማቸው መጠሪያ መረዳት እንደሚቻለው አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት አስፈላጊውን ትዕዛዝ አክብረው እንዲያሽከረክሩ የመቆጣጠር ስራን የሚያከናውኑ ሲሆኑ

▶ እነዚህን የመንገድ ዳር ምልክቶች በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ መጣስ ወይም አለማክበር በትራንስፖርት ደንብ መተላለፍ ለቅጣት ይዳርጋል፡፡

❖ እነዚህ የሚቆጣጠሩ የመንገድ ዳር ምልክቶች በዋናነት በሦስት ንዑስ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡

በሚቆጣጠሩ ስር የሚገኙ 3ቱ የመንገድ ዳር ምልክቶች ⤵

1. የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች

2. የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች

3. ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች ይባላሉ ።

(1) የሚከለክሉ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ 1.2.2 የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ 1.2.3 ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች

Part 1.3 መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች

መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች ከስማቸው መጠሪያ መረዳት እንደሚቻለው የተለያዩ መረጃዎችን

▶ አስፈላጊ አገልግሎት ማግኛ ቦታዎችን እና

▶ የመንገዶችን አቅጥጫ እና ዘላቂ መሆን አለመሆን ለአሽከርካሪዎች በጽሁፍ በምስል በቀሰት ይገልፃሉ።

አለም አቀፍ መለያቸው እንደሚከተለው ነው ⤵

1. ቅርፃቸው፡- አራት የማዕዘን ነው ።

2. መደባቸው፡- ሰማያዊ ቀለም ነው ።

2. ጠርዛቸው (ክፈፋቸው) ፡- ሰማያዊ ቀለም ነው ።

3. መልዕክት የሚያስተላልፉት፡- በነጭ ወይም በጥቁር ቀለም በተሰራ ስዕል፣ ቀስት፣ ፅሁፍ ነው ።

4. የሚያስተላልፉት የመረጃ መልዕክት፡- ˝ . . .አለ˝ ˝ . .ይገኛል ˝ የሚል ይሆናል፡፡

❖ እነዚህ የመንገድ ዳር ምልክቶች በዋናነት በ 2 ንዑስ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡

እነሱም፡-

1- በራሱ መረጃ ሰጪ እና

2- አቅጣጫ አመልካች ናቸው፡፡

▶ 1.3.1 በራሱ መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች

▶ 1.3.2 አቅጣጫን አመልካች የመንገድ ዳር ምልክቶች


Chapter 2 የመንገድ ላይ መስመሮች

Part 2.0 የመንገድ ላይ መስመሮች ተግባር

የመንገድ ላይ መስመሮች ተግባር

▶ የት ቦታ ላይ ወደ ሌላ አቅጣጫ ገብተን መቅደም እንደምንችል ወይም እንደማንችል ይጠቁማሉ

▶ ለመታጠፍ እና ዞሮ ለመመለሰ የምንጠቀምበትን ረድፍ ያመለክታሉ

▶ በትራፊክ መብራት አካባቢ የምንቆምበትን ሥፍራ ያመለክታሉ

▶ የመንገድ መሐል እና ጠርዝን ያመለክታሉ

▶ ለእግረኞች መተላለፊያ እንዲሆኑ የተዘጋጁ እና የተከለሉ ሥፍራዎችን ያመለክታሉ

▶ አንድን መንገድ በሁለት ነጠላ መንገዶች ይከፍላሉ

▶ ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድን በረድፍ ይከፍላሉ

▶ የመንገድ ዳር ምልክቶችን መትከል አስቸጋሪ በሆነበት መንገድ ላይ ምልክቶችን ተክተው ይሠራሉ

የመንገድ ላይ መስመር አይነቶች

1- በመንገዱ አግድመት የሚሠመር (የዜብራ መስመር) እና

2- በመንገዱ አቅጣጫ የሚሠማሩ (የተሽከርካሪ መስመሮች) ናቸው።

ሌሎች የመንገድ ላይ ቅቦች

1- በቢጫ ቀለም የተሠመረ መስመር ቅብ

2- ማቆሚያ መስመር ቅብ

3- የማስተላለፊያ መስመር ቅብ

4- አቅጣጫን አመልካች ቅብ እና

5- ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ ናቸው።

Part 2.1 በመንገድ አግድመት የሚሰመር /የዜብራ የእግረኛ/ መስመር

2.1 በመንገድ አግድመት የሚሰመር የዜብራ የእግረኛ መስመር

የዜብራ ወይም የእግረኛ ማቋረጫ መስመር ፦

▶ እግረኞች በአጭር ርቀት ውስጥ መንገድ ማቋረጥ እንዲችሉ የሚሰመር መስመር ነው።

▶ አሽከርካሪዎች በዚህ መስመር ውሰጥ በመንቀሳቀስ ላይ ላሉ እግረኞች ምን ጊዜም ቅድሚያ መስጠት አለባቸው፡፡

▶ እነዚህ ለእግረኛ አገልግሎት የሚውሉ የመንገድ ላይ መስመሮች የሚሰመሩትም በመንገዱ አግድመት ሲሆን

▶ማንኛውም አሽከርካሪም በእነዚህ እግረኛ መስመሮች (ዜብራ) ላይ የተሽከርካሪን ፍጥነት መቀነስና ለእግረኞችም ቅድሚያ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

Part 2.2 በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ የረድፍ (የተሽከርካሪ) መስመሮች

2.2 በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ የረድፍ (የተሽከርካሪ) መስመሮች

የረድፍ መስመሮች ፡ - ለተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ረድፋቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ የሚረዳ ሲሆን ⤵
ጥቅሙም ▸ አንድን መንገድ በነጭ መስመር ለሁለት መንገድ በመክፈል ከዚያም ⤵
▶ ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ በማድረግ እና
▶ ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ በማድረግ
ከአንድ በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለማስተላለፍ እንዲቻል በመንገድ ላይ የሚሰመር ነው፡፡

2.2.1 በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ የረድፍ (የተሽከርካሪ) የባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ መስመሮች

እነዚህ የመንገድ ላይ መስመሮች ለተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን የሚሰመሩትም በመንገዱ አቅጣጫ ነው፡፡

እነሱም ፦

1- ድፍን (ያልተቆራረጠ) መስመር /______________ /

2- የተቆራረጠ መስመር /_ _ _ _ _ _ /

3- የተቆራረጠ እና ያልተቆራረጠ (ድፍን) መስመር
/_ _ _ _ _ _ _ /
/__________ / እና

4- የደሴት መስመር በቀለም መስመር የተሠራ የደሴት መስመር ናቸው ።




ነገር ግን ▸ እንደ መንገዱ እና እንደ ትራፊኩ ሁኔታ ድፍ መስመሮቹን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ ላይ የግራ ረድፉን ይዞ መቅደም ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ፦ አንድ መንገድ በተቆራረጠ እና ባልተቆራረጠ መስመር ለሁለት ሲከፈል፡-

➡ ባልተቆራረጠው (ድፍን) መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ ▸ መስመሩን ረግጦ
▶ መታጠፍ አይችልም፣
▶ ዞሮ መመለስ አይችልም
▶ መደረብ ወይም መቅደም አይችልም
ነገር-ግን ▸ እንደ አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ጥንቃቄን በማድረግ መስመሩን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ ላይ የግራ ረድፉን ይዞ መቅደም (መደረብ) ይቻላል፡፡

➡ በተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው ተሽከርካሪ ▸ የሁለቱንም መስመሮች ረግጦ ⤵

▶ መታጠፍ ይቻላል

▶ ዞሮ መመለስ ይቻላል

▶ መደረብ ወይም መቅደም ይቻላል ፡፡




2.2.2 የባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ መስመር

እነዚህ የመንገድ ላይ መስመሮች ለተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን የሚሰመሩትም በመንገዱ አቅጣጫ ነው፡፡

እነሱም ፦

1- ድፍን (ያልተቆራረጠ) መስመር

2- የተቆራረጠ መስመር ናቸው።

1- አንድ ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ መስመር ሲከፈል ፦

ማንኛውም አሽከርካሪ በራሱ ረድፍ ውስጥ በማሽከርከር የተቆራረጠ መስመር ረግጦ ወይም አልፎ ⤵
▶ ፍጥነት ለመጨመር፣ ለመቀነስ ይችላል
▶ ለመታጠፍ ይችላል
▶ መቅደም ወይም መደረብ ይችላል
ነገር-ግን - መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ በመሆኑ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው፡፡

2- አንድ ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ ባልተቆራረጠ (ድፍን) መስመር ሲከፈል ፦

ያልተቆራረጠውን ድፍን ነጭ መስመር ረግጦ ፡-

▶ መታጠፍ አይቻልም

▶ ዞሮ መመለስ አይቻልም

▶ መደረብ (መቅደም) አይቻልም ።

3- አንድ ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ በቀለም በተሰራ ደሴት ሲከፈል ፦

ከላይ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው
▶ መስመር አንድ ላይ የሚገኙ አሽከርካዎች ፊት ለፊት ብቻ የመሄድ እድል (ፈቃድ) ያላቸው።
▶ ሰለዚህ በመስመር ሁለት መንገድ ውስጥ ገብተው (ይዘው) ማሽከርከር አይፈቀድላቸውም፡፡
▶ መስመር ሁለቶች ግን የመስመር አንድንም ሆነ የመስመር ሁለትን መንገድ ተከትለው ማሽከርከር ይችላሉ፡፡

Part 2.3 የመንገድ ላይ ቅቦች

2.3. የመንገድ ላይ ቅቦች

2.3.1. የማቆሚያ ስፍራ ቅብ

2.3.2. የመተላለፊያ መስመር ቅብ

2.3.3. አቅጣጫን አመላካች ቅብ

2.3.4. ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ ናቸው።

2.3.1 የማቆሚያ ስፍራ ቅብ

▶ አሽከርካሪዎች በምልክቱ ውስጥ ለማቆሚያ በተዘጋጀው ሥፍራ ላይ ብቻ ማቆም አለባቸው።
▶ በአራት አቅጣጫም ሆነ በማንኛውም መገናኛ መንገድ ላይ መንገዶች ከሚገናኙበት ማዕዘን ወይም ኩርባ ከ 12 ሜትር ባነሰ ርቀት ውስጥ አቁሞ መሔድ ክልክል ነው፡፡

ማንኛውም አሽከርካሪ በእነዚህ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራዎች ተሽከርካሪውን ማቆም ከፈለጉ የተሰመረውን መስመር ሳይረግጥ ወይም ሳይነካ መሆን ይኖርበታል፡፡

በመንገዱ ቀኝ እና ዳርቻ መኪናን ለማቆሚያ አመቺ በሚሆን ዓይነት በመንገዶች ባለሥልጣን ለአንድ መኪና ስፋቱም ሆነ ቁመቱ ይበቃል ተብሎ በተቀባ ክልል ውስጥ አለአግባብ አቁሞ መሔድ ክልክል ነው፡፡

2.3.2. የመተላለፊያ መስመር ቅብ

▶ የቀለም ነጠብጣብ ባላቸው ክልሎች ውስጥ ለማቆም ሆነ ማሽከርከር ክልክል ነው፡፡

2.3.3. አቅጣጫን አመላካች ቅብ

▶ እነዚህ ምልክቶች በመታጠፊያ ወይም አደገኛ ኩርባዎች እና መንገዱ ፊት ለፊት በማይቀጥልበት መገናኛ ስፍራ ላይ አሽከርካሪዎች የመንገዱን ክልል አልፈው እንዳይወጡ የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች ናቸው፡፡
▶ ምልክቶቹ ጥቁርና ነጭ ቀለም በተቀቡ ትክል ድንጋዮች የመታጠፊያ፣ የገደላማ ወይም የድልድይ አካባቢ ተጀምሮ እስከሚያልቅበት ቦታ ድረስ ተተክለው የሚታዩ ሲሆን በተጨማሪም መንገዱ ፊት ለፊት በማይቀጥልበት እና አደገኛ መታጠፊያ ስፍራዎች ላይ አግድም የተተከሉ ሰሌዳዎች በአንፀባራቂ ነጭ እና ጥቁር ቀስት የመንገዱን አቅጣጫ ያመለክታሉ፡፡

