Total Pageviews

የማሽከርከር ስልት

Ethiopian Driver book

የማሽከርከር ስልት ስልጠና ማለት

  1. በተለያየዩ የመልካ-ምድራዊ አቀማመጥ ባላቸው አስቸጋሪ መንገዶች ላይ እንዴት ማሽከርከር እንዳለብን የሚሠጥ ስልጠና ነው።

  2. አስቀድሞ አደጋን ተከልክሎ ስለ ማሽከርከር የሚሠጥ ስልጠና ነው።

  3. የመንገድ ህግጋቶችን ጠብቀው ስለ ማሽከርከር የሚሠጥ ስልጠና ነው።

  4. ተሽከርካሪን ለጉዞ ስለማዘጋጀት

  5. እራስን እንደ አሽከርካሪ ለጉዞ ስለማዘጋጀት

  6. የምንጓዝበትን የትራፊክ እና የመንገድ ሁኔታ ስለመገመት

  7. ሞተር ሰለ ማስነሳት ማጥፍት

  8. ከቆምንበት ሰለ መነሳት ስለ መቆም ሰለማቆም እና ሞተር ስለ ማጥፋት የሚሠጥ ስልጠና ነው።

ለተሳካ የማሽከርከር ሂደት ልናጤናቸው የሚገቡ 3 ቱ ነገሮች

  1. ተሽከርካሪን ለጉዞ ማዘጋጀት

  2. እራስን እንደ አሽከርካሪ ለጉዞ ማዘጋጀት

  3. የምንጓዝበትን የትራፊክ እና የመንገድ ሁኔታ መገመት ናቸው።

Chapter 1 ዋና ዋና የተሽከርካሪ የመሳሪያዎች

ዋና ዋና የተሽከርካሪ የመሳሪያዎች፡-

1- የመገናኛ መሳሪያዎች፦ አሽከርካሪውን ከሌሎች የትራፊክ ተሳታፊዎች ጋር መግባባት እንዲችሉ የሚያደርግ የመሳሪያ አይነት ሲሆን
እነሱም ፡-
ጡሩንባ (ክላክስ)፣ ፍሬቻ፣ የማስጠንቀቂያ መብራቶች፣ የማቆሚያ መብራት፣ የኋላ ማርሽ መብራት፣ የፍሬን መብራት፣ የአሽከርካሪ የእጅ ምልክት፣....... እና እንዲሁም በሀገራችን ብቻ አጭር ረጅም መብራት (የሰላምታ መብራት) ነገር ግን ዋና ተግባሩ ለትዕይንት ነው።.

2- የመከላከያ መሳሪያዎች፦ በግጭት ጊዜ አሽከርካሪውን ተሳፋሪውንና እንዲሁም በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ ዕቃዎችን ከጉዳት የሚከላከሉ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለምሳሌም፡- የግንባር መስታወት፣ ፓራውልት (መጋጫ)፣ የመቀመጫ ቀበቶ (ሲት ቤልት)፣ የአየር ከረጢት (ኤር ባግ)፣ . . .

3- የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፦ አሽከርካሪው የትራፊክ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች ናቸው፡፡
እነሱም ፡-
ለምሳሌ፡- የግንባር መስታወት፣ ስፖኪዮ፣ የዝናብ መጥረጊያ፣ የግንባር መብራት፣ የጨረር መከላከያ፣ . . .

4- የተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፦ ተሽከርካሪውን ከተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ የምንቀሳቀስበት ክፍል ሲሆን ለምሳሌ ያህልም፡- የኢንጅን (ሞተር) ማስነሻ ቁልፍ፣ የነዳጅ መስጫ ፔዳል፣ የማርሽ ዘንግ ከፍሪሲዮን ጋር፣ ፍሬን፣ መሪ፣ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡


Chapter 2 ተሽከርካሪን ለጉዞ ስለ ማዘጋጀት


ሀ- ተሽከርካሪን ለጉዞ ማዘጋጀት

አንድ አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን ከማሽከርከሩ በፊትሁልጊዜ የዕለት ተዕለት ስራው ሊሆን ከሚገባው ነገሮች መሀል የተለያዩ የተሽከርካሪውን ክፍሎች መፈተሽ ወይም በጥሩ ሁኔታ ላይ ስለመገኘታቸው ማረጋገጥ ሲሆን አሽከርካሪዎች በፍተሻ ወቅት ማንኛውም ጉድለት ካጋጠማቸው ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት በራሳቸው መቅረፍ የሚችሉት ከሆነ በራሳቸው አልያም የባለሙያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ በባለሙያ ችግሩን መፍታት መቅረፍ ይገባቸዋል።

የተሽከርካሪ ፍተሻ

ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈተሹ ፍተሻዎች

1.ሞተር ከመነሳቱ በፊት የሚፈተሹ ፍተሻዎች

2.ሞተር ከተነሳ በኃላ የሚፈተሹ ፍተሻዎች

3.በጉዞ ላይ የሚፈተሹ ፍተሻዎች

1.ሞተር ከመነሳቱ በፊት የሚፈተሹ ፍተሻዎች

ሞተር ከመነሳቱ በፊት የሚፈተሹ ፍተሻዎች በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-

1.ውጫዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ

2.ውስጣዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ

1.ውጫዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ

• ፍሳሽ ማየት

• የዝናብ መጥረጊያ ጎማ ማየት

• ስፖኪዮ ማየት

• የመብራት መስታወት ማየት

• የጎማ ንፋስ መጠን ማየት

2.ውስጣዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ

ውስጣዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ ባጭሩ ባ-መ-ዘ-ው-ን(አ)ነ ወይም BLOWAF ፍተሻ ይባላል።

ይህም ማለት

• ባ - ባትሪ

• መ - መብራት

• ዘ - ዘይት

• ው - ውሃ

• ን - ንፋስ/አየር

• ነ - ነዳጅ ነዳጅ ማለት ናቸው።

በ እንግሊዘኛው ደግሞ

• B - Battery/ባትሪ

• L - Light/መብራት

• O - Oil/ዘይት

• W - Water/ውሃ

• A - Air/ንፋስ/አየር

• F - Fuel/ነዳጅ ማለት ነው።

3. ሞተር ከተነሳ በኃላና በጉዞ ላይ የሚፈተሹ ፍተሻዎች

የዳሽ ቦርድ መለኪያዎች፡ጠቋሚዎችንና ማስጠንቀቂያ መብራቶችን መከታተል

ፍሬን፣ መሪና ነዳጅ መስጫ መስራቱን ማረጋገጥ

መፈተሽ የሚገባቸው ክፍሎች ውጫዊ የተሽከርካሪ ክፍሎች ፍተሻ

1- ውጫዊ ክፍሎችን ስለመፈተሽ /የምልከታ ፍተሻ (ቪዢዋል ኢኒስፔክሽን :-

አሽከርካሪዎች ሁሌም የተሽከርካሪ ፍተሻ መጀመር የሚገባቸው ሙሉ የተሽከርካሪውን አካል አንዴ በመዞር በአይናቸው ጠቅላላ ሁኔታውን በመቃኘት እንዲሁም ጎንበስ በማለት የፈሰሰ ወይም የተንጠባጠበ ነገር እንዳለ በመቃኘት መሆን ይገባል።