▶ ወደ ግራ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ መንገድ ላይ የሚተከል ማስጠንቀቂያ ምልክት

▶ ለፊት ለፊት የሚቀጥል መንገድ ያለመኖሩን የሚያስጠነቅቅ የቀስት እና የትክል ድንጋይ አንፀባራቂ ምልክት

▶ ወደ ቀኝ የሚታጠፍ አደገኛ መጠምዘዣ መንገድ ላይ የሚተከል የማስጠንቀቂያ አንፀባራቂ ምልክት

2.3.4- ቅድሚያ ስጥ የሚል ቅብ


Chapter 3 የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች

Part 3.0 የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች ዓይነቶች

አለም አቀፍ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች ብዙውን ጊዜ የሚገኙት በመስቀለኛና በመገናኛ መንገዶች ላይ ሲሆን ተላላፊዎች (ተሽከርካሪዎችና እግረኞች) ተራቸውን ጠብቀው በስርዓት እንዲተላለፉ በማድረግ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ፡፡

አለም አቀፍ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች በሚሰጡት አገልግሎት በሁለት ይከፈላሉ፡፡

እነሱም፡-

1- የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራቶች እና

2- የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች ይባላሉ፡፡

Part 3.1 የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት

3.1- የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት

እነዚህ መብራቶች እግረኞች በቀላሉ ከተሽከርካሪ ጋር ሳይገናኙ ሳይገፉና ለአደጋ ሳይጋለጡ መንገዱን እንዲያቋርጡ ከማድረጋቸውም ባሻገር ለተሽከርካሪዎችም እግረኞችን በማስቆም በቀላሉ እንዲያሽከረክሩ የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡

▶ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እግረኞች መንገድ እንዳ ያቋርጡ ወይም እንዲቆሙ እንዲሁም
▶ ተሽከርካሪዎች በሚቆሙበት ጊዜ መንገድ ማቋረጥ እንዲችሉ
የተለያየ ቀለም ባላቸው መብራቶች መልዕክት የሚያስተላልፍ የመቆጣጠሪያ መሣሪያ ሲሆን በውስጡም ከተሽከርካሪ መተላለፊያ መብራት መለየት እንዲቻል የእግረኛ ምስል ይኖራቸዋል፡፡

ለእግረኛ አገልግሎት የሚውሉት እነዚህ የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራቶች በመብራት አቀማመጣቸው ከላይ (መጀመሪያ) ቀይና ከታች (ቀጥሎ) አረንጓዴ ቀለም ያላቸው ሲሆን በአበራር ቅደም ተከተላቸው ደግሞ ቀይ ➡ አረንጓዴ ወይም አረንጓዴ ➡ ቀይ ቀለም ይኖራቸዋል፡፡

ትርጉማቸውም፡-

1.1- ቀይ የእግረኛ ምስል:- ያለበት የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ እግረኞች ከተሽከርካሪ መተላለፊያ ውጪ በመሆን ለእግረኞች በተከለለ ስፍራ ላይ አረንጓዴ የእግረኛ ማስተላለፉያ መብራት እስኪበራ ይቆማሉ (ይቆያሉ)፡፡

2.2- አረንጓዴ የእግረኛ ምስል:- ያለበት የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ እግረኞች በተዘጋጀላቸው የእግረኛ መተላለፊያ ወይም ማቋረጫ (ዜብራ) ብቻ ተጠቅመው መንገዱን ያቋርጣሉ፡፡

ባጭሩ

1. ቀይ የእግረኛ ምስል ያለበት መብራት ሲበራ :- እግረኞች መንገድ እንዲያቋርጡ አይፍቀድላቸውም

2. አረንጓዴ የእግረኛ ምስል ያለበት መብራት ሲበራ :- እግረኞች ለመተላለፊያ በተሰመረ መስመር ውስጥ ብቻ እንዲያቋርጡ ይፈቀድላቸዋል፡፡

Part 3.2 የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች

3.2- የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች

ለተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውሉት እነዚህ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች፡- ቀይ፤ ቢጫና አረንጓዴ ቀለማት ሲኖራቸው የመብራት አቀማመጣቸውም ከላይ ወደታች ቀይ ➡ ቢጫና ➡ አረንጓዴ ቀለም ሊሆን ይችላል፡፡

የአበራር ቅደም ተከተላቸው

የአበራር ቅደም ተከተላቸውም ስንመለከት ከታች እንደተዘረዘረው አራት አይነት እድሎች ይኖሩታል፡፡

እነሱም፡-

1- ቀይ ➡ ቀይናቢጫ ➡ አረንጓዴ ➡ ቢጫ ወይም

2- ቀይናቢጫ ➡ አረንጓዴ ➡ ቢጫ ➡ ቀይ ወይም

3- አረንጓዴ ➡ ቢጫ ➡ ቀይ ➡ ቀይናቢጫ ወይም

4- ቢጫ ➡ ቀይ ➡ ቀይናቢጫ ➡ አረንጓዴ ይሆናሉ

ትእዛዛቸውም ፡-

1- ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ፦
▶ቀይ በሚበራበት አቅጣጫ ያሉ ተሽከርካሪዎች ለእግረኛ መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ መቆም አለባቸው፡፡
▶ ቀይ መብራት እየበራ አልፎ መሄድ በህግ ከማስጠየቁም በተጨማሪ ለአደጋ ያጋልጣል፡፡

2- ቀይ እና ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች በአንድነት ሲበሩ ፡-
▶ በቀይ መብራት ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡
▶ ወደ መገናኛው መንገድ በመድረስ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ከእግረኛ መተላለፊያ መስመር ሳያልፉ በመቆም ለመሄድ ይዘጋጃሉ፡፡

3- አረንጓዴ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ፡- ይህ መብራት ከ ቀይ እና ቢጫ መብራት ቀጥሎ ሲበራ
▶ አሽከርካሪዎች ቀድመው ወደ መረጡት አቅጣጫ ማለፍ አለባቸው
▶ በዚህም ወቅት ዘግይተው በእግረኛ መተላለፊያ ውስጥ በማለፍ ላይ ላሉ እግረኞች ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4- ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ብቻውን ሲበራ ፡- ይህ መብራት ከ አረንጓዴ መብራት ቀጥሎ ሲበራ
▶ ወደ መገናኛው መንገድ በመምጣት ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ለእግረኛ መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፉ ይቆማሉ፣
▶ ወደ መገናኛው መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካሪዎች በፍጥነት መንገዱን ለቀው መውጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባጭሩ ፡-

1- ቀይ ➡ (ቁም)! ማለት ነው።

2- ቀይና ቢጫ ➡ (ለጉዞ ተዘጋጅ)! ማለት ነው።

3- አረንጓዴ ➡ (ሂድ (እለፍ))! ማለት ነው።

4- ቢጫ ➡ መስቀለኛ ውስጥ ለገባ በፍጥነት መስቀለኛውን መንገድ ተሻገር ወይም ለቀህ ውጣ ማለት ሲሆን መስቀለኛ ውስጥ ላልገባ (ለማቆም ተዘጋጅ)! ማለት ነው።

ስለዚህ ▸ ቀዩ (¤) የተሽከርካሪ(🚐) ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ➡ የእግረኛ(🚶) መብራት አረንጓዴው (🚶) ስለሚበራ አሽከርካሪዎች ዜብራውን ሳያልፍ መቆም አለባቸው ነገር ግን ቀጥሎ ➡ ቀይ እና ቢጫ የተሽከርካሪ(🚐) ማስተላለፊያ መብራት ይበራል እናም አሽከርካሪዎች ለመሄድ እንዲዘጋጁ የሚያደረግ በመሆኑ እግረኞች ማለፍ የለባቸውም ምክንያቱም ቀጥሎ ➡ አረንጓዴው (¤) የተሽከርካሪ(🚐) የትራፊክ መብራት ስለሚበራ እና ➡ የእግረኛ (🚶) መብራት ቀዩ (•) ስለሚበራ እግረኞች መንገዱ ዳር ላይ መቆም አለባቸው ።

ተጨማሪ ሌሎች (ልዩ) የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች፡-

ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት እና ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ናቸው።

መልዕክታቸው እና ትዕዛዛቸው ፡-

2- ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ ፦
▶ ማንኛውም አሽከርካሪ በመንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ እንዳለ ተገንዝቦ ➡ ለእግረኛ መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ ➡ በመቆም አደጋ የማያስከትል መሆኑን ሳያረጋግጥ እንዲያልፍ አይፈቀድለትም፡፡
▶ ይህ መብራት በባቡር ሐዲድ ማቋረጫ ባቡር በሚያልፍ ጊዜ እና በመገናኛ ሥፍራዎች ላይ የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ ወይም ሌላ አደገኛ ሁኔታ ሲኖር የሚበራ መብራት ነው፡፡
▶ አንዳንዴም በቀን የሚበራ ሲሆን ይህ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ የደረሰ ማንኛውም አሽከርካሪ ለእግረኛ ማቋረጫ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ በመቆም ግራና ቀኙን ሳይመለከት ና ለተላላፊ ቅድሚያ ሳይሰጥ ማለፍ የተከለከለ ነው ።
▶ በመሆኑም የተላለፈውን መልዕክት ያለጥንቃቄ መንገድ ለማቋረጥ መሞከር ለአሰቃቂ አደጋ ከማጋለጡ በተጨማሪ በሕግ ያስቀጣል፡፡

2- ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ፡- ▶ አሽከርካሪው በመንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ፍጥነቱን በመቀነስ ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ ማለፍ ይችላል፡፡
▶ ይህ መብራት በአብዛኛው የትራፊክ መጨናነቅ በማይበዛበት ወቅት ለምሳሌ በምሽት አሽከርካሪዎች ሌሎች ተላላፊዎች ሳይኖሩ ለረጅም ሰዓት እንዳይቆሙ እንደ ሁኔታው በጥንቃቄ መተላለፍ እንዲችሉ ሊያገለግል ይችላል፡፡
▶እንዲሁም የተለየ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ሆኔታ እንዳለ ለመግለጽ ለሊት ለሊት የሚበራ ሲሆን ይህ የተሽከርካሪ ማስተላለፊ መብራት ሲበራ የደረሰ ማንኛውም አሽከርካሪ ፍጥነቱን በመቀነስ ግራና ቀኙን ተመልክቶ ተላላፊ ካለ ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቆ ማሽከርከር አለበት፡፡

Part 2.3 ጥንድ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች

ጥንድ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች

ጥንድ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች የሚያስተላልፉት መልዕክት (ትእዛዝ ) እላያቸው ላይ ባለው ቀስት መሰረት ወይም መብራቶቹ ባሉበት አቅጣጫ ይወሰናል፡፡

ጥቅም ▶ የጥንድ መብራቶች ጥቅም በአንድ ጊዜ የሁለት አይነት መብራቶችን ጥንድ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነው ➡ ማለትም (መብራቶች ጎን ለጎን በጥንድ ሆነው ሲበሩ) የሚያስተላልፉት ትዕዛዝ ወይም መልዕክትም ጥንድ ይሆናል፡፡

1- ቀይ መብራት በበራበት በኩል▸ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ወደ ግራ የሚታጠፉት አሽከርካሪዎች ይቆማሉ፡፡

2- አረንጓዴ መብራት በበራበት በኩል ▸ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ቀጥታ ፊት ለፊትና ወደ ቀኝ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ጉዞ እንዲቀጥሉ ስለተፈቀደላቸው መሔድ አለባቸው፡፡

3- አረንጓዴ መብራት በበራበት በኩል ▸ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ወደግራ ለሚታጠፉት አሽከርካሪዎች እንዲጓዙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

4- ቀይ መብራት በበራበት በኩል▸ ቀስቱ እንደሚያመለክተው ፊት ለፊት ወይም ወደ ቀኝ ታጥፈው የሚጓዙ አሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ይገደዳሉ፡፡


Chapter 4 የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች

የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች

ትራፊክ፦ ማለት በየብስ በባህርና በአየር ያለ ማንኛውም እንቅስቃሴ ማለት ነው።

የትራፊክ ፖሊስ፡-

የትራፊኩን ወይም የተሽከርካሪዎችን እና የእግረኞችን እንቅስቃሴ ሁኔታ ለመቆጣጠር ብዙውን ጊዜ በመስቀለኛ መንገዶች፣ በአደባባዮች፣ የትራፊክ ፍሰቱ ከፍተኛ በሆነባቸው ቦታዎች፣ የትራፊክ ፖሊሶች የትራፊክ ፍሰቱን ለመቀነስና ስርዓት ለማስያዝ ሲባል የማስተናበር ስራዎችን የሚሠሩ ናቸው።

የትራፊክ ፖሊሶች የሚሰጡት የእጅ ምልክት ትዕዛዝና ትርጓሜ










Chapter 5 የትራንስፖርት ህጎች እና ደንቦች

Part 5.1 ከቁጥር ጋር የተገናኙ የትራንስፖርት ህግና ደንቦች

✔ 1 ሜትር፡- ማንኛውም አሽከርካሪ ከተጠቀሰው ከ 1 ሜትር ሜትር በላይ ከተሽከርካሪው የፊት አካል ውጪ ትርፍ ጭነት መጫን የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ብዙ ቦታ በመያዝ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያውካል፡፡)

✔ 2 ሜትር፡- ማንኛውም አሽከርካሪ ከተጠቀሰው 2 ሜትር በላይ ከተሽከርካሪው የኃላ አካል ውጪ ትርፍ ጭነት መጫን የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ብዙ ቦታ በመያዝ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያውካል፡፡)

✔ 2 ሰዓት፡- የተበላሸ ከባድ ተሽከርካሪን (ካሚዮንን) በከተማ ክልል ውስጥ ከተጠቀሰው 2 ሰዓት በላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ከተሽከርካሪው ርዝመትና ስፋት አንፃር ተሽከርካሪው ሳይነሳ ለብዙ ሰዓት ከቆየ የትራፊክ እንቅስቃሴውን በጣሙን ያውካል፡፡)

✔ 3 ሜትር፡- በሚጎትት እና በሚጎተት ተሽከርካሪ መሀል ከተጠቀሰው 3 ሜትር በላይ አስፍቶ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- በቀላሉ ለመዞር ወይም ለመታጠፍ አይመችም፣ ብዙ ቦታ በመያዝ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያውካል፡፡)

✔ 4 ሰዓት፡- አሽከርካሪዎች ያለ እረፍት ከ4 ሰአት በላይ እንዳያሽከረክሩ ይመከራል።

✔ (ምክንያቱም፦ አንድ አሽከርካሪ ከ 4 በላይ ሲያሽከረክር የድካም ስሜት ይፈጠራል ይሄ ደግሞ የአእምሮና የአካል ብቃታችን እንዲቀንስ በማድረግ ወደ አደጋ ውስጥ እንድንገባ ያደርጋል። ሰለዚህ አሽከርካሪዎች 4 ሰአትም ሳይጠብቁ በተቻለ መጠን በየሁለት ሰአቱ እረፍት ቢያደርጉ የበለጠ ንቁ ሆነው ማሽከርከር ይችላሉ።)

✔ 4 ሰዓት፡-ያለእረፍት ከተጠቀሰው ከ 4 ሰዓት በላይ መኪና ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- አሽከርካሪው በየ 4 ሠዓቱ እረፍት ሳይወስድ በተከታታይ በማሽከርከሩ ምክንያት በሚፈጠር ከባድ ድካም ምክንያት አደጋ አዳይፈጠር ነው ፡፡)

✔ 5 ሜትር፡- ከጎርፍ ማስወገጃ ፉካ (ቦይ) በተጠቀሰው ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- የጎርፍ አቅጣጫን ሊያስቀይር ይችላል፡፡ ፉካውን (ቦዩን) ከእይታ በመከለል ሌሎች አሽከርካሪዎችንም ሆነ እግረኞችን ያውካል፡፡)

✔ 6 ሜትር፡- በባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በተጠቀሰው ሜትር ክልል ውስጥ የማርሽ ዘንግ መነካካት የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ልለፍ አልለፍ
፣ ባቡሩ ይደርስብኛል ወይስ አይደርስብኝም
በሚለው የማመንታት ሀሳብ ምክንያት የሚደርስን አደጋ ለመቀነስ፡፡)

✔ 6 ሰዓት፡- ማንኛውንም የተበላሸ ተሽከርካሪ በከተማ ክልል ውስጥ ከተጠቀሰው ሰዓት በላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ተጎትቶ ወይም ቀላል ጥገና ተካሂዶለት ሳይነሳ ለብዙ ሰዓት ከቆየ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያውካል፡፡)

✔ 12 ሜትር፡- በእግረኛ ማቋረጫ (ዜብራ ክሮስ) አካባቢ በተጠቀሰው በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 12 ሜትር፡- በነዳጅ ማደያ (Fuel Station) አካባቢ በተጠቀሰው በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 12 ሜትር፡-በማንኛውም አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች አካባቢ በተጠቀሰው በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 12 ሜትር፡-ቁም!! በሚለው የመንገድ ዳር ምልክት አካባቢ በተጠቀሰው በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 12 ሜትር፡-በማንኛውም መስቀለኛ ወይም በለ አራት አቅጣጫ መንገዶች ላይ እና በመገናኛ መንገዶች ላይ መንገዶች ከሚገናኙበት ማዕዘን ወይም ኩርባ ከ 12 ሜትር ባነሰ ርቀት ውስጥ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- በተለያየ አቅጣጫ ወደ መንገዱ የሚመጡ መኪኖች ስላሉ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት እንዳይፈጠር እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት ነው፡፡)

✔ 12 ሜትር፡-በማንኛውም መውጫና መግቢያ በሮች (ለምሳሌ፡- በሆስፒታል፣ በእሳትና ድንገተኛ፣ በፖሊስ ጣቢያ፣ በመንግስትና በግል ተቋማት፣ . . .) መውጫና መግቢያ በሮች አካባቢ በተጠቀሰው በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 12 ሜትር፡-የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በታች በ ሆነ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወይም የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር ባነሠ መንገድ ላይ ከሌላ ከቆመ ተሽከርካሪ በተቃራኒው በትይዩ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- መንገዱ እየጠበበ ስለሚመጣ የትራፊክ መጨናነቅ ይጨምራል፡፡)

✔ በአጠቃላይ ፡- ከማንኛውም አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች፣ ከእግረኛ ማቋረጫ (ዜብራ)፣ ከማንኛውም መጋቢ ወይም መስቀለኛ መንገዶች፣ ከማንኛውም መውጫና መግቢያ በሮች (ለምሳሌ፡- ከሆስፒታል፣ ከእሳትና ድንገተኛ፣ ከፖሊስ ጣቢያ፣ ከመንግስትና ከግል ተቋማት፣ . . .) አካባቢ በተጠቀሰው 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡-
- በተሽከርካሪዎች ላይ በሚፈጠር አደጋ ምክንያት ነዳጅ ማደያ አካባቢ አደገኛ የእሳት አደጋ ሊፈጠር ስለሚችል፡፡
- አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በቀላሉ እንዳይታዩ ሰለሚከለክል /ስለሚጋርድ/
- እግረኞች የሌሎችን ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በቀላሉ እንዳይመለከቱ እና እንዳይከታተሉ ስለሚጋርድ እንዲሁም
- አሽከርካሪዎች የእግረኞችን እንቅስቃሴ በቀላሉ እንዳይመለከቱ እና እንዳይከታተሉ ስለሚጋርድ
- የትራፊክ መጨናነቅን ስለሚጨምር
- ታጣፊ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲታጠፉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንዳያውክ ነው፡፡)

✔ 15 ሜትር፡- ከአውቶቡስ ማቆሚያ ፌርማታ ከፊትና ኃላ በተጠቀሰው በ15 ሜትር ክልል ውስጥ እንዲሁም የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በታች የሆነ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ከሆነ በትይዩ በ30 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ለ አውቶብሶች ማቆሚያ ቦታ እንዲኖራቸው ነው፡፡)

✔ 15 ሜትር፡- የመስቀለኛ መንገድን አቋርጦ ወደ ግራ የሚታጠፍ ማንኛውም አሽከርካሪ ከተጠቀሰው ሜትር በፊት የግራ (ወደ ግራ) ፍሬቻ ማብራት አለበት፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ለሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች አስቀድሞ ለማሳወቅ፡፡)

✔ 20 ሜትር፡- ከማንኛውም የባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በተጠቀሰው 20 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ከሁሉም በተሻለ ረጅም ሜትር ማቆም የተከለከለበት ምክንያት የባቡር መሄጃ መንገድ እንደመሆኑና ባቡርን እንደተሽከርካሪ በቀላሉ በፍጥነት ለመቆጣጠር ስለማይቻል በእይታ ችግር ተሽከርካሪዎች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ከወዲሁ መንገዱን ለእይታ አመቺ በማድረግ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ፡፡)

✔ 25 ሜትር፡- ከማንኛውም መውጫና መግቢያ በር በትይዩ በተጠቀሰው 25 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ተሽከርካሪዎች ለመግባት ወይም ለመውጣት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ እክል ላለመፍጠር፡፡)

✔ 30 ሳ.ሜ፦ በትርፍ ጭነቶች ላይም ከ30 ሳ.ሜ ካሬ ያላነሰ ቀይ ጨርቅ እንዲሁም በምሽት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ከፊት ነጭ ወይም ቢጫ ከኃላ ቀይ መብራት ሊያስገጥም ይገባል፡፡

✔ ቀይ ጨርቅ ፦ በትርፍ ጭነቶች ላይ ከ30 ሳ.ሜ ካሬ ያላነሰ ቀይ ጨርቅ መንጠልጠል አለበት፡፡

✔ ነጭ ወይም ቢጫ መብራት ፦ከፊት ትርፍ ጭነት ጭኖ በምሽት የሚንቀሳቀስ አሽከርካሪ ከፊት ነጭ ወይም ቢጫ መብራት ሊያደርግ ይገባል፡፡

✔ ቀይ መብራት ፦ከኋላ ትርፍ ጭነት ጭኖ በምሽት የሚንቀሳቀስ አሽከርካሪ ከኋላ ቀይ መብራት ሊያደርግ ይገባል፡፡

✔ በአጠቃላይ ስለ ጭነት ፦ በትርፍ ጭነቶች ላይ ከ30 ሳ.ሜ ካሬ ያላነሰ ቀይ ጨርቅ እንዲሁም በምሽት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ከፊት ነጭ ወይም ቢጫ ከኃላ ቀይ መብራት ሊያስገጥም ይገባል፡፡