እንዲህ አይነት ፍተሻዎች ቀጣዩን ፍተሻችንን ከመርዳታቸው ባሻገር ያላስተዋልናቸውን ወይም ያላየናቸውን ነገሮች ድንገት ሊጠቁሙን ስለሚችሉ ጥቅማቸው ብዙ ነው።


2- የሞተር ፣ የፍሬን ፣ የፍሪሲዬን እና የመሪ ዘይት ስለመፈተሽ

2.1- የሞተር ዘይት ፡ - ሁል ጊዜ አሽከርካሪዎች የሞተር (ኢንጅን) ዘይትን ከመፈተሻቸው በፊት ተሽከርካሪው ቀጥ ባለ ቦታ ላይ (ዳገታማ ወይም ቁልቁለታማ ባልሆነ ቦታ ላይ) ስለመቆሙ እርግጠኛ መሆን ይገባቸዋል።

▶ ንፁህና ብናኝ የሌለው ጨርቅ ማዘጋጀት

▶ የተሽከርካሪውን ኮፈን በጥንቃቄ መክፈት።
( ሎክ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ሎኩ መያዙን እርግጠኛ መሆን ይገባል )

▶ ሊቤሎውን (ዲፕስቲኩን) መሳብና ባዘጋጀነው ንፁህ ጨርቅ አማካኝነት እላዩ ላይ የሚገኘውን ዘይት አፅድቶ መልሶ ማስገባት (መክተት)

▶ ሊቤሎውን (ዲፕስቲኩን) በድጋሚ በመሳብ ወደ ታች ሳይዘቀዝቁት ወደ ላይም ሳያደርጉት (ሳያቆሙት) አግድም ቀጥ አድርጎ በመያዝ።

▶ በሊቤሎው (ዲፕስቲኩ) ላይ የሚገኘውን ዘይት መጠን መብዛትና ማነስ ማየት ፣ መቆሸሽ አለመቆሸሽ እና መወፈር መቅጠኑን ማረጋገጥ።

ከፍተሻ በኃላ

- የዘይት መጠኑ ካነሰ መጨመር

- የዘይት መጠኑ ከበዛ መቀነስ

- ዘይቱ ከቆሸሸ፣ ከወፈረ እና ከቀጠነ ዘይቱን ሙሉ ለሙሉ መቀየር ይገባል።

- በተጨማሪም ዘይቱን ከመጨመር ፣ ከመቀነስ ፣ ከመቀየር ጎን ለጎን እነዚህን ነገሮች ማድረግ ለምን አሰፈላጊ እንደሆነ በማወቅ ተገቢውን ስራ ማከናወን ተገቢ ነው። ያለበለዚያ ግን ችግሩ በድጋሚ ሊያጋጥመን ይችላል።

2.2- የመሪ ዘይት ፡ - በሞተር እገዛ የሚሰራ የመሪ / በመሪ ዘይት የሚሠራ (ፓወር ስትሪንግ) ክፍል ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከናወን የፍተሻ ዓይነት ነው።

  • የተሽከርካሪው መሪ (ጎማ) ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ።

  • ክዳኑን መክፈትና የዘይቱን መጠን ማረጋገጥ።

  • በብዙ ተሽከርካሪዎች ላይ የዘይት መጠን መመልከቻው ከክዳኑ ጋር አብሮ ወይም ተጣብቆ የተሰራ ነው።

ከፍተሻ በኃላ

- የዘይቱ መጠን ካነሰ ተገቢው ቦታ ድረስ ተገቢውን ዘይት መጨመር


2.3- የፍሬን ዘይት ፡ - ፍሬናቸው በዘይት ወይም በዘይትና በታመቀ አየር ልዩ ቅንብር የሚሰራ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከናወን የፍተሻ አይነት ነው።

- የተሽከርካሪው ፍሬን ፔዳል አለመረገጡን ማረጋገጥ

- የዘይቱ መጠን MAX ወይም የላይኛው ምልክት ላይ መሆኑን በማየት ማረጋገጥ።

ከፍተሻ በኃላ

- የዘይቱ መጠን ካነሰ ተገቢው ቦታ ድረስ ተገቢውን ዘይት መጨመር


2.4- የፍሪሲዮን ( ክለች ) ዘይት ፡ - ፍሪሲዮናቸው በዘይት ወይም በዘይትና በታመቀ አየር ልዩ ቅንብር የሚሰራ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከናወን የፍተሻ አይነት ነው።

- የተሽከርካሪው ፍሪሲዮን ፔዳል አለመረገጡን ማረጋገጥ

- የዘይቱ መጠን MAX ወይም የላይኛው ምልክት ላይ መሆኑን በማየት ማረጋገጥ።

ከፍተሻ በኃላ

- የዘይቱ መጠን ካነሰ ተገቢው ቦታ ድረስ ተገቢውን ዘይት መጨመር


Note ፦ ሙሉ ለሙሉ በሚያሰኝ ሁኔታ አብዛኛው ተሽከርካሪዎች ለፍሬንና ለፍሪሲዮን የሚጠቀሙት የዘይት አይነት አንድ አይነት ነው።

2.5- የአውቶማቲክ ካምቢዮ ዘይት ፡ - ተሽከርካሪያችን አውቶማቲክ ካምቢዮ ( ትራንስሚሽን ) የሚጠቀም ከሆነ ልክ እንደ ሞተር ዘይት ሁሌም የዚህን ዘይት መጠን ( ሁኔታ ) መፈተሽ ይገባል።


3- የራዲያተር ውሃ ፣ የባትሪ ውሃ እና ሌሎች ውሃ የሚየስፈልጋቸውን ክፍሎች ስለመፈተሽ

3.1- የራዲያተር ውሃ ፍተሻ ፡ - የሞተር (የኢንጅን) የማቀዝቀዣ ዘዴያቸው በውሃ የሚሰራ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከናወን የፍተሻ አይነት ነው።

  • የተሽከርካሪው ሞተር (ኢንጅን) የቀዘቀዘ መሆኑን ማረጋገጥ

  • የራዲያተር ክዳኑን መክፈት

  • አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ላይ የራዲያተር ውሃ የሚታየውና የሚረጋገጠው በኤክስፓንሽን ታንክ ወይም በሪዘርቫየር በኩል ሊሆን ይችላል።
    Note:- የዚህ አይነት ተሽከርካሪ ከሆነ