✔ (ምክንያት፡- በቀላሉ ለሌሎች አሽከርካሪዎች ወይም ተላላፊዎች ለመታየት፡፡)

✔ 30 ሜርት፡- ማንኛውም አሽከርካሪ አርቆ ወይም አሻግሮ ለማየት ባልቻለበት ጊዜ ከኮረብታ ጫፍ ፣ ቁልቁለት፣ ከድልድይ፣ ተነጥሎ ከተሰራ መሹለኪያ ወይም ከጎባጣ መንገድ ሲደርስ በተጠቀሰው 30 ሜትር ክልል ውስጥ መቅደም /መደረብ/ ፤ አዙሮ መመለስ ፤ወደ ግራ መጠምዘዝ እና ወደ ግራ አቅጣጫን ወይም ረድፍን መቀየር የተከለከለ ነው፡፡

✔ 30 ሜትር፡- በማንኛውም የባቡር ሀዲድ ማቋረጫ መንገድ ላይ በተጠቀሰው 30 ሜትር ክልል ውስጥ መቅደም /መደረብ/ ፤ አዙሮ መመለስ እና ከግራ ወደ መሀል፣ ከመሀል ወደ ግራ፣ ከመሀል ወደ ቀኝ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደ መሀል፣ ከቀኝ ወደ ግራ አቅጣጫን ወይም ረድፍን መቀየር የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ብዙ ጊዜ በእነዚህ አካባቢዎች የትራፊክ እንቅስቃሴው እየጨመረ ስለሚመጣ እንደተፈለገ አቅጣጫ መቀየር ካልተከለከለ በስተቀር የትራፊክ እንቅስቃሴው የበለጠ እየጨመረና እየተጨናነቀ ስለሚመጣ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እጅጉን ያውካል፡፡)

✔ 30 ሜትር፡- በማንኛውም የመስቀለኛ መንገድ ላይ በተጠቀሰው 30 ሜትር ክልል ውስጥ መቅደም /መደረብ/ ፤ አዙሮ መመለስ እና ከግራ ወደ መሀል፣ ከመሀል ወደ ግራ፣ ከመሀል ወደ ቀኝ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ ወደ መሀል፣ ከቀኝ ወደ ግራ አቅጣጫን መቀየር የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ብዙ ጊዜ በእነዚህ አካባቢዎች የትራፊክ እንቅስቃሴው እየጨመረ ስለሚመጣ እንደተፈለገ አቅጣጫ መቀየር ካልተከለከለ በስተቀር የትራፊክ እንቅስቃሴው የበለጠ እየጨመረና እየተጨናነቀ ስለሚመጣ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እጅጉን ያውካል፡፡)

✔ 30 ሜትር፡- በአውቶቡስ ማቆሚያ ፌርማታ አካባቢ የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በታች በሆነ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ላይ ተሽከርካሪን በትይዩ በተቃራኒ በኩል በ30 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ 40 ሳ.ሜ(0.4 ሜትር)፡- ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን በሚያቆምበት ወቅት ከመንገድ (40 ሳ.ሜ) ጠርዝ ከተጠቀሰው 40 ሳ.ሜ በላይ አስፍቶ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- መንገዱን በማጥበብ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያውካል፡፡)

✔ 48 ሰዓት፡- ማንኛውንም የተበላሸ ተሽከርካሪን ከከተማ ክልል ውጪ ከተጠቀሰው 48 ሰዓት በላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ከከተማ ክልል አንፃር ሲታይ ሰዓቱ ከፍ የተደረገበት ምክንያት ተሽከርካሪውን ጎትቶም ሆነ ቀላል ጥገናን አከናውኖ ለማንሳት ባለሙያዎች እስኪደርሱ ወይም እስከሚመጡ ጊዜ ስለሚወስድና በዚህ አካባቢም ያለው የትራፊክ እንቅስቃሴው አነስተኛ ስለሆነ ነው፡፡)

✔ 50 ሜርት፡- በግልፅ ለማየት አዳጋች በሆኑ መንገዶች (ኩርባዎች፣ ጠመዝማዛማ፣ . . .) በተጠቀሰው 50 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም ክልል ነው።

✔ (ምክንያት፡- ለማየት አዳጋች መንገዶች እንደመሆናቸው መጠን በእይታ ችግር ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋና የትራፊክ እንቅስቃሴ መታወክ ለመቀነስ፡፡)

✔ 50 ሜርት፡-ማንኛውም አሽከርካሪ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ድፍኑ ነጭ መስመር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ከተጠቀሰው 50 ሜትር በፊት የሚሄድበት የመስመር አቅጣጫ ወይም ረድፍ መምረጥ /በያዝ/ አለበት ፡፡

✔ (ምክንያት፡- የመስቀለኛ መንገድ 50 ሜትር ክልል የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚበዛበት አካባቢ ስለሆነ ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋና የትራፊክ እንቅስቃሴ መታወክ ለመቀነስ፡፡)

✔ 50 ሜትር፡- ከከተማ ክልል ውጪም ሆነ በከተማ ክልል ውስጥ ከፊት ለፊት ተሽከርካሪ ካለ በተጠቀሰው 50 ሜትር ክልል ውስጥ ረጅሙን የግንባር መብራት መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ከፊት ለፊት የሚንቀሳቀስን ተሽከርካሪ እይታ ስለሚያውክ ነው ።)

✔ 50 ሜትር፡- ማንኛውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኃላ ባለው መንገድ በ50 ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትራፊክ ወይም ተላላፊ በግልጽ በሚታይ መልኩ ባለ 3/ሶስት ማእዘን አንጸባራቂ ሰሌዳ ማስቀመጥ አለበት።

✔ (ምክንያት፡- ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ከሩቅ ተመልክተውት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለመጠቆም፡፡)

✔ 50 ሜትር፡- አንድ አሽከርካሪ በመታጠፊያ ቦታ የሚታጠፍ ከሆነ ከተጠቀሰው 50 ሜትር በፊት ፍሬቻ ማብራት አለበት፡፡

✔ (ምክንያቱም፡- ለሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ሆነ ከኋላ ለሚከተሉ አሽከርካሪዎች አስቀድሞ ለማሳወቅ፡፡)

✔ 100 ሜትር፡- የአደጋ አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪን በስራ ላይ እያለ ከተጠቀሰው ከ 100 ሜትር ባነሰ ርቀት ተከትሎ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

✔ (ምክንያት፡- ምክንያቱም የአደጋ አገልግሎት ሠጭ ተሽከርካሪዎች በቅድሚያ የሠውን ህይወት የማዳን ስራ ስለሚሠሩ ያለ ምንም መከልከል የማሽከርከር ፍቃድ ስላላቸው በሚኖረው መሯሯጥ ምክንያት የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት መንገዱን ከአደጋ ስጋት አስቀድሞ ነፃ እና ሌሎች አሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰን ገደብን እንዳይጥሱ ለማድረግ)።

✔ ከፍጥነት ወሰን መመርያ ቁጥር 1/2010 ላይ የተወሰደ፡-

በከተማ ክልል ዉስጥ የሚያሽከረክር ማንኛዉም አሽከርካሪ በግልጽ በመንገዱ ላይ የሚታይ የተቀመጠ ልዩ የፍጥነት ወሰን የሚደነግግ የትራፊክ ምልክት ከሌለ በስተቀር ማንኛዉንም የሞተር ተሸከርካሪ መደበኛ የፍጥነት ወሰን መመርያ ቁጥር 1/2010 ላይ በሰፈረዉ መሰረት ይሆናል ፡፡
1. የእግረኛ መንገድ በሌለበት የመንደር ዉስጥ እና የሰብሳቢ መንገድ ላይ በሰዓት ከ 15 ኪሎ ሜትር በላይ ማሽከርከር የለበትም ፡፡
2. የእግረኛ መንገድ ባለበት የመንደር ዉስጥ እና የስብሳቢ መንገድ ላይ በሰዓት ከ 30 ኪሎ ሜትር በላይ ማሽከርከር የለበትም፡፡
3. በመለስተኛ የከተማ ጎዳና ላይ በሰዓት ከ 40 ኪ.ሜ.በላይ ማሽከርከር የለበትም ፡፡
4. በዋና የከተማ ጎዳና እና በቀለበት መንገድ የዉጭኛዉ መተላለፍያ መስመር ላይ በሰዓት ከ 50 ኪ.ሜ በላይ ማሽከርከር የለበትም ፡፡
5. በቀለበት መንገድ የዉስጠኛዉ መተላለፍያ መስመር ላይ በሰዓት ከ70 ኪ.ሜ በላይ ማሽከርከር የለበትም ፡፡
6. የቀላል ባቡር የተዘረጋበትን መስመር ተከትሎ በሚገኝ ዋና የከተማ ጎዳና ላይ በሰዓት ከ 40 ኪ.ሜ በላይ ማሽከርከር የለበትም ፡፡


Part 5.2 ከቁጥር ውጪ ያሉ የትራንስፖርት ህግና ደንቦች

▶ 1. በጠባብ ድልድይ ፣ በመስቀለኛ እና ለማየትና ለማሽከርከር አዳጋች በሆኑ መንገዶች ላይ (ኩርባ፣ ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ጠመዝማዛማ፣ የተበላሸ መንገድ፣ . . .) ተሽከርካሪን መቅደም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 2. የአደጋ አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪን በስራ ላይ እያለ መቅደም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 3. የትራፊክ ፍሰቱ ከፍተኛ በሆነ መንገድ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከርም ሆነ ለማቆም የሚፈቅድ ምልክት ከሌለ በስተቀር ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 4. በቀኝ በኩል ቦታ እያለ በግራ በኩል ቀስ ብሎ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 5. ቀስ (ረጋ) ብሎ ማሽከርከር የፈለገ አሽከርካሪ የቀኝ መስመሩን ይዞ ማሽከርከር አለበት፡፡

▶ 6. በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ (ዜብራ) እግረኛን ለማሳለፍ የቆመ ተሽከርካሪን መቅደም ወይም መደረብ የተከለከለ ነው፡፡

▶ 7. በቀኝ በኩል ተሽከርካሪን መቅደም ወይም መደረብ የተከለከለ ነው፡፡

▶ 8. ተሽከርካሪን መቅደም የፈለገ አሽከርካሪ መቅደም የሚፈቀድለት በስተግራ በኩል ብቻ ነው።

▶ 9. ተሳፋሪን ከ 25 ኪ.ግ በታች ለሆነ ጭነት ማስከፈል ክልክል ነው ወይም ተሳፋሪ እስከ 25 ኪ.ግ ለሆነ ጭነት በነፃ መጫን ይችላል ።

▶ 10. በከተማ ክልል ውስጥ ረጅም የግንባር መብራትን መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 11. ለማየትና ለማሽከርከር አዳጋች በሆኑ መንገዶች (ኩርባ፣ ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ጠመዝማዛማ፣ የተበላሸ መንገድ፣ . . .) ረጅም የግንባር መብራትን መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 12. በባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ ላይ ዳገት የሚወጣና ቁልቁለት የሚወርድ ተሽከርካሪ በአንድ መንገድ ቢገናኙ ዳገት የሚወጣው ቅድሚያ ያገኛል ወይም ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

▶ 13. ከፍተኛ ድምፅ ያለውን ጡሩምባ (ክላክስ) በከተማ ክልል ውስጥ መጠቀም የተከለከለ ነው።

▶ 14. ከፍተኛ ጭስ የሚያጬስ ተሽከርካሪን ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 15. በመንገድ ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ማሳጠብ ወይም ማጠብ የተከለከለ ነው፡፡