- የኤክስፓንሽን ታንኩን ወይም የሪዘርቫየሩን ክዳን መክፈት

- የውሃውን መጠንና ንፅህና በራዲያተሩ ውስጥ እንዲሁም ኤክስፓንሽን ታንክ ወይም በሪዘርቫየር ካላቸው በዚሁ ውስጥ መመልከት

ከፍተሻ በኃላ

- የውሃው መጠን ካነሰ መጨመር

- ውሃው ከቆሸሸ መቀየር


3.2- የባትሪ ውሃ ፡ - በእያንዳንዱ የባትሪ ሴል ወይም በስድስቱም ሴል ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ (የተጣራ ውሃና አሲድ ድብልቅ) መጠን መመልከት

ከፍተሻ በኃላ

- በባትሪው ሴል ውስጥ ማለትም በስድስቱም የባትሪ ሴል ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ (የተጣራ ውሃና አሲድ ድብልቅ) መጠን ካነሰ (የተጣራ ውሃና አሲድ ድብልቅ) መጨመር።


3.3- የግንባር መስታወት ማፅጃ ውሃ ፡ - የዚህን ማፅጃ ውሃ መጠን መመልከት።

ከፍተሻ በኃላ

- የግንባር መስታወት ማፅጃ ውሃው ካነሰ መጨመር


4- ለጎማ የሚደረጉ ፍተሻወች

፡ -

4.1- የጎማ የነፋስ መጠን ፡ - በአቅራቢያችን ወደሚገኝ ጎሚስታ ደርሰን መቶ በመቶ የጎማችንን የነፋስ መጠን እስክናረጋግጥ ድረስ በአይናችን የነፋሱን መጠን መገመት

4.2- የጎማ የጥርስ ሁኔታ ፡ - ከምናሽከረክርበት ኪ.ሜ፣ የትራፊክ ሁኔታ፣ የአየር ንብረት.... አንፃር የጎማችንን የጥርስ ሁኔታ መመልከት

4.3- የጎማችንን የብሎን (ኮለኔት) ሁኔታ ፡ - በጎማ መፍቻ ወይም በጎማ ማሰሪያ በመጠቀም የጎማችንን ጥብቀት ማረጋገጥ

ከፍተሻ በኃላ

  • የጎማ ነፋስ ለማሽከርከር በማይመች ሁኔታ ከቀነሰ ተቀያሪውን (ስኮርት) ጎማ መቀየር።

  • ለማሽከርከር ብዙ የሚያውክ ካልሆነ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጎሚስታ ሄዶ የነፋሱን መጠን ማስተካከል ወይም ለባለሙያ ማሳየት

  • የጥርሱ ሁኔታ ካለቀ ወይም ለምንጓዝበት መንገድ አመቺና ተመጣጣኝ ካልሆነ መቀየር

  • የላሉ ወይም በአግባቡ ያልጠበቁ የጎማ ብሎኖች (ኮለኔት) ካሉ ማጥበቅ


5- የተለያዩ መብራቶችንና የኤሌትሪክ ክፍሎችን መፈተሽ ፡ - ተሽከርካሪው ላይ ተገጥመው የሚገኙትን የተለያዩ የመብራት አይነቶች ( የግንባር መብራት፣ የማቆሚያ መብራት፣ ፍሬቻ፣ የአደጋ መብራት፣ የፍሬን መብራት፣ የኋላ ማርሽ መብራት፣ የጭጋግ መብራት፣ . . .) ፣ ጡሩምባ ወይም ክላክስ

... መሰበር አለመሰበራቸውን ፤ መሰንጠቅ አለመሰንጠቃቸውን ፤ መቆሸሽ አለመቆሸሻቸውን ፤ መብራት አለመብራታቸውን ፤ ወዘተ መፈተሽ

- የግንባር መብራትን ለመፈተሽ ተሽከርካሪያችንን ግድግዳ ፊት ለፊት ወይም አንድ ወጥ የሆነ ጠፍጣፋ ነገር አቁመን ቢሆን በቀላሉ ረጅምና አጭር መብራታችን መስራት አለመስራቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

ከፍተሻ በኃላ

- የተሰበሩትንና የተሰነጠቁትን መቀየር

- የቆሸሹትን ማፅዳት

- የማይበሩትና እንዲበሩ መስራት ወይም ማሰራት


6- የተለያዩ የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ሰለመፈተሽ ፡ - ተሽከርካሪው ላይ ተገጥመው የሚገኙትን የተለያዩ የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ማለትም የግንባር መስታወት፣ የኋላ ትዕይንት መቆጣጠሪያዎችን ( ስፖኪዮ ) ፣ የጨረር መከላከያ፣ የዝናብ መጥረጊያ እና የመሳሰሉት መሰበር አለመሰበራቸውን፤ መሰንጠቅ አለመሰንጠቃቸውን፤ መቆሸሽ አለመቆሸሻቸውን ወዘተ መፈተሽ

ከፍተሻ በኃላ

- የተሰበሩትንና የተሰነጠቁትን መቀየር

- የቆሸሹትን ማፅዳት

- የማይሰሩትን መስራት ወይም ማሰራት


7- የተለያዩ የፔዳል አይነቶችን ስለመፈተሽ ፡ - ተሽከርካሪያችን ላይ የሚገኙትን ሁለት ወይም ሶስት ወይም አራት ( እንደተሽከርካሪው አይነት ስለሚለያዩ ነው ) ፔዳሎችን በመርገጥና በመልቀቅ ቦታቸው በፍጥነት መመለሳቸውንና ወይም እዛው ታች አለመቅረታቸውን ማረጋገጥ።

ከፍተሻ በኃላ

✿ - (በፍሪሲዮን ፔዳል) መበላሸት ምክንያት ☞ ማርሽ ለማስገባት ልንቸገር ስለሚንችል

✿ -(በፍሬን ፔዳል) መበላሸት ምክንያት ☞ በአግባቡ ተሽከርካሪያችንን ለመቆጣጠር ልንቸገር ስለሚንችል

✿ -(የነዳጅ መስጫ ፔዳል) በመበላሸቱ ምክንያት ☞ ነዳጅ ሰጥቶ ሊቀር ስለሚችል ለአደጋ መፈጠር ምክንያት እንዳይሆንብን በቶሎ ችግሩን ፈልጎ ማስተካከል ወይም ማሰራት ይጠበቅብናል።

8- የተለያዩ ችንጋዎችን መጥበቅ ወይም መላላት ሰለመፈተሽ

ከኮሎ (ክራንክ ሻፍት) መካኒካል ሀይል ተቀብለው የሚሽከረከሩ የተለያዩ ክፍሎች ለምሳሌ የውሃ ፓምፕ፣ የዘይት ፓምፕ፣ ቫኪዩም ፓምፕ፣ ዲናሞ፣ ወዘተ ሀይል የሚቀበሉበት ችንጋ በአግባቡ መጥበቁንና አለመጥበቁን መፈተሽ።