▶ 16. የተሸፈነ፣ ቀለሙ የለቀቀ፣ የተጨማደደ ሰሌዳ (ታርጋ) ለጥፎ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 17. የትራፊክ ደሴትን (አደባባይን) ወደ ግራ መዞር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 18. የጭንቅላት መከላከያ (ሔልሜት) ሳያደርጉ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 19. የቆመ ተሽከርካሪን ደርቦ ሌላ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 20. በሰንሰለት የሚጓዝና በሰዓት ከ10 ኪ.ሜ በታች የሚሄድ ማንኛውንም ተሽከርካሪ በዋና መንገድ ላይ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 21. እጅን በመስኮት አውጥቶ ተሽከርካሪ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 22. ማንኛውንም ነገር እየበሉና እየጠጡ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 23. ሲጋራ እያጬሱ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 24. አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ ወይም እየተጠቀሙ፤ የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ ወይም እየጠጡ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 25. ግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር መሪን በአንድ እጅ ይዞ ማሽከርከር የተከለከለ ነው፡፡

▶ 26. ሦስተኛ ተሽከርካሪን ደርቦ ማሽከርከር ወይም መቅደም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 27. ለማየትና ለማሽከርከር አስቸጋሪ ወይም አዳጋች በሆነ መንገድ ወይም ሁኔታ (ለምሳሌ ኩርባ፣ ጉም፣ ጭጋግ፣ ዝናብ፣ አቧራ፣. . .) ተሽከርካሪን መቅደም (መደረብ) የተከለከለ ነው ።

▶ 28. የአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ከማንኛውም ተላላፊና ተሽከርካሪ ቅድሚያ አላቸው፡፡

▶ 29. በስተግራ በኩል ማንኛውንም ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 30. በነጠላ መንገድና መንገዱ በነጭ ቀለም በተከፈለበት ስፍራ መኪና ማቆም የተከለከለ ነው።

▶ 31. ሌላውን ተላላፊ በሚያሰናክል አኳሃን ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 32. ከተመሳሳይ አቅጣጫ ሁለት ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ደሴት (አደባባይ) ጋር እኩል ቢደርሱ አደባባይ ለመዞር በግራ በኩል የሚገኘው ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያገኛል፡፡

▶ 33. በመስቀለኛ መንገድ ላይ ከተለያየ አቅጣጫ በ900 (አጠገብ ለአጠገብ ካሉ መጠምዘዣዎች) ተሽከርካሪዎች እኩል ቢገናኙ በስተቀኝ ያለው ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያገኛል፡፡

▶ 34. ከተለያየ አቅጣጫ በ1800 (ፊት ለፊት) ተሽከርካሪዎች እኩል በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቢገናኙ ቀጥታ የሚያሽከረክር ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያገኛል፡፡

▶ 35. በመሿለኪያዎች ውስጥና በድልድዮች ላይ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ 36. ከማንኛውም ማጠምዘዣ (መጋቢ መንገድ) ዋናውን መንገድ የሚቀላቀሉ ተሽከርካሪዎች ለእግረኞችና በዋና መንገድ ለሚገኙ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለባቸው፡፡


Part 3 የተሽከርካሪን እንቅስቃሴ የሚወስኑ ህጎች

❖ መስቀለኛ መንገዶች ስለመድረስ እና ስለመግባት፡

✔ ማንኛውም የተሽከረካሪ አሽከርካሪ ከአንድ መስቀለኛ መንገድ በደረሰ ጊዜ ከመስቀለኛው መንገድ ውስጥ ለገባ ተሸከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡

✔ ከተለያየ አቅጣጫ ሁለት ወይም ከሁለት የሚበዙ ተሸከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ከመስቀለኛ መንገድ የደረሱ እንደሆነ አሽከርካሪው ከቀኝ በኩል ለተቃረበው ተሸከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡

✔ በአንድ መስቀለኛ መንገድ ላይ የትራፊክ ክብ ሰርቶ እንደሆነ፣ ወደ ክቡ የተቃረበው ተሸከርካሪ አሽከርካሪ አስቀድሞ ክቡን በመዞር ላይ ላሉት ተሸከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡

❖በመስቀለኛ መንገድ ላይ ወደ ግራ ስለመጠምዘዝ

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ከገባ በኋላ ወደ ግራ ለመጠምዘዝ ቢፈልግ አደጋ እንዳያስከትል በቂ በሆነ ርቀት ላይ አቁሞ ከፊት ለፊቱ ለቀረበው ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡

❖ ቅድሚያ ወደ ሚሰጥበት መንገድ ስለመግባት፡

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ ቅድሚያ የሚሰጥበት መንገድ ጋር ከተያያዘ መስቀለኛ መንገድ በተቃረበ ጊዜ የማለፍ ቅድሚያ ምልክት ከተደረገበት መንገድ ለተቃረበ ተሸከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት።

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ ከፊት ለፊቱ ቁም የሚል ምልክት ከተደረገበት መስቀለኛ መንገድ በደረሰ ጊዜ ተሸከርካሪውን በማቆሚያው መስመር ወይም በእግረኞች ማቋረጫ አጠገብ ወይም አቋራጩን መንገድ አሻግሮ ለማየት በሚያስችለው ቅርብ ቦታ ላይ አቁሞ ከአቋራጩ መንገድ ለተቃረበው ማንኛውም ተሸከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡

❖ ስለ አደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪዎች ልዩ ሁኔታዎች

✔ ማናቸውም የአዳጋ አገልግሎት ተሸከርካሪ አሽከርካሪ ተግባሩን በሚያከናውንበት ጊዜ ⤵

✔ በየትኛውም ደንብ የተፃፈውን ግዴታ ሳይጠብቅ ተሸከርካሪውን ለማቆም

✔ አደጋ በማያደርስ አኳኋን የተሸከርካሪውን ፍጥነት ቀንሶ ቁም በሚል ምልክት ላይ ሳይቆም

✔ ለማለፍ ከተወሰነው ፍጥነት በላይ ለመንዳት

✔ ተግባሩን ለመፈፀም በሚያስፈልገው መጠን ስለትራፊክ የወጡትን ድንጋጌዎች እና የመንገድ ምልክቶች ሳይመለከት በፈቀደው አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ይፈቀድለታል

✔ ማንኛውም የአደጋ አገልግሎት አሽከርካሪ ከተፈቀደለት ተግባር ውጪ ለሆኑ ሌሎች ጉዳዮች ተሸከርካሪውን መጠቀም የለበትም።

✔ ቀድሞ የሚሔደው የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪ በሚፈፅመው ተግባር ተከፋይ የሆነ የሌላ የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪ አሽከርካሪ ካልሆነ በቀር ማንኛውም አሽከርካሪ ከአንድ 100 ሜትር ባነሰ ርቀት ከአንድ የአደጋ አገልግሎት ተሸከርካሪ ኃላ ተጠግቶ መንዳት የለበትም።

❖ ተሽከርካሪን ስለማቆም

✔ ማንኛውም የባለሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን ከቁልቁለት መንገድ ላይ ባቆመ ጊዜ የተሸከርካሪውን የፊት እግሮች ከመንገዱ በጣም ወደ ሚቀርበው ጠርዝ መመለስ አለበት።

✔ የድንጋይ ጠርዝ ባለበት መንገድ ላይ ተሽከርካሪውን ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ የሚያቆም ማናቸውም ሰው ከድንጋይ ጠርዝ በጣም የሚቀርበውን የተሸከርካሪው እግር ከ40 ሣንቲ ሜትር እንዳይርቅ አድርጎ ከድንጋይ ጠርዝ በትይዩ መስመር ማቆም አለበት፡፡

✔ የማንኛውም ባለሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በምሽት ጊዜ ተሸከርካሪውን ሲያቆም የማቆሚያ ወይም የፖርኪንግ መብራት ማብራት አለበት።

❖ ለማቆም የተከለከሉ ቦታዎች

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በላይ ካልሆነ በቀር ተሸከርካሪውን ከሌላ ተሸከርካሪ ተቃራኒ አንፃር ከመንገድ ላይ ለጊዜው ወይም ለረጅም ጊዜ ማቆም የለበትም።

✔ ማንኛውም የተሸከርካሪ አሽከርሪ በዚያው መንገድ የሚነዳ የሌላ ተሸከርካሪ አሽከርካሪ ከሁለቱም አቅጣጫ ከ50 ሜትር ርቀት ላይ ለማየት በማይችልበት ሥፍራ በመንገድ ላይ ተሸከርካሪውን ማቆም የለበትም።

❖ አቅጣጫ መቀየሪያ ህጎች

❖ ወደ ግራ ስለ መጠምዘዝ፡

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ አርቆ ወይም አሻግሮ ለማየት ባልቻለበት ጊዜ ከኮረብታ ጫፍ ፣ ቁልቁለት፣ ከድልድይ፣ ተነጥሎ ከተሰራ መሹለኪያ ወይም ከጎባጣ መንገድ ሲደርስ ከ 30 ሜትር ባነሰ ርቀት ውስጥ ወደ ግራ መጠምዘዝ የለበትም።

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ ከመስቀለኛ ወይም ከ ባቡር ሐዲድ ማቋረጫ መንገድ በ 30 ሜትር ርቀት ውስጥ ወደ ግራ መጠምዘዝ የለበትም።

✔ ማንኛውም አሽከርካሪ የማያቋርጥ ያልተቆራረጠ ነጭ የቀለም መስመር በተደረገበት መንገድ ላይ ወደ ግራ መጠምዘዝ የለበትም።

❖ በትራፊክ ደሴት ዙሪያ ስለማሽከርካር፡

✔ በትራፊክ ደሴት ዙሪያ የሚያሽከረክሩ ማንኛውም የተሸከርካሪ አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴት ቀኙን አቅጣጫ ብቻ ተከትሎ መንዳት አለበት፡፡

❖ በነጠላ መንገዶች በተከፋፈለ መንገድ ስለማሽከርከር፡

✔ በሌላው ተላላፊ ወይም በሚከተለው ተሸከርካሪ ላይ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን ካልተረጋገጠ በስተቀር ከአንዱ ነጠላ መንገድ ወደ ሌላ አቅጣጫ መቀየር አይፈቀድለትም፡፡

❖ ስለ መጠምዘዝና ወደ ኋላ ስለ ማሽከርከር፡

✔ ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ በሌላ ተላላፊና በሚከተሉት ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ የማያስከትል መሆኑን ካላረጋገጠ በቀር በሚሄድበት አቅጣጫ ተሽከርካሪውን ወደ ሌላ መንገድ ለመጠምዘዝ ወይም የሚሄድበትን አቅጣጫ በማንኛውም አኳኋን ለመለወጥ ወይም የቆመ ተሸከርካሪውን ሲያስነሳ የነበረበትን አቅጣጫ ለመለወጥ አይፈቀድለትም ፡፡

❖ ወደ ቀኝ የሚጠመዘዝ፡

✔ ወደ ቀኝ የሚጠመዘዝ አሽከርካሪ በተቻለ መጠን የመንገዱን ቀኝ ጎን ተጠግቶ መጠምዘዝ አለበት ይህንንም ለማድግ የሚችለው በቀኝ በኩል የሚጓዝ ሌላ ተሽከርካሪ የሌለ እንደሆነ ነው።