ከፍተሻ በኃላ

▶ ከመጠን በላይ ጠብቀውም ከሆነ ከመጠን በታች ላልተውም ከሆነ አስፈላጊው መጠን ድረስ ብቻ ማጥበቅ።


9- አስፈላጊ መፍቻዎች እና መሳሪያዎች መኖራቸውን ስለመፈተሽ

ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መፍቻዎች፣ ክሪክ ከእነማንሻውና ማውረጃው፣ የጎማ መፍቻ፣ ተቀያሪ( ስኮርት ) ጎማ፣የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች፣ ሶስት ማዕዘን አንፀባራቂ፣ የመጀመሪያ ህክምና መስጫ ሳጥን፣ እና የመሳሰሉት በተሽከርካሪው ላይ መኖራቸውን ማረጋገጥ።

ከፍተሻ በኃላ

▶ ከላይ ከዘረዘርናቸው ነገሮች በተሽከርከሪያችን ላይ የሌሉትን መሳሪያዎች ማሟላት ይገባናል።


10- የዳሽ ቦርድ ላይ ጠቋሚ መሳሪያዎችን ሰለመፈተሽ ፡ -

እነዚህ መሳሪያዎች እንደተሽከርካሪው አይነት ቢለያዩም ተሽከርካሪው ላይ የሚገኙት ጠቋሚ ምልክቶች ሞተር ከመነሳቱ በፊትም ሆነ ከተነሳ በኋላ አልያም ተሽከርካሪው እየተጓዘ ሁሉም በትክክል መስራታቸውን መፈተሽ ይገባል።

ከፍተሻ በኃላ

▶ የማይሰራ ጠቋሚ ምልክት ካለ መስራት ወይም ማሰራት

Chapter 3 እራስን እንደ አሽከርካሪ ለጉዞ ማዘጋጀት

2- እራስን እንደ አሽከርካሪ ለጉዞ ማዘጋጀት

ማንኛውም አሽከርካሪ ሁልጊዜ ተሽከርካሪውን ከማሽከርከሩ በፊት በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ መዘገጀት ይገባዋል።

1- የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ (የመንጃ ፈቃድ) መያዙን ማረጋገጥ

2- ድፍን ጫማ ማድረጉን ማረጋገጥ (በሲሊፐርም ሆነ ባዶ እግር ማሽከርከር ስለማይፈቀድ)

3- በማሽከርከር ላይ ተፅዕኖ (ጫና) እንደማይፈጥር በሀኪም ካልታዘዘ መዳሐኒት ውጪ አለመውሰዱን ወይም አለመዋጡን እርግጠኛ መሆን

4- ማንኛውንም የአልኮል መጠጥ አለመጠጣቱት እርግጠኛ መሆን

5- ማንኛውንም አደንዛዥ ዕፅ አለመጠቀሙን እርግጠኛ መሆን

6- በማሽከርከር ላይ ተፅዕኖ ከሚፈጥር ማንኛውም ብስጭት ፣ ንዴት ፣ ሐዘን ፣ ደስታ ፣ ድካም ፣ እና ከመሳሰሉት ስሜቶች ውጪ መሆኑን እርግጠኛ መሆን።

7- ጋቢና ገብቶ በአግባቡ በር መዝጋት

8- የመቀመጫ ቀበቶ ማሰር(ቤልት)


Chapter 4 የምንጓዝበትን የትራፊክ እና የመንገድ ሁኔታ ሰለመገመት

3- የምንጓዝበትን የትራፊክ እና የመንገድ ሁኔታ መገመት

ሁልጊዜ አሽከርካሪዎች መዘጋጀት ካለባቸው ነገሮች አንዱ ከፊት ወይም በኋላ የምንሄድበትን የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲሁም የመንገዱን ሁኔታ (ደረጃ) ማወቅ ወይም መገመት ይገኝበታል።

ይህም ሌላ አማራጮች ካለን እንድናማትርና በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ወይም ከመንገዱ ለማሽከርከር አለመመቸት አንፃር ከሚደርስ መናደድ፣ መበሳጨት፣ ማዘን፣ ትዕግስት ማጣት ከመሳሰሉት ስሜቶች እንድንርቅ ወይም ከወዲሁ አምነን እንድንቀበል ይረዳናል።

Chapter 5 የማሽከርከር ስልት ሁለት

የማሽከርከር ስልት ሁለት

በዚህ ክፍል ላይ የምናየው ሀሳብ በማሽከርከር ስልት አንድ ላይ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ከአደረግን በኃላ የተሽከርካሪውን ሁኔታ ፣ እንደ አሽከርካሪ የራስን ሁኔታ ፣ የመንገዱን እና የትራፊኩን ሁኔታ በማጤን እንዴት እንደምናሽከረክር እንመለከታለን።

Part 5.1 ሞተር ለማስነሳት

አሽከርካሪዎች ሞተር ለማስነሳት ማድረግ የሚገባቸው

• የእጅ ፍሬን በአግባቡ መያዙን ማረጋገጥ

• ፍሪሲዎን በመርገጥ ማርሽ ዜሮ ላይ ማድረግ /አውቶማቲክ ማርሽ ከሆነ N/P

• የሞትር ማስነሻ ቁልፉን በአግባቡ ማስገባት

• የተቆለፈውን መሪ በመክፈትና On ላይ ወይም ኳድሮ በመክፈት ናፍጣ ሞተር ከሆነ በማሞቂያ ተጠቅሞ ማሞቅ።

ቤንዚን ኢንጂን ከሆነ ቾክ ቫልቭ መሳብ።

• የኢንጂን ማስነሻ ቁልፉን On ወደ Start ወደሚለው መጠምዘዝና ማስነሳት ።

ለማስነሳት መቆየት ያለበት ለ30 ሰከንድ ብቻ ነው፡፡

• ኢንጂኑ ከ30 ሰከንድ በላይ አልነሳ ካለ ሙሉ ለሙሉ ወደ lock ወደሚለው ቁልፉን በመመለስ ድጋሚ መሞከር፡፡

• ኢንጂን ከተነሳ እንደ ሞተሩ ሙቀት በሚኒሞ/በአይድሊንግ ማሰራት

Part 5.2 የኢንጂን አጠፋፍ

የኢንጂን አጠፋፍ

• ተሽከርካሪውን ሙሉ ለሙሉ ፍሬንና ፍሪሲዮን በመርገጥ ማቆም

• የእጅ ፍሬን በማያዝ እና ማርሽ ዜሮ ላይ ማድረግ/አውቶማቲክ ማርሽ ከሆነ P ላይ ማድረግ

• ፍሪሲዮንና የእግር ፍሬን መልቀቅ

• እንደ ኢንጂኑ/ሞተሩ ሙቀት መሰረት በአይድሊንግ ማሰራት

• የኢንጂን ማሰነሽ ቁልፍ ከOn ወደ Lock ማዞር

Part 5.3 ተሽከርካሪን ከቆመበት ጉዞ ስለማስጀመር

ተሽከርካሪን ከቆመበት ጉዞ ስለማስጀመር

1ኛ. ማየት

አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪያቸውን አንቀሳቅሰው ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት በመሀልና በኃላ መመልከቻ ስፖኪዮ/መስታወት ከኃላ የመንገዱን/አከባቢውን/ ሁኔታ መቃኘት አለባቸው ።

▶ በግራና ቀኝ ጎን መመልከቻ ስፖኪዮ/መስታወት አጠቃላይ የትራፊኩን ሁኔታ ማየትና መቆጣጠር አለባቸው ።

2ኛ. የማርሽ አጠቃቀም ማወቅ

የኢንጂኑ ሀይል/ጉልበት ከፍተኛ ለሆነ ተሽከርካሪዎች

• ዳገት ላይ ከሆኑ 1ኛ ማርሽ ማስገባትና መጠቀም

• ሜዳ ላይ ጭነት የጫነ ከሆነ 1ኛ ማርሽ ማስገባትና መጠቀም

• ሜዳ ላይ ጭነት ያልጫነ ከሆነ 2ኛ ማርሽ ማስገባትና መጠቀም

• ቁልቁለት ላይ ከሆነ የጫነም ሆነ ያልጫነ 2ኛ ማርሽ ማስገባትና መጠቀም

Part 5.4 የፍሬቻ አጠቃቀም

ፍሬቻ አጠቃቀም

❖ የግራ ፍሬቻ ☜

❖ የቀኝ ፍሬቻ ☞

▶ ወደግራ አቅጣጫ (ረድፍ) ለመቀየር

▶ ወደ ቀኝ አቅጣጫ (ረድፍ) ለመቀየር

▶ ከቆምንበት ለመነሳት

▶ ለመቆም

▶ ለመደረብ (ለመቅደም)

▶ ለማስቀደም

▶ ወደ ግራ ለመታጠፍ

▶ ወደ ቀኝ ለመታጠፍ

▶ ከቀኝ ወደ ግራ ለመዛወር

▶ ከግራ ወደ ቀኝ ለመዛወር

• ፍሬቻ የማይሰራ ከሆነ በእጅ ምልክት መሰጠት አለበት።

• አሽከርካሪዎች ወደ ሚሄዱበት ወደ ሚያቋርጡበት አቅጣጫ ተገቢውን የፍሬቻ ምልክት ማሳየት አለባቸው ።


Part 5.5 የጉዞ አጀማመር

የጉዞ አጀማመር

• አሽከርካሪው ጉዞ ሲጀምር በድጋሚ በጎንና በመሀል መመልከቻ መስታወት/ስፖኪዮ/ የአከባቢውን/የትራፊክ ሁኔታ በማየት ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ መስጠት

• የእጅ ፍሬን መልቀቅ

• በግራ እግር ፈሪሲዮን ግማሽ በመልቀቅ በቀኝ እግር ነዳጅ ድጋፍ ማድረግ

• እንደ መንገዱ ሁኔታ የመሪ እርምጃ መውሰድ

• ተሽከርካሪው ዳገት ላይ የቆመ ከሆነ ተሽከርካሪው ወደ ኃላ እናዳይንሸራተት ባላንስ ሰርቶ መነሳት

ባላንስ ማለት

• በፍሪሲዮንና በነዳጅ አመጣጥኖ ተሽከርካሪን ለተወሰነ ደቂቃ/ሰከንድ/ለማቆም ወይም እንዳይንሸራተት ማድረግ ማለት ነው።

• ሀይል ከሞተር ወደ ፍሪሲዮን መተላለፍ የሚጀምርበት ቦታ ላይ የሚፈጠር ክስተት ነው።

✦የፊት ባላንስ ለመስራት

• ተሽከርካሪን ሙሉ ለሙሉ በፍሬንና በፍሪሲዮን ማቆም

• ፍሪሲዮን ፔዳል በመርገጥ 1ኛ(➀) ማርሽ ማስገባት

• ፍሪሲዮን ፔዳል ግማሽ ድረስ መልቀቅ

• የእግር ፍሬን በመልቀቅ ሞተር በማይጠፋ መልኩ ነዳጅ መስጫ ፔዳል ላይ ድጋፍ ማድረግ

✦የኃላ ባላንስ ለመስራት

• ተሽከርካሪን ሙሉ ለሙሉ በፍሬንና በፍሪሲዮን ማቆም

• ፍሪሲዮን ፔዳል በመርገጥ የኃላ(Ⓡ) ማርሽ ማስገባት

• ፍሪሲዮን ፔዳል ግማሽ ድረስ መልቀቅ

• የእግር ፍሬን በመልቀቅ ሞተር በማይጠፋ መልኩ ነዳጅ መስጫ ፑዳል ላይ ድጋፍ ማድረግ

Part 5.6 ርቀትን ጠብቆ ስለማሽከርከር

ርቀትን ጠብቆ ስለማሽከርከር

እጅግ ተጠጋግቶ ማሽከርከር ለአደጋ መፈጠር አንደኛው ምክንያት ነው።

እጅግ ተጠጋግቶ ማሽከርከር ግጭቶች ያበዛል፣በመሆኑም አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት ጊዜ ማስተዋል የሚገባቸው፡-

• ፍጥነታቸውን፡ የመንገዱን አጠቃላይ ሁኔታ፣የትራፊኩን/ተንቀሳቃሹን/ብዛት

• የአከባቢው የአየር ሁኔታ መጠን ይኸውም ጉም፣ኃይለኛ ዝናብ፣አቧራ፣ጨለማ፣ጭጋግ

• የተሽከርካሪ የቴክኒክ አቋም

• የራሳቸው ንቃትና ቅልጥፍና

ስለዚህ አንድ አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ ሁሉ ከኃላ ከሚከተሉ ተሽከርካሪዎችና በእርሱ መካከል በቂ ርቀት መኖር ይገባዋል።

ምክንያቱም ከፊት ለፊቱ የሚጓዘው አሽከርካሪ በድንገት ወይም በአጋጣሚ አቅጣጫውን ሊለውጥ ወይም ሊያቆም ስለሚችል።

በእያንዳንዱ 10ኪ.ሜ. የመኪና ፍጥነት ውስጥ ከምንከተለው መኪና ቢያንስ 6 ሜትር ወይም የአንድ መኪና ርዝመት ያህል ወደ ኃላ ራቅ በማለት ማሽከርከር።

የመንገዱ ርዝማኔ የሚለካው በሚጠቀመው ወይም በያዘው ተሽከርካሪ ርዝመት መጠን መሆን አለበት።

Part 5.7 ተሽከርካሪን ስለመቅደም

ተሽከርካሪን ስለመቅደም

• መንገዱ ባለ ሁለት አቅጣጫ ሆኖ የመንገዱ ስፋት አነስተኛ በሆነበት መንገድ ላይ ከፊት በተቃራኒ አቅጣጫ መንገድ የሚመጣን ተሽከርካሪን ፍጥነት ማገናዘብና መገመት።