❖ ወደ ግራ ስለሚጠመዘዝ፡

⚫ ማንኛውም የሞተር ተሸከርካሪ አሽከርካሪ ወደ ግራ በሚጠመዘዝበት ወቅት፡

✔ ከባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወደ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ለመጠምዘዝ የመሀል አካፋዩን መስመር ወደ ግራ በመተው መስቀለኛ መንገድ መግባትና ወደ ግራ በሚጠመዘዝበት አቅጣጫ ባለው መንገድ ያለውን የመሀል አካፋይ መስመር ወደ ግራ በመተው መስቀለኛውን መንገድ መውጣት

✔ ከባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ወደ ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ ለመጠምዘዝ የመሀል አካፋዩን መስመር ወደ ግራ በመተው መስቀለኛ መንገድ መግባትና ወደ ግራ በሚጠመዘዝበት አቅጣጫ ያለውን ባለአንድ አቅጣጫ መንገድ የግራ ጠርዝ ይዞ ከመስቀለኛው መንገድ መውጣት

✔ ከባለአንድ አቅጣጫ መንገድ ወደ ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ ለመጠምዘዝ የባለአንድ አቅጣጫ መንገድ የግራ ጠርዝ*በመያዝ ወደግራ በሚጠመዘዝበት አቅጣጫ ያለውን ባለሁለት አቅጣጫ መንገድ የግራ ጠርዝ ይዞ ከመስቀለኛው መንገድ መውጣት

❖ ወደ ኋላ ስለማሽከርከር

✔ ማናቸውም የተሸከርካሪ አሽከርካሪ ወደ ኃላ ለማሽከርካር ግድ አስፈላጊ ከሆነና በሕይወትና በንብረት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጎ በማንኛውም መስቀለኛ መንገድና ደሴት ላይ ወደኋላ ማሽከርካር ይፈቀድለታል።

✔ ማንኛውም የተሸከርካሪ አሽከርካሪ ዕይታን የሚያውክ ወይም በተወሰነ ርቀት ለማየት ባልቻለበት ጊዜ የሚሄድበትን ነጠላ መንገድ ለውጦ ወደ ሌላው መስመር ለመሻገር አይፈቀድለትም።

❖ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ስለመጠቀም

▶ ማናቸውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ የሚገጥመውን አደጋ ለመከላከል ግድ አስፈላጊ ካልሆነ፣አደጋውን የሚከላከልበት ሌላ መንገድ ከሌለውና የሚያሰማውም የማስጠንቀቂያ ድምጽ በተቻለ መጠን አጭር ካልሆነ በስተቀር፣ በከተማ መንገድ ውስጥ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት አይፈቀድለትም።

▶ ተሽከርካሪ በቆመበት ግዜ በማናቸውም አኳኃን የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።

▶ ሆስፒታልና ትምህርት ቤት አከባቢ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ማሰማት ክልክል ነው።

❖ ነዳጅ ስለመሙላት/ማስሞላት

▶ ማንኛውም ሰው የተሽከርካሪው ሞተር እየሰራ፣ ተሽከርካሪው የህዝብ ማመላለሻ ከሆነ በተሽከርካሪ ውስጥ መንገዶች እያሉ ማናቸውም ነዳጅ መሙላት ወይም ማስሞላት የለበትም።

▶ በተሽከርካሪው አጠገብ እሳት ወይም ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ሲኖር በሞተር ተሽከርካሪው ነዳጅ እንዲሞላ ወይም የነዳጅ መክደኛ እንዲከፈት ወይም ሌላ ሰው ይህንን እንዲያደርግ መፍቀድ ክልክል ነው።

▶ ማናቸውም ሰው ተሽከርካሪውን ነዳጅ ሲሞላ ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው።

▶ በአጠቃላይ በነዳጅ ማደያ አካባቢ ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው።

▶ ማናቸውም ሰው ተሽከርካሪውን ነዳጅ ሲሞላ በሞባይል ስልክ ማነጋገር ወይም ሌሎች ኤሌክትሮኒክስ ነክ መሳሪያዎችን መጠቀም የለበትም።

❖ የተበላሸ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ስለመጠገን

1. ማንኛውም ሰው በመንገድ ላይ ተሽከርካሪን ለመጠገን ወይም ለማደስ አይፈቀድለትም ፣ ከዚህም ሌላ ተሽከርካሪው በማናቸውም አከኃን ያለ ማቋረጥ፣

▶ በከተማ ውስጥ ሲሆን ከ6 ሰአት በላይ
▶ ከከተማ ውጪ ሲሆን ከ48 ሰአት በላይ በአንድ ቦታላይ መቆየት የለበትም።

2. ማንኛውም ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው ፊትና ኃላ ባለው መንገድ በ50 ሜትር ርቀት ላይ ለሌላ ትርፊክ በግልጽ በሚታይ መልኩ ባለ 3/ሶስት ማእዘን አንጸባራቂ ሰሌዳ ማስቀመጥ አለበት።

3. ማንኛውም ሰው የተጎዳ ወይም የተበላሸ ተሽከርካሪ መኪና ከመንገድ ላይ በሚያነሳበት ግዜ በመንገድ ላይ የወዳደቁ የመስታወት ስባሪዎች እና ሌሎች ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ ከመንገድ ማስወገድ አለበት።

❖ ረጅም የግንባር መብራት መጠቀም የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች

▶ የመንገድ መብራት በቂ ካልሆነ በስተቀር በከተማ መንገድ ስታሽከረክር

▶ በተቃራኒ መንገድ የሚመጣ ተሽከርካሪ ሲቃረብና እስኪያልፍ ድረስ

▶ በ50 ሜትር ርቀት የምትከተለው ተሽከርካሪ ሲኖር

▶ ተሽከርካሪ በቆመበት ወቅት

▶ የማናቸውም ባለሞተር ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በማብሪያ ግዜ ተሽከርካሪውን ሲያቆም የማቆሚያ መብራት ማብራት አለበት።

❖ የንግድ ሸቀጥ አጫጫን

• ጭነት ከተሽከርካሪው በስተፊት ባለው ጫፍ ከአንድ/1 ሜትር በስተኃላ ከተሽከርካሪው ከሁለት/2 ሜትር በላይ ተርፎ መውጣት የለበትም።

• መብራት በሚበራበት ግዜ ከፊት ተርፎ በሚገኘው ጭነት ጫፍ ነጭ/ቢጫ ከኃላ ተርፎ በሚገኘው ጭነት ላይ ቀይ መብራት መደረግ አለበት።

• መብራት በማያስፈልግበት ግዜ በተራፊው ጭነት ላይ በፊትና በኃላ ጫፍ 30 ሳ.ሜ. ካሬ የሆነ ቀይ ጨርቅ ወይም ቀይ ቀለም የተቀባ ጠፍጣፋ ሰሌዳ መደረግ አለበት።

ተሽከርካሪ ስለመጎተት

• አንድ አሽከረካሪ በሌላ የሞተር ተሽከርካሪ በሚጎተትበት ጊዜ በመሀከላቸው ያለው ርቀት ከ3 ሜትር የማይበልጠ ሆኖ ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በሽቦ ገመድ ወይም በጠንካራ የመሳቢያ የብረት ዘንግ በጥብቅ መያያዝ አለባቸው።

• ማንኛውም የሞተር ተሽከርካሪ በአንድ ግዜ ከአንድ ተሽከርካሪ በላይ እንዲጎትት አየፈቀድለትም።

▶ ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚኖርበት መንገድ ላይ ተሽከርካሪን ያለ አግባብ ማቆምና መቅደም የተከለከለ ነው፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች ማቆምና መቅደም የተከለከለባቸውን እንዲሁም ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

❖ ተሽከርካሪን ማቆም የሚከለክልባቸው ሁኔታዎች

▶ በከተማ ክልል ውስጥ ከ 6 ሰአት በላይ በብልሽት ምክንያት በአውራ ጎዳና ላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ ከከተማ ክልል ውጭ ከ 48 ሰአት በላይ በብልሽት ምክንያት በአውራ ጎዳና ላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ ለከባድ ተሽከርካሪ ከ 2 ሰአት በላይ በብልሽት ምክንያት በአውራ ጎዳና ላይ ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

❖ ተሽከርካሪን ማቆም የሚከለክልባቸው ቦታዎች

▶ የጎርፍ ማስተላለፊያ ቦይ / ፉካ / ባለበት በ 5 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም ክልክል ነው፡፡

▶ በመስቀለኛ / በመገናኛ / መንገድ ፤ ቁም የሚል ምልከት ባለበት ፤ ከእግረኛ ማቋረጫ መስመር በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡

▶ ከባስ / ከአውቶቢስ / ማቆሚያ ፌርማታ ከፊት 15 ሜትር ከኋላ 15 ሜትር በአጠቃላይ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ የመንገዱም ስፋት ከ 12 ሜትር በታች በሆነ መንገድ ላይ ከአውቶቢስ ማቆሚያ ፌርማታ ትይዩ ወይም በተቃራኒ በ 30 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ በባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ 20 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም ክልክል ነው፡፡

▶ መስሪያ ቤቶች መውጫና መግቢያ በር ግራና ቀኝ ከ 12 ሜትር ባነሰ ርቀት ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም ክልክል ነው፡፡

▶ የመንገዱም ስፋት ከ 12 ሜትር በታች በሆነ መንገድ ላይ ከመስሪያ ቤቶች መውጫና መግቢያ በር ትይዩ ወይም በተቃራኒ ከ 25 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ የመንገዱም ስፋት ከ 12 ሜትር በታች በሆነ መንገድ ላይ በቆመ ተሽከርካሪ ትይዩ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ ከሁለቱም አቅጣጫ መንገዱን ግልጽ ሆኖ ማየት በማይቻልበት ስፍራ በ 50 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለ ነው፡፡

▶ በመንገድ ጥግ ቆሞ ከሚገኝ ተሽከርካሪ አጠገብ ደርቦ ማቆም ክልክል ነው።

▶ በድልድይና በመሿለኪያ መንገዶች ላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡

▶ በአንድ ነጠላ መንገድና መንገዱ በነጭ ቀለም በተከፋፈለበት ስፍራ ማቆም ክልክል ነው፡፡

ተሽከርካሪን መቅደም የሚከለክልባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች

1. ከመስቀለኛ ወይም ከባቡር ሀዲድ ማቋረጥ በ 30 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ መቅደም ክልክል ነው፡፡

2. በሶስተኛነት ደርቦ መቅደም ክልክል ነው፡፡

3. በኮረብታማ ጫፍ ላይ ፤ በጠባብ ድልድይ ላይ ፤ በመሿለኪያና በቁልቁለት መንገድ ላይ መቅደም ክልክል ነው፡፡

4. በሚቀድመውና በሚቀደመው ተሽከርካሪ መሀከል በቂ ርቀት ሳይኖር መቅደም የተከለከለ ነው፡፡

5. ድፍን ወይም ያልተቆራረጠ መስመርን አቋርጦ መቅደም የተከለከለ ነው፡፡

6. እግረኞችን ለማሳለፍ የቆመን ተሽከርካሪ መቀደም የተከለከለ ነው።

❖ መቆም ግዴታ የሆነባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች

1. ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የትራፊክ መብራት በሚበራበት ስፍራ / ቦታ / ላይ፡፡

2. ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ባለበት መንገድ ላይ፡፡

3. በእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ውስጥ እግረኞች ለማለፍ በእንቅቃሴ ላይ እያሉ፡፡

4. ከማንኛውም ቤት መውጫና መግቢያ መንገድ ወደ ዋና መንገድ ከመግባት በፊት ወይም ከመጋቢ መንገዶች ወደ ዋና መንገድ ሲገባ

❖ ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎችና ሁኔታዎች

▶ የእግረኛ ማቋረጫ መስመር ላይ

▶ ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች ባሉበት ቦታ ላይ

▶ ለህዝብ ተሽከርካሪዎች

▶ ለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች አደጋን ለመከላከል ሲሰማሩ

▶ መዝጊያ የሌለው የባቡር ሃዲድ ላይ

▶ ቁልቁለት የሚወርድ ተሽከርካሪ ዳገት ለሚወጣ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት።