• በግራ በኩል እና መሀል ስፖኪዮ አማካኝነት ከኃላና ከጎን ተሽከርካሪ አለመኖሩን ማየት

• ከነበርንበት ረድፍ በመጠኑ ወደ ግራ ወጣ በማለት ከፊት ለፊት የሚመጣ መኖር ያለመኖሩንና ከፊት ያለውም ተሽከርካሪ ሌላውን ሊቀድመው አለመፈለጉን ማረጋገጥ።

• በበቂ ጊዜና ርቀት አስፈላጊውን የግራ ፍሬቻ ማሳየት

• ከፊት ያለው ተሽከርካሪ ድንገት አቅጣጫ ለውጦ አደጋ እንዳያስከትል በጥሩምባ ወይም በመብራት የማስጠንቀቂያ ምልክት ማሳየት።

• ተሽከርካሪውን መሉ ለሙሉ መቅደምዎን ሲያረጋግጡ የቀኝ ፍሬቻ አብረቶ ወደ ነበሩበት

መመለስ ቅድሚያ ወደ ሚሰጥባቸው ቦታዎች ስለማሽከርከር

• ማንኛውም የተሽከርካሪ አሽከርካሪ ከአንድ መስቀለኛ መንገድ በደረሰ ግዜ ከመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ለገባ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት።

• ከልዩ ልዩ አቅጣጫ ሁለት ወይም ከሁለት የሚበዙ ተሽከርካሪዎች በአንድ ግዜ ከመስቀለኛ መንገድ የደረሱ እንደሆነ ማንኛቸውም አሽከርካሪ ከቀኝ በኩል ለተቃረበ ተሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት

• በአንድ መስቀለኛ መንገድ ላይ የትራፊክ ክብ ሰርቶ እንደሆነ ወደ ክቡ የተቃረበ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ አስቀድሞ ክቡን በመዞር ላይ ላሉት ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ መስጠት አለበት።

• ዳገት በማውጣት ላይ ያለ ማንኛውም አሽከርካሪ ቅድሚያ መስጠት አለበት ➡ ነገር ግን የህዝብ ማመላለሻ የያዘ አሽከርካሪ በሁለቱም አቅጣጫም ቢሆን ቅድሚያ አለው።

• ከግል ቤት መውጫ ወይም ከመጋቢ መንገድ ወደ ዋና መንገድ ሲገባ ቆሞ ቅድሚያ መስጠት አለበት።

• ከመቆሚያ ስፍራ ወይም ከመንገድ ጠርዝ ወደ መተላለፊያ ስገባ ቅድሚያ መስጠት አለበት

• በሚታጠፉና ዞሮ በሚመለሱበት ወቅት ቅድሚያ መስጠት አለበት

የተሽከርካሪ ፍጥነት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች

• መንገድ የተሰራበትን አከባቢ/የቦታው የጂኦግራፊ አቀማመጥ ሁኔታ

• የመንገዱን አሰራር

• የተሽከርካሪው የጭነት ልክ/የሞተሩ ጉልበትና አስተማማንነት

• የአከባቢ የአየር ሁኔታ

• የትራፊክ/ተላላፊ ብዛት

Part 5.8 ተሽከርካሪን ስለማቆም

ተሽከርካሪ ስለማቆም

• በጉዞ ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ከተለያየ አቅጣጫ ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ አይተው እርምጃ ለመውሰድ ወስነው እግራቸውን ከነዳጅ መስጫ ፔዳል እስከ ፍሬን መያዣ ፔዳል ለማድረስ በአማካይ የአንድ ሰከንድ 0.75 ያህል ግዜ ይፈጃል።

የመቆሚያ ጠቅልል ርቀት

የመቆሚያ ጠቅላላ ርቀት በሚከተሉት ምክንያቶች ሊያጥር ወይም ሊረዝም ይችላል

• አደጋ በመለያ ግዜ

• እርምጃ በመውሰጃ ግዜ

• በጎማ ጥርስ ሁኔታ

• በፍሬን ብቃት

• የመንገድ አይነትና ሁኔታ

• በተሽከርካሪ ላይ በሚኖር ክብደት

ተሽከርካሪ ለረጅም ጊዜ አቁሞ ስለመሄድ

የተሽከርካሪው ፊት ወደ ዳገት ከሆነ

• 1ኛ ማርሽ ማስገባት

• መሪ ወደ መንገዱ ጠርዝ ማዞር

• ታኮ ማድረግ

የተሽከርካሪው ፊት ወደ ቁልቁለት ከሆነ

• የኃላ ማርሽ ማስገባት

• መሪ ወደ መንገዱ ጠርዝ ማዞር

• ታኮ ማድረግ

Part 5.9 በአደገኛ ሁኔታ ስለማሽከርከር

በአደገኛ ሁኔታ ስለማሽከርከር

በምሽት ስለማሽከርከር

• በምሽት ስታሽከረክር ለአደጋ የተጋለጥክ ነህ ➡ ምክንያቱም በምሽት ጊዜ ሊፈጠር የሚችል አደጋን ወዲያውኑ ተረድተህ መልስ ለመስጠት በቀን ጊዜ በፍጥነት ስታያቸው የነበሩ ሁኔታዎች በማታ ጊዜ በፍጥነት ስለማይታዮ እርምጃ ለመውሰድ ትዘገያለህ።ስለዚህ የምሽት አነዳድ ከቀን አነዳድ ሶስት ግዜ የበለጠ አደገኛ መሆኑ በጥናት ተረጋግጡዋል።

• በምሽት አነዳድ ወቅት የመንገዱ፣ የአሽከርካሪውና የሌሎች አሽከርካሪዎች ሁኔታና የተሽከርካሪው ሁኔታ በአነዳድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

የሌሎች አሽከርካሪዎች ሁኔታ

• በምሽት የማየት ሀይላቸው በመቀነሱ

• ከብርሀን ወደ ጨለማ መንገድ ሲገቡ ዓይናቸው የማየት ሀይሉን ለማስተካከል ጊዜ ስለሚወስድ

• ከፊት ለፊት በሚመጣ ተሽከርካሪ መብራት የአሽከርካውን አይን የማየት አቅም ላይ ችግር ስለሚፈጥር

የመንገዱ ሁኔታ

• አንዳንድ መንገዶች በቂ መብራት አላቸው ሌሎች ደግሞ የላቸውም ስለዚህ አሽከርካሪው

በመንገዱ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በተሽከርካሪው መብራት ብቻ እንዲጠቀም ሊገደድ ይችላል።

በተሽከርካሪው ሁኔታ

• የተሽከርካሪ አጭር የግንባር መብራት 50ሜትር፣ረጅሙ የግንባር መብራት ደግሞ 100ሜትር ማሳየት ይችላል።

• የግንባር መብራት ከቆሸሸ ሊኖር የሚችለው ነጸብራቅ በግማሽ በመቀነሱ።

• የግንባር መብራት በትክክለኛው አቅጣጫ ካልተስተካከለ።

በምሽት ስናሽከረክር ልንከተላቸው የሚገቡ ቅደም ተከተሎች

• መንገድ ከመጀመርህ በፊት ንቁና በቂ እርፍት የወሰድክ መሆንህን አረጋግጥ

• በሽምት የጸሀይ መነጽር አትጠቀም።

የምሽት መነጽር ካደረግህ ንጹህና ያልተጫረ መሆኑን አረጋግጥ

• ተሽከርካሪህን ፈትሽና አጽዳ

• የግንባር መብራህ የሌሎችን እይታ እንዳይከለክል ተጠንቀቅ

• የውስጥ መብራት በጣም እንዳያንጸባርቅ አድርግ

• የእንቅልፍ ስሜት ከተሰማህ አቁምና እረፍት ውሰድ

በዝናባማ የአየር ሁኔታ ስለማሽከርከር

• በሚያንሸራትት መንገድ ላይ በዝግታ አሽከርክር

• ከቆምክበት ስትንቀሳቀስ በዝግታ ተንቀሳቀስ

• በኩርባ መንገድ ላይ በጥንቃቄ አዙር

• በኩርባ መንገድ ላይ ፍሬን አትጠቀም

• ጎማ እንዲሸራተት ሊያደርግ ስለሚችል ከሚገባው በላይ ፍሬን አትጠቀም

• በከባድ ዝናብ ካሽከረከርክ ፍሬን ሊረጥብ ስለሚችል ተጠንቀቅ

• በቆመ ወይም እየተጓዘ ያለ ውሀ ውስጥ አታሽከርክር

• ተሽከርካሪ በጭቃ ከተያዘ የሬዶታ ማርሽና አክስል ሎክ ተጠቀም

በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ስለማሽከርከር

• በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ተሽከርካሪን ያለማሽከርከር ይመከራል

• የጭጋግ ወይም አጭር የግንባር መብራት ተጠቀም

• ወደ ጭጋጉ ቦታ ፍጥነት ቀንሰህ ግባ

• አደጋ ቢደርስ ተሽከርካሪህን ለማቆም ተዘጋጅ

• የውጪ መስታወት በጉም ከተሸፈነ የዝናብ መጥረጊያ ተጠቀም

• የውስጥ መስታወት በጉም ከተሸፈነ የውስጥ ማሞቂያ/ኤር ኮንዲሽነር/ ወይም ፎጣ ተጠቀም

Chapter 6 ሞተር ሰለማስነሳት

❖ ሞተር ስለማስነሳት

1- የሞተር ማስነሻ ቁልፉን ማስገባት ወይም መሰካት

2- የእጅ ፍሬን መሳቡን ማረጋገጥ

3- የእግር ፍሬን መርገጥ

4- ማርሽ ዜሮ ማድረግ (ማንዋል ካምቢዮ ከሆነ )

5- በሞተር ማስነሻ ቁልፍ አማካኝነት ማሞቅ;(ለናፍጣ ሞተር)

6- ቾክ ቫልቭ መሳብ(በቤንዚን ሞተር ላይ ሆኖ ማንዋል ቾክ ቫልቭ ላላቸው)

7- የሞተር ማስነሻ ቁልፍ ተጠቅሞ ማስነሳት ( ሞተር ቶሎ አልነሳም ቢል እንኳን የሞተር ቁልፍን ከ 30 ሰከንድ በላይ በ START ቦታ ላይ ማቆየት አይመከርም)

8- የሳብነውን ቾክ ቫልቭ መመለስ ( የቤንዚን ሞተር ከሆነ )


Chapter 7 ከቆምንበት ሰለመነሳት

❖ -ከቆምንበት ለመነሳት

1- የግራ ፍሬቻ ማብራት

2- ፍሬን መርገጥ

3- ፍሪሲዮን መርገጥ(ማንዋል ካምቢዮ ከሆነ)

4- አስፈላጊውን ከባድ ማርሽ ማስገባት ☞ ይህም ማለት

ዳገት እና ጭነት የጫነ ተሽከርካሪ ከሆነ 1 ኛ ማርሽ

▶ ቁልቁለትና እና ጭነት የጫነ ተሽከርካሪ ከሆነ 2 ኛ ማርሽ

▶ ቀጥተኛ እና ለጥ ባለ መንገድ ላይ እንደ ተሽከርካሪው ጉልበት 1 ኛወይም 2 ኛ ማርሽ መጠቀም እንችላለን።

5- እንደአስፈላጊነቱ መሪን ወደ ቀኝ መያዝ

6- ፍሪሲዮን ግማሽ መልቀቅ ( የሞተሩ ድምፅ እስኪቀየር )

7- የእጅ ፍሬን መልቀቅ ( ማውረድ )

8- የኋላ ትዕይንት መቆጣጠሪያ ( ስፓኪዮ ) መመልከት ☞ በይበልጥ የግራ ስፖኪዮ መመልከት

9- ፍሪሲዮን እየለቀቁ ፍሬን ለቆ ነዳጅ መደገፍ ( በትንሹ )

Chapter 8 ስለ መቅደም/መደረብ

ሐ - ለመደረብ ( ለመቅደም ) ፡ -

1- የግራ ፍሬቻ ማብራት

2- የግራ ስፖኪዮ መመልከት

3- መሪን እንደአስፈላጊነቱ ወደ ቀኝ መያዝ ( ማዞር )

4- ከፊት ለፊት ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ማረጋገጥ ( ባለ ሁለት አቅጣጫ መንገድ ከሆነ )

5- የተሽከርካሪን ፍጥነት መጨመር


Chapter 9 ለመቆም ፣ ለማቆም እና ሞተር ለማጥፋት

መ - ለመቆም ፣ ለማቆም እና ሞተር ለማጥፋት ፡ -

1- የቀኝ ፍሬቻ ማብራት

2- የቀኝ ስፖኪዮ መመልከት

3- ፍጥነትን መቀነስ

4- መሪን እንደአስፈላጊነቱ ወደ ቀኝ መያዝ

5- ፍሬን ረግጦ ማቆም (አውቶማቲክ ካምቢዮ ላይ)

6- ፍሬንና ፍሪሲዮን ረግጦ ማቆም (ማንዋል ካምቢዮ)