▶ ከመጋቢ መንገድ ወደ ዋና መንገድ በመምጣት ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች በዋናው መንገድ ላይ ላሉት ቆመው ቅድሚያ መስጠት አለባቸው።

ሌሎች የትራፊክ ህግና ደንቦች

▶ መስቀለኛ መንገድ ላይ በ 50 ሜትር ክልል ውስጥ ከገቡ በኋላ አቅጣጫን መምረጥ ተሽከርካሪን መቅደም ክልክል ነው፡፡

▶ በመድሀኒት፤በመጠጥ፤በአደንዛዥዕፅ ተመርዞ ማሽከረከር ክልክል ነው፡፡

▶ ተሽከርካሪው ባለመታደሱ ምክንያት ከሚገባው በላይ ጭስ፤እንፋሎት፤ዘይት ወይም ነዳጅ የሚተፋ፤ድምፅ የሚያሰማ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ መንዳት ክልክል ነው፡፡

▶ ማንኛውም አሽከርካሪበ መሪ / በፍሬን / ሊቆጣጠርው የማይችለውን አደጋ እስካላጋጠመው ድረስ የማስጠንቀቂያ ድምፅ / ጡሩንባ / እንዲያሰማ አይፈቀድለትም፡፡

▶ ማንኛውም አሽከርካሪ የተሽከርካሪን በር በትክክል መዘጋቱን ወይም ተሳፋሪዎችን ለአደጋ የሚያጋልጥና በድንገት የማይከፈት መሆኑን ሳያረጋግጥ መንገድ ላይ እንዲቀሳቀስ አይፈቀድለትም፡፡

❖የመንገድ ደረጃ

✔ የመንገድ ደረጃ /ዓይነት/ አስፋልት፣ ኮረኮንች፣ አንሸራታች፣ ወዘተ በመባል የሚጠቀሱ ሲሆን በእነዚህ በተለያዩ የመንገድ ዓይነቶች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ የጉዞ ዝግጅት እንደዚሁ የተለያየ ይሆናል፡፡


Chapter 6 የሀገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ

☞ የፍጥነት ወሰን ገደብ

❖ የፍጥነት ወሰን ገደብ ወይም ልክ በፍጥነት ወሰን ደንብ ውስጥ እንደተወሰው ይሆናል።
▶ ስለሆነም ማንኛውም ሰው በማንኛውም መንገድ ላይ ተሽከርካሪ ሲያሽከረክር የመንገዱን ሁኔታ ፣ የትራፊኩን ብዛት እና ሁኔታ እንዲሁም ተላላፊውን ለማየት እና ተሽከርካሪውን በሙሉ ለመቆጣጠር ያለው ችሎታ ከሚፈቅድለት ፍጥነት በላይ ማሽከርከር አያስችለውም።
▶ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት መወሰን ተገቢ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ የመንገዶች ባለስልጣን በክልሉ ውስጥ በሚገኘው በማንኛውም መንገድ ላይ የተፈቀደውን የፍጥነት ወሰን ገደብ ወይም ልክ ለጊዜውም ወይም ለሁልጊዜ ለማሳነስ ይችላል።
- የመንገዶች ባለስልጣን ይህን ውሳኔ ሲያሳድር ተገቢውን ምልክት በመትከል ለሕዝብ ማስታወቅ ይኖርበታል።

❖ በዝግታ ስለ ማሽከርከር
▶ ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ ከመስቀለኛ መንገድ ፤ ከጎባጣ መንገድ ፣ ከእግረኛ ማቋረጫ ፤ ከጠማማ መንገድ ፥ ከጠባብ ድልድይ ከኮርብታ ጫፍ ወይም ቁልቁለት መንገድ ሲደረስ እንዲሁም በጠባብ ድልድይ ወይም በጠባብ መንገድ በጠመዝማዛ መንገድ ላይ በሚነዳበት ጊዜ ፥ የማየት ሀይል በሚቀንስበት ወቅት፥ ለእግረኛ እና በመንገዱ ላይ ለሚጠቀሙት ሁሉ እና አደጋ አንደ የሚያስከትል በሚያሰጋበት ጊዜ ሁሉ የተሽከርካሪውን ፍጥነት በጣም መቀነስ አለበት።

የሀገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ በሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች/ነገሮች ላይ የተመረኮዘ (የተመሰረተ) ነው፡፡
1- በመንገዶች ደረጃ /በመንገዶች አሰራርና አመችነት ሁኔታ/
2- በምና ሽከረክረው ተሽከርካሪ ክብደት
3- በምና ሽከረክረው ተሽከርካሪ የመጫን አቅም ላይ የተሞረኮዘ ነው።

የሀገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ በሚከተሉት መንገዶች ላይ ይሠራል

የሀገራችን መንገዶች በከተማ ክልል እና ከከተማ ክልል ውጪ የሚገኙ መንገዶች ተብለው በሁለት ይከፈላሉ።
ከከተማ ክልል ውጪ የሚገኙ መንገዶች ደግሞ 1ኛ ደረጃ ፥ 2ኛ ደረጃ እና 3ኛ ደረጃ መንገድ በመባል በሶስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ናቸው።

1- በከተማ ክልል ውስጥ፦ በሀገራችን ብዙ የከተማ ክልሎች ይገኛሉ (ወደ 1000 ገደማ)፡፡

በትልቋ ከተማ አዲስ አበባም ሆነ በጣም ጥቂት የሚባል ነዋሪ ባላቸው የክልል ከተሞቻችን ያለው የፍጥነት ወሰን ገደብ አንድ አይነት ነው፡፡

2- ከከተማ ክልል ውጪ ፡- ከከተማ ክልል ውጪ የሚገኙ መንገዶች በሶስት አይነት ደረጃ ባላቸው አውራ ጎዳናዎች የተከፋፈሉ ናቸው ፡፡
እነሱም፡- 1ኛ ፥ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ አውራ ጎዳና ይባላሉ።

ከከተማ ክልል ውጪ የሚገኙ 3ቱ የአውራ ጎዳና ደረጃወች ትርጓሜ

1- 1 ኛ ደረጃ አውራ ጎዳና፡- ማለት ሀገርን ከሀገር የሚያገናኙ መንገዶች ማለት ነው፡፡

2- 2 ኛ ደረጃ አውራ ጎዳና ፡- ማለት ክፍለ ሀገርን ➡ ከክፍለ ሀገር ፣ / ክልልን ➡ ከክልል የሚያገናኙ መንገዶች ማለት ነው ።

3- 3 ኛ ደረጃ አውራ ጎዳና፡- ማለት ወረዳን ➡ ከወረዳ ፣ ቀበሌን ➡ ከቀበሌ እና የዞን መንገዶችን የሚያገናኙ መንገዶች እና ፒስታ መንገዶች

ተሽከርካሪዎች በሶስት አይነት የጠቅላላ ክብደት መጠን ተከፍለው እናገኛቸዋለን፡፡

እነሱም፡-

1- ከ3500 ኪሎ ግራም በታች (ለምሳሌ አውቶሞቢል ፣ ሞተር ሳይክል ፣ ባጃጅ.... ወዘተ) ።

2- ክብደታቸው ከ 3500 - 7500 ኪሎ ግራም ለሆነ (ለምሳሌ ህዝብ-1 ፣ ደረቅ-1 .... ወዘተ)።

3- ከ 7500 ኪሎ ግራም በላይ (ለምሳሌ ህዝብ-2 ፣ ደረቅ-2 .... ወዘተ)።

የተሽ/ሪ ዓይነት

በከተማ ክልል ውስጥ

ከከተማ ክልል ውጭ

በ1ኛ ደ/አ/ጎ

በ2ኛ ደ/አ/ጎ

በ3ኛ ደ/አ/ጎ

▶ ለአውቶሞቢል ፣ ለሞተር ሳይክል ፣ ለባጃጅ ወይም
▶ ክብደታቸው ከ 1500 ኪ.ግ - 3500 ኪ.ግ ለሆኑ ወይም
▶ ክብደታቸው ከ3500 ኪ.ግ. በታች ለሆኑ

60

100

70

60

▶ ለህዝብ-1 ፥ እስከ 30 ሰው ወንበር ያለው
▶ለደረቅ-1 እስከ 35 ኩንታል ለሚጭን
▶ ለመለስተኛ የህዝብ
▶ ለመለስተኛ የጭነት
▶ ለታክሲ ፣ ለንግድ እና ለኪራይ ተሽከርካሪዎች እና
▶ ክብደታቸው ከ 3500 - 7500 ኪ.ግ ለሆነ

40

80

60

50


▶ ለከፍተኛ የህዝብ
▶ ለከፍተኛ የጭነት ወይም
▶ ለትልልቅ ካባድ ተሽከርካሪዎች ወይም
▶ ክብደታቸው ከ 7500 ኪ.ግ. በላይ ለሆነ

30

70

50

40


Chapter 7 በቂ ርቀትን ጠብቆ ሰለ ማሽከርከር

☞ በቂ ርቀትን ጠብቆ ሰለ ማሽከርከር

እጅግ በጣም ተጠጋግቶ ማሽከርከር ለአደጋ መፈጠር አንደኛው ምክንያት ነው ግጭቶችንም ያበዛል፣ በመሆኑም አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት ጊዜ ማስተዋል የሚገባቸው፡-

• ፍጥነታቸውን

• የመንገዱን አጠቃላይ ሁኔታ

• የትራፊኩን/ተንቀሳቃሹን/ ብዛት

• የአካባቢው አየር በርቀት የማሳየት መጠን ጉም፣ኃይለኛ ዝናብ፣ አቧራ፣ ጨለማ፣ ጭጋግ፣... ወዘተ.

• የተሽከርካሪውን የቴክኒክ አቋም

• የራሳቸውን ንቃትና ቅልጥፍና አደጋን ፈጥኖ የመከላከል ችሎታቸውን

• የጤንነታቸውን መሟላትና ከእነዚሁ ጋር ተያይዘው ሊታሰብባቸው የሚገባቸውን ሁኔታዎች ሁሉ መገናዘብ ናቸው፡፡

▶ ስለዚህ አንድ አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ ሁሉ ከኋላ በሚከተሉት ተሽከርካሪዎችና በእርሱ መሀከል በቂ ርቀት መኖር ይገባዋል፡፡

▶ ምክንያቱም ከፊት ለፊቱ የሚጓዘው አሽከርካሪ በድንገት ወይንም በአጋጣሚ አቅጣጫውን ሊለውጥ ወይም ሊያቆም ስለሚችል ነው፡፡

▶ ስለዚህ በእንዲህ ያለ ጊዜ መኪናን ከግጭት ለማዳን ሲባል ፈጥኖ በማሰብና በመወሰን ፍጥነትን መቀነስ የግድ በመሆኑ አሽከርካሪው በቂ ርቀት ባለመጠበቁ ምክንያት በተፈጠረ ሳቢያ ቸልተኛነት ያልተጠበቀ ድንገተኛ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ማወቅ ይገባል፡፡

❖ ስለዚህ ማንኛውም አሽከርካሪ የሚከተለውን የማሽከርከር ሥነ ሥርዓት ማክበር ይኖርበታል፡፡

▶ በእያንዳንዱ 1ዐ ኪ.ሜ የመኪና ፍጥነት ውስጥ ከምትከተለው መኪና ቢያንስ 6 /ስድስት ሜትር/ ወይም የአንድ አውቶሞቢል ርዝማኔ ያህል ወደ ኋላ ራቅ በማለት ማሽከርከር፡፡

▶ ከዚህም ሌላ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚኖርበት መንገድ ላይ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቢሆን አቅጣጫን በመለዋወጥ እየተሹለከለኩ መቅደምና የአሽከርካሪው የማሽከርከር እንቅስቃሴ ሌሎችን ግራ በማጋባት ለአደጋ መንስኤ መሆን የለበትም፡፡

▶ የመኪናዎች ርዝማኔ አንዱ ከሌላው ስለሚለያይ ማንኛውም አሽከርካሪ በራሱና ከፊቱ ለፊቱ ከሚንቀሳቀሰው ሌላ ተሽከርካሪ ፍጥነት አንፃር ወደ ኋላ መራቅ አለበት፡፡

▶ የመንገዱ ርዝማኔ የሚለካው በሚጠቀመው ወይንም በያዘው ተሽከርካሪ ርዝመት መጠን መሆን አለበት፡፡

❖ ለዚህም የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡

ከላይ በ Chapter-6 ላይ ሰለ ሀገራችን የፍጥነት ወሠን ደንብ በተገለፀው መሠረት የሚያሽከረክር ማንኛውም አሽከርካሪ ቀጥሎ ከታች በተገለፀው መሰረት ከፊት ለፊቱ ካለው ተሽከርካሪ መራቅ አለበት፡፡

የተሽከርካሪው ፍጥነት

ከፊቱ ካለው ተሽከርካሪ መራቅ ያለበት

በሰዓት ከ40-50 የሚያሽከረክር

20 ሜትር ፣ የሶስት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ50-60 የሚያሽከረክር

25 ሜትር ፣ የአራት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ70-80 የሚያሽከረክር

30 ሜትር ፣ የአምስት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ90-100 የሚያሽከረክር

36 ሜትር ፣ የስድስት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ100-110 የሚያሽከረክር

43 ሜትር ፣ የሰባት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ110-120 የሚያሽከረክር

48 ሜትር ፣ የስምንት መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ130-140 የሚያሽከረክር

55 ሜትር ፣ የዘጠኝ መኪና ርዝማኔ

በሰዓት ከ150-160 የሚያሽከረክር

58 ሜትር ፣ የአስር መኪና ርዝማኔ


Chapter 8 የፍሬቻ አጠቃቀም እና የአሽከርካሪዎች የእጅ ምልክቶች

Part 1 የአሽከርካሪዎች የእጅ ምልክቶች

ጥቅም:- ፍሬቻ ወይም የፍሬን መብራት በብልሽት ምክንያት በማይሰራበት ጊዜ ወይም በግልጽ ከርቀት በማይታይበት ጊዜ አሽከርካሪዎች

▪ ከቆሙበት ቦታ ተነስተው ጉዞ ሲቀጥሉ

▪ የያዙትን ነጠላ መሥመር ትተው ወደ ሌላ ሲቀይሩ

▪ የሚከተሉትን ተሽከርካሪ ሲቀድሙ

▪ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ሲታጠፉ

▪ በስተግራ ወደ ኋላ ዞረው ሲጓዙ

▪ የሚያዩትን ተሽከርካሪ እንዲያልፍ ሲፈቀድላቸው እና

▪ ለማቆም ሲፈልጉ የሚያሳዮዋቸው የእጅ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።








1

2

3

1- ወደ ግራ ለመታጠፍ

2- ወደ ቀኝ ለመታጠፍ

3- ፍጥነትን ለመቀነስ

Part 2 የፍሬቻ አጠቃቀም

የፍሬቻ አጠቃቀም

❖ የግራ ፍሬቻ ☜

❖ የቀኝ ፍሬቻ ☞

▶ ወደግራ አቅጣጫ (ረድፍ) ለመቀየር

▶ ወደ ቀኝ አቅጣጫ (ረድፍ) ለመቀየር

▶ ከቆምንበት ለመነሳት

▶ ለመቆም

▶ ለመደረብ (ለመቅደም)

▶ ለማስቀደም

▶ ወደ ግራ ለመታጠፍ

▶ ወደ ቀኝ ለመታጠፍ

▶ ከቀኝ ወደ ግራ ለመዛወር

▶ ከግራ ወደ ቀኝ ለመዛወር


ክፍል /Chapter 9 የእሳት አደጋን መከላከል

የእሳት አፈጣጠርና የማጥፊያ ዘዴው

እሳት እንዴት ይፈጠራል?

ሶስቱ የእሳት ውህዶች ወይም እሳት የሚፈጥሩ ነገሮች
የሚከተሉት ሶስት ነገሮች በአንድ ላይ ከተገናኙ እሳት ይፈጠራል፡፡
እነሱም፡-
1- ሙቀት
2- ኦክስጂን/አየር
3- ተቀጣጣይ/ነዳጅ ነገር

ሶስቱ ተቀጣጣይ/ነዳጅ ነገሮች

ተቀጣጣይ/ነዳጅ ነገሮች በሶስት መልክ ይገኛሉ ፡፡

እነሱም ፡-

1- በጠጣርነት/ጠጣር ተቀጣጣይ ነገሮች፡-
ለምሳሌ፦ እንጨት፣ ጨርቅ፣ ወረቀት፣ ጥጥ፣ . . .

2- በፈሳሽነት/ፈሳሽ ተቀጣጣይ ነገሮች፡-
ለምሳሌ ፦ ኬሮሲን (ነጭ ጋዝ)፣ ናፍጣ፣ ቤንዚን፣ የተለያዩ ዘይቶች፣ . . . ናቸው።

3-በጋዝነት/ጋዝ (ጋዛማ) ተቀጣጣይ ነገሮች፡-
ለምሳሌ፡- ሚቴን፣ ቡቴን፣ ፕሮፔን፣ . . .ናቸው።

ሶስቱ እሳትን የማጥፊያ ዘዴወች

1. ማፈን

2. ማስራብ እና

3. ማቀዝቀዝ ይባላሉ።

መቀጣጠል (መንደድ) የጀመረን እሳት ለማጥፋት ከላይ እሳት ለመፍጠር ግድ ካስፈለጉን ሶስት ነገሮች አንዱን ማጉደል ወይም ማስወገድ በቂ ነው፡፡

1- ማፈን፦ ኦክስጅን ማሳጣት ☞ ይህ የማጥፋት ዘዴ ማፈን በመባል ይታወቃል፡፡

2- ማስራብ፦ ተቀጣጣይ ነገሮችን ማስወገድ (ማሳጣት) ☞ ይህ የማጥፋት ዘዴ ማስራብ በመባል ይታወቃል፡፡

3- ማቀዝቀዝ፦ ሙቀት ማሳጣት ☞ ይህ እሳትን የማጥፋት ዘዴ በማቀዝቀዝ እሳትን የማጥፋት ዘዴ በመባል ይታወቃል፡፡

አራቱ የእሳት አመዳደብና የማጥፊያ መሣሪያዎቻቸው

1- የ "ሀ" ክፍል ወይም የ A ክላስ ወይም 1ኛ ደረጃ እሳት

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከጠጣር ተቀጣጣይ ነገሮች ሲሆን የማጥፊያ መሳሪያውም ውሃ ይሆናል፡፡

2- የ "ለ" ወይም የ B ወይም 2ኛ ደረጃ እሳት፦

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከፈሳሽ ተቀጣጣይ ነገሮች ሲሆን የማጥፊያ መሳሪያውም
- ድራይ ፓውደር
- ግፊት ያለው ማፈን የሚችል ካፊያ ውሃ፣
- ድራይ ፎም፣
- ካርቦን ዳይኦክሳይድ ይሆናሉ ።

3- የ "ሐ" ወይም የ C ወይም 3ኛ ደረጃ እሳት፦

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው በኤሌክትሪክ እና ከጋዝ ተቀጣጣይ ነገሮች ሲሆን፡- የማጥፊያ መሳሪያውም
- ድራይ ፓውደር
- ሲቲሲ (CTC)
- ቢሲኤፍ (BCF)
- ከርቦዳይኦክሳይድ ይሆናሉ፡፡

4- የ "መ" ወይም የ D ወይም 4ኛ ደረጃ እሳት፦

የዚህ ክፍል እሳት የሚነሳው ከብረት ንጥረ ነገሮች ማለትም በፖታሺየም፣ በማግኒዚየም፣ በካልሲየም . . . ሲሆን፡- የማጥፊያ መሳሪያውም
- ድራይ ፓውደር፣
- ደረቅ ደቃቃ አሸዋ፣
- ታልክኖራፕ፣ . . .ይሆናሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፦

1. የ "ለ" ወይም የ "B" ወይም የ 2ኛ ደረጃ እሳትን ለማጥፋት ካፊያነት ወይም ግፊት የሌለው ውሃን መጠቀም እሳቱን ሊያባብሰው ስለሚችል በጣም አደገኛ ይሆናል፡፡

2. የ "ሐ" ወይም የ "C" ወይም የ3ኛ ደረጃ እሳትንና የ "መ" ወይም የ "D" ወይም የ 4ኛ ደረጃ እሳትን ለማጥፋት ውሃና እርጥበት ያለውን ነገር መጠቀም በፍፁም የተከለከለ ነው፡፡

በተሽከርካሪ ላይ እሳት እንዲነሳ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች

- የተላጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች

- የሞተር ከመጠን በላይ መሞቅ

- የፈሰሱ ወይም የተንጠባጠቡ ነዳጆች

- እና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡


Chapter 10 ዋና ዋና የተሽከርካሪ የመሳሪያዎች

ዋና ዋና የተሽከርካሪ የመሳሪያዎች፡-

1- የመገናኛ መሳሪያዎች፦ አሽከርካሪውን ከሌሎች የትራፊክ ተሳታፊዎች ጋር መግባባት እንዲችሉ የሚያደርግ የመሳሪያ አይነት ሲሆን
እነሱም ፡-
ጡሩንባ (ክላክስ)፣ ፍሬቻ፣ የማስጠንቀቂያ መብራቶች፣ የማቆሚያ መብራት፣ የኋላ ማርሽ መብራት፣ የፍሬን መብራት፣ የአሽከርካሪ የእጅ ምልክት፣....... እና እንዲሁም በሀገራችን ብቻ አጭር ረጅም መብራት (የሰላምታ መብራት) ነገር ግን ዋና ተግባሩ ለትዕይንት ነው።.

2- የመከላከያ መሳሪያዎች፦ በግጭት ጊዜ አሽከርካሪውን ተሳፋሪውንና እንዲሁም በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ ዕቃዎችን ከጉዳት የሚከላከሉ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለምሳሌም፡- የግንባር መስታወት፣ ፓራውልት (መጋጫ)፣ የመቀመጫ ቀበቶ (ሲት ቤልት)፣ የአየር ከረጢት (ኤር ባግ)፣ . . .

3- የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፦ አሽከርካሪው የትራፊክ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች ናቸው፡፡
እነሱም ፡-
ለምሳሌ፡- የግንባር መስታወት፣ ስፖኪዮ፣ የዝናብ መጥረጊያ፣ የግንባር መብራት፣ የጨረር መከላከያ፣ . . .

4- የተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፦ ተሽከርካሪውን ከተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ የምንቀሳቀስበት ክፍል ሲሆን ለምሳሌ ያህልም፡- የኢንጅን (ሞተር) ማስነሻ ቁልፍ፣ የነዳጅ መስጫ ፔዳል፣ የማርሽ ዘንግ ከፍሪሲዮን ጋር፣ ፍሬን፣ መሪ፣ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡


Chapter-End