7- የእጅ ፍሬን መሳብ

8- ማርሽ ዜሮ ማድረግ

9- ተሽከርካሪው በጥሩ ሁኔታ መቆሙን በትዕይንት መስታዎት ተጠቅሞ ማየት

10- እንደአስፈላጊነቱ ሞተር ማጥፋት

11- አስፈላጊውን ከባድ ማርሽ ማስገባት ማለትም

የቆመነው በዳገት ላይ ከሆነ 1 ኛ ማርሽ ማስገባት።

ነገር ግን የቆመነው በቁልቁለት ወይም ቀጥ ያለ መንገድ ላይ ከሆነ የኋላ (R) ማርሽ ማስገባት አለብን።

Chapter 10 አደጋን ተከላክሎ ስለማሽከርከር

በዳገት እና ቁልቁለት ላይ ስለማሽከርከር

- አዲስ ተሽከርካሪ ዳገት ላይ ሲሽከረከር ቀላል ማርሽ መጠቀመ ሲችል

- ቁልቁለት ላይ ግን በከባድ ማርሽ ማሰር አለበት

- ነባር ተሽከርካሪ ዳገት ላይም ሆነ ቁልቁለት ሲወርድ በከባድ ማርሽ ማሰር አለበት

በፀሀያማ እና በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ስለማሽከርከር
- የፀሐይ መነፀር መጠቀም
- በከፍተኛ ፍጥነት አለማሽከርከር
- ስስ ልብስ መልበስ
- AC /cold/ መጠቀም
- በሙቀት ምክንያት ካስፖልት የወጣ ሬንጅ ሊያጋጥም ስለሚችል መጠንቀቅ
- የሞተር ችንጋ፣ የራድያተር ሆዞች በሙቀት ሊለጠጡ ስለሚችሉ መከታተል
- የዘየትና የውሐ መከታተያ ጌጆችን መቆጣጠር
- በየ 2ሰዓት (በ150) ኪ.ሜ ወይም 100 ማይል ጠቅላላ ተሽከርካሪውን አቁመው መፈተሽ አለባቸው
Note፦ በፀሐይ እና በሞቃታማ አየር ወቅት ስናሽከረክር የጎማ የአየር መጠን ይጨምራል፡፡
Note፦ በጉዞ ላይ እያለን የተሽከርካሪው የሞተር ሙቀት ከመጠን በላይ ቢሆንና የራዲያተር ውሀ ቢፈላብን የምንወስደው እርምጃ እና ቅደም ተከተል
1- ተሽከርካውን ዳር አስይዘን በመቆም ሞተር ሳይጠፍ በሚኒሞ/በአይድል/ በማሰራት የሞተሩ ሙቀት እንዲቀንስ ማድረግ
2- ሞተሩን አጥፍተን የራድያተር ክዳኑን በወፍራም ፎጣ በመያዝ ቀስ በቀስ ሙቀቱን አስተንፍሰን መክፈት
3- ሞተር አስነስተን ነዳጅ እየሰጠን የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን መሙላት
4- በድጋሜ ሞተር ካጠፋን በኃላ ትክክለኛውን የውሃ መጠን መሙላቱን ካረጋገጥን በ ኃላ የራድያተር ክዳኑን ገጥመን ሞተር አስነስተን ጉዞአችን እንጀምራለን

በምሽት ጊዜ ስለ ማሽከርከር
- አሽከርካሪዎች በምሽት ጊዜ ሲያሽከረክሩ በቀን ከሚያሽከረክሩት በ50% ለአደጋ የተጋለጥን ስለሆን፡-
▶ ንቁና በቂ ረፍት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው
▶ የእንቅልፍ ስሜት ከተሰማቸው ተሽከርካሪያቸውን አቁመው ሙሉ እረፍት መውሰድ አለባቸው
▶ የፀሐይ መነፀር አለመጠቀም
▶ የግንባር መስታውታቸው ንጽሕናውን የጠቀበ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው
▶ የፊት መብራት ብርጭቆዎች ንጽሕቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው
▶ የውስጥ መብራቶች በጣም እንዳያንፀባርቁ ማድረግ አለባቸው
▶ ረዠሙን መብራት ከከተማ ክልል ውጭ ሌላ አካል በማይጎዳ ሁኔታ መጠቀም አለባቸው።

በጭጋጋማ /ዝናባማ/ ወቅት ላይ ስለማሽከርከር
- በዝቅተኛ ፍጥነት ማሽከርከር
- የዝናብ መጥረጊያ መጠቀም
- ፎጣ መጠቀም
- AC/Hot/ መጠቀም
- ጎማ ሊሾ አለመሆኑን ማረጋገጥ እና ነፋስ አለመቀነሱን ማረጋገጥ
- አጭሩን የግንባር መብራት መጠቀም
- የጭጋግ ማቅለጫ ቢጫ መብራት /fog light/ መጠቀም
- ጭጋጉ ወይም እይታን የሚጋርደው ነገር ከጨመረ ሁሉንም የጎን መብራቶች ተጠቅሞ ተሽከርካሪን ዳር አስይዞ ማቆም

የሰከንድ ህግ
❖ የሰከንድ ህግ ማለት ከፊት ለፊት ካለ ተሽከርካሪ ርቀታችንን የማናስተካክልበት ህግ ነው።
ለምሳሌ ፦
1. የ3 ሰከንድ ህግ ➡ የ3 ሰከንድ ህግ ማለት ተሽከርካሪ በ3 ሰከንድ የሚሄደው ርቀት ማለት ነው።
በመንገድ ላይ ስናሽከረክር ከፊታችን ካለው ተሽከርካሪ ምን ያህል ርቀት ላይ እንዳለን ለማወቅ የ3 ሰከንድ ህግ የላቀ ጠቀሜታ አለው።
ከፊትህ ያለው ተሽከርካሪ ያለበትን ቦታ ምልክት ያዝና አንድ ሺህ አንድ፣አንድ ሺህ ሁለት፣ አንድ ሺህ ሶስት በማለት ቁጠር። ቁጥሩን ሳትጨርስ ከቦታው ከደረስክ ተጠግተህ እያሽከረከርክ ስለሆነ የተወሰነ መራቅ ይጠበቅብሀል ማለት ነው።
2.የ4 ሰከንድና ከዚያ በላይ
• በአንሸራታች መንገድ
• በትክክል ለማየት በሚያስቸግር ቦታ

የጉዳት መጠንን ሰለ መቀነስ
ብዙ አደጋዎች በአንድ ግዜ እንዳይከሰቱ መከላከል አንዱ የማሽከርከር ስልት ነው።
ለምሳሌ፦ በቀኝ በኩል እግረኛ በግራ በኩል ደግሞ ከባድ ተሽከርካሪ ቢገጥምህ ማድረግ ያለብህ ፍጥነትህን በመቀነስ ተሽከርካሪ ማሳለፍና እግረኛውን በጥንቃቄ ማሳለፍ ነው።

ከአደጋ የማምለጥ ስልት
በአደገኛ ሁኔታ አደጋ እንዳይከሰት የሚደርጉ 3 ነገሮች አሉ።
እነሱም
1.በመቆም
2.በመሪ ማዞር
3.ፍጥነት መጨመር ናቸው።

ፍጥነትን ተቆጣጥሮ በማሽከርከር አደጋን መከላከል
የተሽከርካሪ ፍጥነት የሚወሰው

1. በሌሎች ተሽከርካሪዎች ብዛትና ፍጥነታቸው

2. በመንገዱ ሁኔታ

3. በመንገድ ዳር በሚኖሩ እግረኞች ብዛት

4. በአየሩ ሁኔታ ይወሰናል።